ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ዐውደ ምሕረት
Photo
#ኑ-ዝምታን-እንተርጉም
---------------------------------

"አቤቱ ለአፌ ጠባቂን አኑርለት
የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ"

አጥብቆ ቢደግማት የዳዊትን መዝሙር
ተቀጥሮለት መሰል ጠባቂ ከናፍር
እንጂማ
ጆሮ አልባ በሆነች ባናጋሪ ዓለም
አስችሎት ዝም የሚል ትግስተኛ የለም

እኔስ ይመስለኛል የአባቴ ዝምታ
ቃል ያለማውጣቱ የጸትታው ፋታ
በጆሮ አልባ ሀገር
በደንቆሮ መንደር
ሰሚ በሌለበት
ፊደል ማባከኑ ቃላት ማበላሸት
መረበሽ ነው እንጂ መግባባት የለበት
ብሎ ይመስለኛል

እኔስ ይመስለኛል የአባቴ አርምሞ
በማይሰሙ ሰዎች ነብሰ ሥጋው ታሞ
ሰልችቶት ይሆናል አርሞ አርሞ
እንጂማ
እንዲያ ባይሆን ኖሮ
ባልሸሸ ነበረ ካደገበት ጓሮ

እኔስ ይመስለኛል ያባቴ አርሞሞ
ለአንድ መንጋ አንድ እረኛ
ይበቃዋል ካለ እውነተኛ
ከዛ ውጪ ነው ምንደኛ
ብሎ አስቦ በትትና
እራሱን ዝቅ አረገና
ከሰማይ ቤት ደጅ ጠና
የይህን ዓለም ንቋልና

እኔስ ይመስለኛ ያባቴ ዝምታ

አንድም ቢደርስ ነው ከቅዱሳን ተርታ
የበቃ ቢሆን ነው ምግባሩ የበረታ

ግን.... ግን
በሚንጫጫ ዓለም በማይሰማ ቅዬ
እንዴት አስችሏቸው ዝም አሉ አቡዬ?
ለፍላፊ ሳይሰሙት
ኸኸ ባይ ሳይነግሩት
ጆሮ በጠፋበት
ምላስ ሰንበር በዝቶ
ሲገድፍ የሚውል አንደበት ጾም ትቶ
ድንጋዮን ያልጣለው ከአፉ አውጥቶ
እንደምን ተጠራ ዳግማዊው አጋቶ ን ???

#ከኃ/ማርያም ተክለ ኤል
የካቲት 25 /2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ