ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
Forwarded from @ፍኖተ ህይወት
💛ፆም እንዴት ይፆማል???💛
=====================
👏ከመብልና መጠጥ መታቀብ___ የፆሙ ጊዜ እስከሚፈጸም ድረስ ያለምንም መብልና መጠጥ መቆየት ነው፡፡
#መብሉም ፦ ከስጋ ፡ ከእንቁላል ፡ ከወተት ፡ ከቅቤ ፡ ከዓሳና በአጠቃላይ ከእንስሳት ውጤቶች ውጭጭጭ፡፡፡፡፡
#መጠጥ፦ አዕምሮን ጎድተው ሰውን አስክረው የማይገባ ከሚያሰሩና ከሚያሳስቡ የአልኮል መጠጦች መቆጠብ (ከጠላ ፡ አረቂ ፡ ከቢራ መጠጦች) ውጭጭጭ፡፡፡፡፡፡፡፡፡

👏#ህዋሳት ሁሉ ይጡሙ____

#አይን/// ፦ ውጫዊ በሆነ ውበት ከመቅበዝበዝ ፡ ለእግዚአብሔር ከሚጣረሩ ምልከታዎችና ትዕይንቶች/ፊልሞች/ እና ክፉ ነገሮችን ከማየት ይጡም ፡፡ የሚታዩ ነገሮች ሁሉ የአይን ምግብ ናቸውና፡፡፡፡፡

#እጅ/// ፦የሐጢአት ስራን ለመስራት ከመፍጠን ፡ ከሌብነት ፡ ከዝርፊያ ፡ ከህግ ወጭ ለመክበር ሲባል ትርፍን ከማግበስበስ ፡ ከሙስና እና ክፉ ነገሮችን ከማንሳት ከመያዝ ከማቀበል እና ከመስራት ይጡም፡፡፡፡፡፡፡፡

#ጆሮ///፦ ለሐጢአት ከሚጋብዙ ክፉ ወሬዎች ፡ ሐሜቶች ፡ ሙዚቃዎች ከመስማትና ከማዳመጥ ይጡም፡፡፡፡፡፡፡
<<< ሐሰተኛ ወሬ አትቀበል፤ ሐሰተኛ ምስክርም ትሆን ዘንድ ከኃጢአተኛ ጋር እጅህን አታንሣ።>>>
☞ዘጸ 23:1☜

#እግር/// ፦ ሐጢአትና ክፉ ነገር ለመስራት ለመግደል ፡ ለመሳደብ ፡ ከመሮጥ ይጡም፡፡፡፡
<<<ክፉውን ለማድረግ ብዙ ሰዎችን አትከተል፤ ፍርድንም ለማጥመም ከብዙ ሰዎች ጋር ተስማምተህ አትመስክር።>>>>
☞ዘጸ 23:2☜

#አፍ///፦ ከክፉ ንግግር ፡ ሐሰት ከመናገር ፡ በሐሰት ከመመስከር ፡ ከመሳደብ ፡ ከንቱ መሐላ ከመማል አሽሙር ከማውራትና ከአፍ ከሚወጡ አርካሽ ነገሮች ይጡም፡፡፡፡፡፡፡
<<<< ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው፡፡ ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና ፡ ሰውንም የሚያረክሰው ይህ ነው።>>>>
☞ማቴ 15:18-20☜

<<<ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።>>>>
☞ገላ 5:15☜

👏ህግንና ትዕዛዛትን ከመፈፀም____
✞ድሐውን በቸርነት ዕርዳው፤
✞የተጣላሃው ቢኖር ፈጥነህ ታረቅ፤
✞በባለእንጀራህ ቤት አትቅና፤
✞የተራበውን አብላው አጠጣው፤
✞የታረዘውን አልብሰው፤

👏 ከምግባር ሁሉ ታላቁ #ጸሎት ቢሆንም የጸሎት መሰረቱ #ፆም ነው፡፡ ስለዚህ "ፆም ፡ ጸሎት ፡ ስግደት" የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው፡፡፡፡፡፡፡፡፡

👏ስለዚህ እውነተኛ ጦዋሚ____ህሊናህ ሐጢአትን ከማሰብና ከማስታወስ ይጡም : ክፉ ነገርን ከመመኘት ይጡም ፡ አይኖችህ ከንቱ ነገሮችን ከመመልከት ይጡም ፡ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ ፡ አንደበትህ ከሐሜት ፡ በሌላው ላይ ከመፍረድ ከስድብ ፡ ከማታለል፡ ከሽንገላ ንግግሮች ይጡም ፡ እጅህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ፡ እግሮችህም ሐጢአትን ለመፈጸም ከመሔድ ይጡም፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

💛በፆም ወቅት የፍስክ ምግቦችን(ስጋ ፡ እንቁላል ፡ ወተት ፡ ቅቤ ፡ ዓሳ ...) ለምን አንመገብም???💛
====================

👏 አስተውሉ ፡ የፆም አላማ ሰውነትን በጸሎት በስግደት #አክስተንና #አድክመን ለአምላካችን ምስጋና የምናቀርብበት ነው ፡፡
ስለዚህ እነዚህ የእንስሳት ውጤቶች ደግሞ ሰውነትን የሚያከሱና የሚያደክሙ ሳይሆኑ ሰውነትን #የሚያዳብሩ #የሚያጠነክሩ ስለሆኑ በፆም ወቅት አንመገባቸውም፡፡፡፡፡
"ለምሳሌ"፦
"በትንቢተ ዳንኤል 1 : 5-20"
የዳንኤልና የሰለስቱ ደቂቅ ታሪክ
ያንብቡት፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

"ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን አሜን!!!"

ይቀላቀሉን______
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷@sanctuaryTewahedo 🌹
🌷@sanctuaryTewahedo 🌹
🌷@sanctuaryTewahedo 🌹 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹