ገደ? የሚል ጥያቄ ሆኖ እናገኘዋለን) መልሱ ጥያቄው ውስጥ ያለ ነው ጌታው ስለሆነ ለጌታ ደግሞ ስግደት ስለሚገባ ሰገደለት ። “ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።” ማቴ4፥10 ዘጸ 20÷4-5 ይህ አይነቱ ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ የሚገባ ስግደት ነው በስያሜ ደረጃም የአምልኮ ወይም የባህሪ ስግደት በመባል ይታወቃል ። ፈጥረህ የምትገዛ አልፋና ኦሜጋ አንተ ብቻ ነህ ስንል አምላክነት የባሕርይ ገንዘቡ ለሆነ ለእግዚአብሔር ብቻ የምንሰግደው የአምልኮ የስግደት ዐይነት ነው ሁለተኛው ደግሞ ለቅዱሳኑ ሁሉ ይበልጡኑ ለእመቤታች የምንሰግደው የስግደት ዐይነት ሲሆን የጸጋ ወይም የአክብሮት ስግደት በመባል ይጠራል :: በኤልሳቤጥ ሆድ ውስጥ የነበረው የ6ወሩ ጽንስ ቅዱስ ዮሐንስም ይህ ጠንቅቆ የገባው በመሆኑ በእናቱ በኤልሳቤጥ ፊት ለፊት ለቆመችው ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የፀጋ (የአክብሮት)በሆዷ ለጸነሰችው የዕለት ጽንስ ደግሞ እንደ ፈጣሪነቱ የባሕርይ (የአምልኮ)ስግደት አስተባብሮ ሰግዷል ::
🚩*በምንስ አውቆ ? ለሚለው በኤልሳቤጥ የመላባት መንፈስ ቅዱስ ለሆዷ ጽንስ ተርፎላት የ6ወሩ ጽንስ ጌታውና እመቤቱን በሚገባ አውቀ የሚገባውንም ስግደት ሰገደላቸው “በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥” #ሉቃስ 1፥41
የቅዱስ ጴጥሮስ እና የቅዱስ ጳውሎስ የአካል ቅድስናቸው ለልብሶቻቸውና ለጥላቸው ተርፎ ተአምራትን እንዳደረጉ ሁሉ የእናቱ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ለልጆ ተረፈና አዋቂ አደረገው “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።” #ሉቃስ 1፥37 “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።” #ሉቃስ 10፥21
4) የሰው ነጻ ፈቃድ እና የእግዚአብሔር ወሳኝነት እንዴት ይታያል?
ሰው ነጻ ፍቃድ አለው እግዚአብሔር ደግሞ የባህሪ አዋቂነት አለው:: እግዚአብሔር አዋቂ ነው እንጂ ለሰዎች በሰጣቸው ነጻ ፍቃድ ላይ ወሳኝ አይደለም ወሳኙ ሰው ነው ከወሰነማ የሰጠው ነጻ ፍቃድ ነጻ ፍቃድ አይሰኝም ስለዚህ የጥያቄውን መንፈስ ማስተካከል ይገባል ሰው ነጻ ፍቃድ አለው እግዚአብሔር ደግሞ የባሕሪው የሆነ ፍጽም ዕውቀት አለው :: የእግዚአብሔር አዋቂነት በሰው ነጻ ፍቃድ ላይ ተጽኖ ያደርጋል ወይ? ካሉ ግን መልሱ በፍጹም አያደርግም የሚል ይሆናል ። #ለምሳሌ ብዙ ጊዜ ከዚህ ርዕስ ጋር ተያይዞ የሚነሳውን የአስቆሮቱ ይሁዳን ብናነሳ ለይሁዳ እንደዛ መሆን የተነገረበት ትንቢት አስገድዶት እንደሆነ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ ትክክል ግን አይደለም ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ፍቅር በተናገረበት አንቀጹ ፍቅር ከሁሉ እንደሚበልጥ ሲጠቅስ ትንቢት እራሱ ቢሆን ይሻራል የማይሻረው ፍቅር ነው ብሎ የፍቅርን ኃያልነት ሲናገር እናነባለን 1ቆሮ 13 ÷ 2(8) ምን ማለት ነው ትንቢትም ቢሆን እንኳ ስለ ፍቅር ፈንታ ይሻራል ማለቱ ነው ስለዚህ የትንቢት አስገዳጅነት የሚባል ነገር የለም ማለት ነው ይሁዳ ከገንዘብ ፍቅር ይልቅ የክርስቶስ ፍቅር አቃጥሎት ቢሆን ኖሮ ትንቢቱ እራሱ ሊሻርለት ይችል ነበር ነገር ግን ከንዘብ ወዳድ ነበርና ከሚጠፉሁ ገንብ ጋር አብሮ ጠፉ የትንቢቱም መፈጸሚያ ሆነ ። ስለዚህ በአጭሩ የእግዚአብሔር የወደፊቱን የማወቅ ባሕሪው አስገዳጅነት አለው አይባልም::
5 ) እጣፈንታ የሚባል ነገርስ አለ?
አዎን አለ ነገር ግን የዕጣ ፈንታው የምርጫ ካርድ ያለው ሰው ጋር ነው #ለምሳሌ “ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም።” ሐዋ8፥21 ይህ ንግግር ወይም ገጸ ንባብ የሚያስረዳን ዕድል ፈንታና ጽዋ ተርታ የሚባል ነገር እንዳለ ነው የክርስቶስን ፍጽም አምላክነት የመቤታችንን አማላጅነት የቅዱሳኑን ተራዳይነትና ክብር ለሚያምንና ለሚቀበል ሁሉ ጽዋ ተርታው ዕድል ፈንታው ከክርስቶ ጋር ይሆናል ማለት ነው ለዛ ነው የተጠመቅን መሥጋወደሙ የከበርን በቅዱሳኑ ምልጃና ቃል ኪዳን የምንተማመን ሁሉ በክርስቶስ ክርስቲያኖች የተሰኘነው:: ክርስቲያኖች አካል ናቸው ክርስቶስ ደግሞ እራሳቸው ነው::
ዮሐንስ 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።
ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱም፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን? አለው።
ኢየሱስም መልሶ፦ እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፥ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ አለው።
ጴጥሮስም፦ የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም አለው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም፦ካላጠብሁህ፥ከእኔ ጋር #ዕድል_ፈንታ_ጽዋ_ተርታ የለህም ብሎ መለሰለት።
ስምዖን ጴጥሮስም፦ ደንግጡ ጌታ ሆይ፥ እጄንና ራሴን ደግሞ እንጂ እግሬን ብቻ አይደለም አለው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም፦ የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ግን ንጹሕ ነው፤ እናንተም ንጹሐን ናችሁ፥
የመታጠብና ያለ መታጠብ ምርጫ የቅዱስ ጴጥሮስ ነበር በመታጠቡ ሊያገኘው የሚችለውን ነገር መስጠት እና ባለመታጠቡ ሊያጣው የሚችለው መንፈግ የፈጣሪ ድርሻ ነበር :: ዛሬም በጥምቀት የሚገኝ ጸጋ የማግኘት የምርጫ ካርድ በእጃችን ነው ዕጣ ፈንታችንን በክርስቶስ ወይም ከሌላ ወገም የማድረግ መብቱ የኛ ነው እንደ ምርጫችን መስጠት የርሱ ነው ስለዚህ ዕጣ ፍንታ ለሁሉ የተሰጠና የተፈቀደ ሲሆን የፈለጉ ብቻ የሚመርጡት የዕራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ነው ማለት ነው።
#ነገር_ግን_ሁላችሁ_አይደላችሁም አለው። (ይህ ማለቱ ይሁዳን የመሰሉ ከአድያንን ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ የተሰጣቸውን በጥምቀት የተገኘ ልጅነታቸውም በገንዘብ የሚያረክሱ እንዳሉ ሲያመለክት ነው ይህም እግዘብሔርን ፍጽም አዋቂ ነው ያልነውን ያጠነክርልናል ይህ ንግግሩ ለይሁዳ በአሉታዊ መንገድ ተጽኖ አላደረገችም ይልቁኑ ከክፋት ሀሳቡ ተመልሶ በቀና ወደ ማገልገል ልትመልሰው የምትችል የማንቂያ ንግግር ነበረች ይሁዳ ግን አላስተዋለም በገንዘብ ፍቅር ዐይነ ልቡናው ታውሯልና የጌታችን ይህ ዐይነት ምክርና ማንቂያ በዚህ ብቻ የቆመ አልነበረም ምክንያቱም ይሁዳ የትንቢት መፈጸሚያ እንዲሁን ከቶ አይፈቅድም ነበርና በእራት ተቀምጠውም ሳሉ “የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት፤ ያ ሰው ባልተወለደ ይሻለው ነበር " በማለትም የሀሳብ ክእደቱን ወደ ተግባር እንዳያሳድገው እያስተማረው እያስጠነቀቀውም ጭምር ነበር በገንዘብ ፍቅር ተነድፏልና ግና ሊመለስ አልቻለም ሰይጣን ለወዳጁ ድርብ ነው እንዲሉ ይባስ በልቡ ሰይጣን አደረበት። ማር14፥21
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች መዳን የሚሆነውን የድርሻውን ሁሉ ተወጥቷል ከአጥያት መንጫ ጥምቀትን መስርቶ ሥጋውንም ቆርሶ ደሙንም አፍስሶ ሰጥቶናል ከዚህ መዳን ቀርቦ በክርስቶስ ክርስቲያን የመሆንን ዕጣ ፈንታ ጽዋ ተርታን የማግኛ የምርጫ ካርዱ ግን በእጃችን ነው እርሷም ነጻ ፍቃዳችን ናት::
“ማርያምስ ማንም ሊቀማት የማይችለውን መልካሙን ዕድል መረጠች” ሉቃስ 10፥42
ኃ/ማርያም
ጥቅምት 08/2013ዓ,ም
አ.አ ኢትዮጵያ
@YEAWEDIMERITE
ዓውደ ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit