ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ስለ ጥያቄዎ እናመሰግናለን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

#ወደ መልሱ ስናመራ በኦርቶዶክስ ተዋህዶና በካቶሊክ መካከል የሰማይና የምድር ያክል ብዙ ልዮነት አለ ልዮነት የለውም የሚሉ አካላትን በሦስት ከፍሎ መመልከት ይቻላል የመጀመሪያዎች ባለማወቅ ና በለመረዳት በየዋህነት አንድ ነን የሚሉ የዋሐን ሲሆኑ እነዚኞችን በማሳወቅ በመንገርና በማስተማር በቀናች ሃይማኖት ማጽናት ይጠበቅብናል ሁለተኞቹ ሆን ብለው ልዮነቱን እያወቁ ምዕመናንን በማደናገር በአንድነን ሽፋን ለማስኮብለል በማሰብ የሚናገሩት ሲሆን እነዚኞቹን ደግሞ በአፍ የሚያስተምሩትን በአፍ በመጽአፍ የሚያስተምሩትን በመጽሐፍ እንደ አመጣጣቸው መመለስ ይገባል “ወንድሞች ሆይ፥ እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።” — 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥14 ሦስተኞቹ ደግሞ ለመኮብለል በራሳቸው ተነሳሽነት ካመጡት ዝንባሌ የተነሳ ልዮነት የለም ወደ ሚል ዝንባሌያቸውን ትክክል ለማሰመሰል የሚጥሩ ወይም ለመሄድ ያኮበኮቡ ናቸውና ከእነዚኞቹ ነፍስ ይማር ብለን እንርቃቸዋለን
“ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።”
— 2ኛ ተሰሎንቄ 3፥6


ከዚህ አንጻር ጥቂት ልዮነቶቻችንን እንመልከት

#ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ

1) መንፈስ ቅዱስ የሰረጸው ከአብ ብቻ ነው ።

2) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋህዶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ሆኗል።

3)ንሰሐ መግባት በአጸደ ሥጋ እንጂ በአጸደ ነፍስ ሆና ንስሐ መግባት የለም ወይም አይቻልም ይህም ማለት በሰማይ መካነ ንስሐ የለም ።ያለውም የጽድቅ እና የኩነኔ ቦታ ነው። ለዚህም የአላዛርና የነዌ ታሪክ አስረጂ ነው። ሉቃ 16÷19

4) ሾማምንት የሚወስኑት ውሳኔ አይሳሳቱም ብለን አናምንም።

5) ህጻናትን ቃጠመቅን በኃላ ወዲያው 36 ዕዋሳቶቻቸውን ሜሮን እንቀባለን።

6) የምንሰዋው የክርስቶስን ክቡር ሥጋና ቅዱስ ደም ነፍስ የተለየው መለኮት የተዋሕደው ነው ብለን እናምናለን።

7 )ሕጻናት ከተጠመቁ በኃላ ሜሮን እንደተቀቡ ወዲያው ይቆርባሉ።

8)ከጳጳሳት በቀር ቀሳውስትና ዲያቆናት ማግባት ከፈለጉ አንዳንድ ሚስት አግብተው ክህነትን ተቀብለው ሊያገለግሉ ይችላሉ ።

9) ሥዕል እንስላለን እንጂ ሐውልት አንቀርጽም አንዳንድ የተሰሩ ሃውልቶች ቢኖሩም የኛ ትውፊት አይደለም ። ከ10ቱ ትዕዛዛት መእንዱና ግንባር ቀደሙ በፊትህ ማናቸውንም ምስል አትቅረጽ አትስገድላቸውም የሚል ነውና። ዘጸ20

10)ካህናት ጽሕማቸውን ያሳድጉታል እንጂ አይላጩትም እንኳን ካህናት ሥልጣነ ክህነት የሌላቸው ወንዶች እንኳ ከከንፈሮቻቸው ጽሕማቸውን እዳያራግፉ (እንዳይላጩ)ፍትሐ ነገሥት ያዛዛል።

11) ከጥንት እስከዛሬ በካህናትና በምዕመናን መካከል ያለ ልዮነት በእኩል ሥጋ ወደሙን እናቀብላለን ።

12)የሥጋውና ደሙ መንበር የሆነ የፈጣሪያችን ኅቡዕ ሥሞች የተቀረጹበት የምህረት መሰዊያ በሜሮን የከበረ ታቦት አለን።



#ካቶሊክ

1) መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ይሰርጻል ይላሉ።

2) ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት በሕርይ ነው ይላሉ።

3) ሰውች ስለሰሩት ኃጢያት ንስሐ ገብተው የንሰሐ ሥርዓትን እየፈጸሙ(ቀኖናቸውን)ሳይፈጽሙ ቢሞቱ በመንግሥተ ሰማያትና በገሃነም እሳት መካከል ልዮ የሆነ መካነ ንስሐ/Pergatory/ስላለ ወደዚያ በመሄድ መከራ ተቀብለው በኃላ መንግሥተ ሰማያት ይገባሉ ብለው ያምናሉ።

4) ፖፑ የክርስቶስ እንደራሴና የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በላይ ስለሆነ የሚወስነው ውሳኔ አይሳሳትም ብለው ያምናሉ።


5) ሕጻናትን አቁርበው ሜሮን የሚቀቡት አድገው ነፍስ ካወቁ በኃላ ነው።

6) የሚሰውት መሥዋዕት/የክርስቶስ ሥጋና ደም /ነፍስ ያለው መለኮት የተዋሐደው ነው ብለው ያምናሉ ።

7) ካህቶቻቸው በሙሉ ሚስት አያገቡም።



8) ከሥዕል በተጨማሪ ለጌታችን እና ለእመቤታች የድንጋይ ሃውልት ያቆማሉ።

9) ካህናቶቻቸው ጽሕማቸውን ይላጫሉ ::

10) ለቀዳስያን ካህናት ሥጋ ወደሙን ሲሰጡ ለምዕመናን ግን ሥጋውን ብቻ ያቀብላሉ በኃላ ከቫቲካን(ሀለት) 2 ጉባኤ ወዲህ ግን አሻሽለው ለምዕመናንም ሥጋና ደሙን እንዲሰጣቸው ወስነዋል። ሆኖም ሥጋውን በደሙ ውስጥ ነክረው ሥጋውን ብቻ ነው የሚያቀብሏቸው ። ይህንንም የሚያደርጉት ደም በሥጋ ያድራል ስለዚህ ደሙን ከሥጋው ያገኙታል የሚል ፍልስፍና ስላነገቡ ነው። ይህ ግን ዳቦን በሻይ ነክሮ እንደ ማውጣት ያለ ነውና ያስቅፋል ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በምሴተ አሙስ ለቅዱሳን ሐዋርያቶቹ ይህ ሥጋዬ ነው ብሎ ይህም ደሜ ነው ጠጡ አላቸው እንጂ ነክራችሁ ብሎ አላላቸውም። #ማቴ 26÷26


11) ታቦት የላቸውም

..........ይቆየን......
@YEAWEDIMERITE
ሕዳር 05/2013ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ

#ዓውደ ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit