ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
መስቀል አማትበው ሕዝ ቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከ ኪሳቸው ክተቱት። ወዲያው ወታደሮች በሩምታ ተኩስው ገደሉ ዋቸው። ይህ እንደሆነ አስገድዶ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ።
ማታ ከአስገዳዩ ኮለኔል ጋር ተገኖኝተን ስንጫወት 'በዚህ ቄስ መገደል አኮ ሕዝቡ ተደሰቷለ' እለኝ 'እንዴት?' ብለው 'አላየህም ሲያጨበጭብ' አለኝ። እኔም #ባታውቀው_ነው_እንጂ_የሕዝቡ_ባህል_ሲናደድም_ያጨበጭባል' አልኩት። 'እንዴት?' ቢለኝ እጄን እያጨበጨብኩ አሳየሁት። ከዚህ በኋላ " የሆነው ቢሆን እኔ ትልቅ ማስታወሻ አግኝቼአለሁ " ብሎ አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ ይዘውት የነበረውን መስቀልና መጽሐፍ ቅዱስ የኪስ ስዓታቸውን ጭምር አሳየኝ። #መጽሐፍ_ቅዱሱ መሐል ለመሐል በጥይት ተስንጥቋል። መስቀሉም ልክ በመሐከሉ ላይ ጥይት በስቶት ወጥቷል። የኪስ ስዓታቸውንም እንዳየሁት፡ እንደዚሁ ጥይት በስቶ ታል"
ጠላት ድል ተደርጎ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የብፁዕነታቸውን አኩሪ ታሪክ ትውልድ ሲዘክርላቸው እንዲኖር መታሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ በግርማዊ ቀዳማዊ ንጉሠ ነገሥት አሳሳቢነት #ሐምሌ 16 ቀን 1938 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እምብርት ሐውልት ቆሞላቸዋል ::

...........ይቆየን...... #አባታችን_ከአቡነ_ጴጥሮስ_ረድኤትና_በረከት እርሱ #በቸርነቱ_ይክፈለን_አሜን🙏


#ምንጭ
1) ዜና ጳጳሳት ኢትዮጵያውያን (ዲ/ን መርሻ አለሀኝ)
2) ታሪካዊ መዝገበ ሰብ (ፋንታሁን እንግዳ

#ዓውደ_ምህረት_የእናንተ
@AwediMeherit
@AwediMeherit