ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#ከመጽሐፍት_አንደበት የተሰኘው መርኃ ግብራችን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ዘውትር ዓርብ ምሽት የሚቀርብ ይሆናል። በመርኃ ግብሩም ከቅዱሳት መጽሐፍት እየመራረጥን ለእናንተ ለውድ ተከታታዮቻችን የምናቀርብ ይሆናል።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
#ከመጽሐፍት_አንደበት

ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 69 ክፍል አንድ ከቁጥር 1 እስከ 5

#ይዘት ነገረ_ሥላሴ

አቅራቢ #ኢዮብ_ክንፈ

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#ከመጽሐፍት_አንደበት

«የበቃሁ ነኝ» የሚባለው መቼ ነው?

በአንድ ገዳም ውስጥ የሚኖር መነኩሴ ነበር፡፡ ከገዳሙ አበምኔት ጋርም ስለመንፈሳዊ ሕይወታቸው እያነሡ ሲወያዩ «አባቴ እኔ ዛሬ የዓለምን ኃጢአት ግፍና በደል አየሁ፡፡ ስለዚህ የበቃሁ ሆኛለሁ፡፡» ብሎ አጫወታቸው፡፡ አበምኔቱም «፥ወንድሜ ሆይ እስቲ በርትተህ ጸልይ ፥ገና ነህ፡፡» ብለው መለሱለት፡፡

እንዲሁም በሌላ ጊዜ ወደ አበምኔቱ ቀርቦ «አባቴ አሁንስ በቅቻለሁ ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ ሲወጡና ሲወርዱ የሕዝቡንም ኃጢአት ሲያስተሠርዩ አይቻለሁ፡፡» አላቸው፡፡ «ልጄ ሆይ ገና ነህ ፥ አሁንም በርታና ጸልይ፡፡» ብለው ሸኙት፡፡ ይህም መነኩሴ ወደ ዋሻው ገብቶ አብዝቶ ይጾምና ይጸልይ ጀመር፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ ስላየውም ራእይ ለአበምኔቱ እንዲህ ሲል ገለጠላቸው፡፤ «አባቴ ሆይ ዛሬስ በዓለም ሳለሁ የሠራሁትን ኃጢአት ሁሉ አንድ በአንድ አሳየኝ፡፡» አላቸው እርሳቸውም «ልጄ የበቃኸው አሁን ነው፤» ብለው አሰናበቱት፡፡

ክርስቲያናዊ ሕይወት ምድራዊ ፍላጎትንና የሰይጣንን ሽንገላ በመቃወም ሰማያዊ መንግሥት የሚወረስበት ምሥጢር በመሆኑ ፈተናውም የዛኑ ያህል ከበድ ይላል፡፡ ብዙ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን መመላለስ ቃለ እግዚአብሔር መማር ሲጀምሩ የራሳቸውን ኃጢአት እያሰቡ ከማልቃስ እና ንስሐ ከመግባት ይልቅ የሌላውን በደል መቁጠር ይጀምራሉ፡፡ «እነ እገሌ እንኳን እንዲህ አደረጉ ጉድ ነው!» ማለትን ያበዛሉ፡፡ ሌላውን ሲመለከቱ ሊድኑበት የሚችሉበትን ወርቃማ የንስሐ ጊዜ በከንቱ ያበላሹታል፡፡ መጽሐፍ ግን «ለዚህ ዓለም ከማይመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ» /፩ጢሞ ፬ ፥ ፯/ ይላል፡፤ ይህ መነኩሴ የተገለጠለት ራእይ ለመዳኑ የጠቀመው የራሱን ኃጢአት ያየ ጊዜ መሆኑን ከታሪኩ መረዳት እንችላለን፡፡ እኛስ የሚታየን የማን ኃጢአት ነው? የራሳችን ወይስ የሌላው?

ምንጭ፡- ከሰይጣን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ እና ሌሎች ከሚለው የተወሰደ፤

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit