ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
እሰይ ተወለደ.mp3
Unknown Artist
#መዝሙር #እሰይ_ተወለደ

በወንድማችን #ይትዐየን_ባዩ

ክራር #አቤኔዘር

እሰይ ተወለደ የዓለም መድኃኒት(3)
ይኸው ተወለደ የዓለም መድኃኒት(3)

ትንቢት ተናገሩ ነቢያት ሁሉ(3)
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ(2)

ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ(3)
የእስራኤል ንጉሥ ተወልዷል እያሉ(3)

ሰብአ ሰገል መጡ ይዘው እጅ መንሻ(3)
ወርቅ እጣኑን ከርቤ ለማርያም እጅ መንሻ(3)

ሕፃናት እንሂድ ከልደቱ ቤት(3)
ውሃው ሆኗልና ማርና ወተት(3)

በሶርያ ታየ ፈጣሪ እንደ እንግዳ(3)
ብስራተ ልደቱን ለሁሉ ሊያስረዳ(3)

"መልአኩም ቀርቦ እንዲህ አላቸው። እነሆ ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ። ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል።" ሉቃ 2:10-11

"መልካም የገና በዓል።"

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit