ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
🔥ገብረ አብ💥:
ሰላም ለእርስዎ ይሁን!🙏

ጥያቄ ነበረኝ።

ከማኅፀን የሚመረጡ ቅዱሳን አሉ?
ከማኅፀን የሚመረጡ ኃጥኣንስ?

ቅዱስ ዮሐንስ በማኅፀን ሳለ ለጌታ ለምን ዘለለ?...በምንስ አውቆ?


የሰው ነጻ ፈቃድ እና የእግዚአብሔር ወሳኝነት እንዴት ይታያል?

እጣፈንታ የሚባል ነገርስ አለ?


በመጀመሪያ ስለ ጥያቄዎ እናመሰግናለን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን
በጽሁፍ አመቺ ስላሎነ ወደ ፊት ይህን መሰሉ ጥያቄ በድምጽ የምመልው ይሆናል ..... ለዛሬ ግን

1 ) ከማኅፀን የሚመረጡ ቅዱሳን አሉ?
አዎን በደንብ አሉ #ለምሳሌ እንደነ ማን ቢሉ
በብሉይ ኪዳን
#መስፍኑ_ሶምሶም
“እነሆ ...ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናል ” መሳፍንት13፥5
#ነቢዮ_ኤርምያስ
“በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ”ት.ኤር 1፥5
*በአዲስ ኪዳን
#መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
- “በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤” ሉቃስ 1፥15
-ጻድቁ ተክለ ሃይማኖት ገ/ ተ/ሃይማኖት ወዘተ

2) ከማኅፀን የሚመረጡ ኃጥኣንስ?
ከጅምሩ መመረጥ የሚለው ቃል ለበጎ የሚቀጸል ነው ለክፉሁ ነገር መመረጥ አይባልም መመረጥ የሚባለው ለመልካም ነገር ነው ይህ ዐይነቱ ስህተት አገሌ የተባለው ተጫዋች የእግር መሰበር አደጋ አስተናገደ እንደሚሉ ጋዜጠኖች አይነት ስህተት ነው አስተናገደ ለደጎ ነገር ይናገሩለታል እንጂ ለክፉሁ አይነገርም ተቀብለው የሚያስተናግዱት መልካሙን ጥሩሁን ነር ነውና ። ክፉሁንማ ማን ተቀብሎ ሊያስተናግደው ይፋልጋል??? ማንም ዛሬ ቅልጥሜን ከጥቅም ውጪ ላርገው ብሎ ወደ ሚዳ የሚገባ ተጫዋች የለም ስለዚህ አደጋ ገጠመው ፣ አደጋ ደረሰበት ተብሎ ይነገራል እንጂ አስተናገደ ተብሎ አይነገርም ማስለናገድ የአስተናጋጁን መልካም ፍቃድ የሚጠይቅ ነገር ነው ። በዚህ አንጻር ተመረጠ ወይም ተመረጡ ሲባል ለመልካም ነገር ብቻ ተቀጽሎ ይነገራል እንጂ ለክፉሁ ነገር ተመረጠ፣ ተመረጡ አይባልም ፍጹም ጸያፍ ነው ! ከማኃጸን የተመረጡ ኃጥኃን አሉ ? ለሚለው ጥያቄ የሉም የሚል አጭር መልስ እንሰጣለን ። ዲያቢሎስ ሰልጥኖበት በነበረበት በብሉይ ጊዜ (5500ዘመን ) ላይ ዲያቢሎስ ሊወለዱ የተጸነሱ ጽንሶችን ገና በእናታቸው ማህፀን ሳሉ ይቆራኛቸዋል ሲወለዱም ይጠናወታቸውና ክፉሁ ሥራ ሲያሰራቸው ቆይቶ በኃላ ሲሞቱ ነፍሳቸውን በሲኦል ሥጋቸውንም በመቃብር ይቀራመታቸው ነበር ሌላው ቀርቶ ከማህጸን ጀምሮ የተመረጡ የእግዚአብሔር ሰዎች እንኳ ሲሞቱ ይገቡ የነበሩት ሲኦል ውስጥ ነበር ይህ የሆነበትም ምክንያት በአዳም በደል ምክንያት 5500ዘመን ሙሉ ገነት ተዘግታለ ሲኦል ተከፍታ ሰው ከአምላክ ነፍሥ ከሥጋ ሰማይ ከምድር ተጣልተው የነበረ በመሆኑ ነው። “...ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ ...።” ኢሳ64፥6

#አሁን ግን ያ የመከራ ጊዜ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መሰዋትነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተወግዷል ። ከእንግዲህ ከዲያቢሎስ ቁራኝነት ነጻ ወጥተናል ማንም በማኃፀን ሳለ ያለ ወላጆቹ ክፉሁ ፍቃድና ክፉሁ ምርጫ ካልሆነ በቀር በዲያቢሎስ ቁራኚነት ተይዞ አይወለድም “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤” ቆላስይስ 2፥14

#በነጻነት_ልንኖር_ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።” ገላ5፥1

“በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል።” 2ኛ ጴጥሮስ 2፥20

ከእርኩሳት መናፍስት ጋር ከአጋንንት ጋር በመተባበር ፍቃዳቸውን ለዲያቢሎስ ሰጥተው የዲያቢሎስ የግብር ልጅ የሚሆኑ ሰዎች የሚወልዱ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ :: ቢሆንም ግን የተወለዱት ልጆች ነፍስ ካወቁበት ጊዜ ጀምረው ትክክለኛውን መንገድ መከተልና በክርስቶስ ክርስቲያን የመባል መብትም ፍቃድም ሆነ ችሎታ ሙሉ በሙሉ አላቸው ስለዚህ እኔኮ እንዲ ስለሆንኩ ነው ብሎ በቤተሰቡ የተሳሳተ መንገድ መቀጠል የበለጠ ትልቁ ስሕተት ነው አንድ ጊዜ ከተሰራልን የድኀነት ሥራ በየ ጊዜው የሚነሱ ሰዎች ሁሉ የመሳተፍ የመካፈል ዕድል በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ለሁሉ የተሰጠ ነው ።“ወዳጆች ሆይ፥ #ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።” ይሁዳ 1፥3


3) ቅዱስ ዮሐንስ በማኅፀን ሳለ ለጌታ ለምን ዘለለ?...በምንስ አውቆ?

#ዘለለ የሚለውን አገላለጽ በመጀመሪያ በወጉ ማወቅ ይገባል ። በዚህ አገባባዊ ፍቺ መሠረት ዘለለ የሚለው የድርጊት ገላጭ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰገደ ብላ ትተረጉመዋለች ። ትርጓሜ ሁለት ዐይነት ነው የመጀመሪያው ዘይቤያዊ ትርጓሜ ይባላል ይህም ቃሉ በተነገረበት ሀገር ፣ቋንቋ ፣ባህል ፣ልማድና ትውፊት እንዳሁም የንግግር ዘዬ ተከትሎ ለቃሉ ቀጥተኛ ፍቺ መስጠት ማለት ነው ።
🌷 #ለምሳሌ ፦ዘለለ - ሽቅብ ሽቅብ አለ ፣ ፏነነ፣ ቦረቀ ፣ፈነደቀ፣ተደሰተ የሚል ቀጥተኛ ትርጓሜን ይሰጣል ።#ሁለተኛው የትርጓሜ መንገድ ደግሞ ምሥጢራዊ ትርጓሜ የሚባል ሲሆን ከቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም ባሻገር የቃሉን ምሥጢራዊ (የተሸሸገ፣የተሰወረ ፣ያልታወቀ፣ግልጥ ያልሆነ) ፍቺ የሚገልጥ ከዘይቤያዊው ትርጉም ጋር አንድ ላይ ሊሆድ የሚችልና ፈጽሞም ከዘይቤያዊ ትርጉም ጋር ሊገናኝ በማይችል መልኩ ሊተረጉም የሚችል የአተረጓጓም ዐይነት ነው።
🌷 #ለምሳሌ ፦ዘለለ- በምሥጢራዊው ትርጉሙ ሰገደ፣ አመሰገነ፣ አከበረ ማለት ነው


ለምን መጻሕፍ የዮሐንስን ስግደት ዘለለ ብሎ ገለጠው? ቢሉ

1) መጻሕፍት ምሥጢርን እንጂ ዘይቤን ሰለ ማይጠነቅቁ ነው። ማለትም በምሥጢር ለሚሰጡት መልክትና ትርጉም ይጨነቃሉ እንጂ የቋንቋን የአገላለጽ ዘይቤን በመጠበቅ እረገድ ብዙ አይጨነቁም ለማለት ነው። ይህ የቅዱሳት መጻሕፍት የታወቀ ልማድ ነው።

2) የሕጻናት የደስተኝነት ሁኔታ(ስሜት) ዘለለ ፣ፈነደቀ፣ ቦረቀ፣ በሚሉ የዘይቤ አነጋገር ስለሚገለጹ ሰዎች በሚገባቸው ዐይነት አገላለጽ ለመግለጽ ስለፈለገ ሕጻኑ በደስታ የሰገደውን ስግደት ዘለለ ብሎ ገለጠው ::

3) በማህጸን ያለ ጽንስ ከፍተኛ እንቅስቃሴውን ለመግለጽ ስንፈልግ ጽንሱ ዘለለ እንላለን ። ማህጸን ለጽንሱ መተኛና እግር ለመዘርጊያ ከሚሆን ቦታ የበለጠ ለመዝለያነት የሚሆን ሰፊ ቦታ ኖሮት አይደለም መጠነኛ የሆነ የጽንስ እንቅስቃሴ በራሱ ለእናቲቱ በመዝለል መጠን የሚሰማ ስሜት እንዲሰማት ያደርጋል ። ጌታውንና የጌታውን እናት የተረዳ ዮሐንስእንዴት አብልጦ በደስታ አይዘል ? ኤልሳቤጥም ይህ የልጇ የደስታ ስሜት ተሰማትና "የጌታዬ እናት ወደእኔ ትመጣ ዘንድ ይህ እንዴት ይሆንልኛል የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በደረሰ ጊዜ ጽንሱ በማህጸኔ በደስታ ዘሏል " አለች። ሉቃ 1፥43-44 ስለዚህ ቅዱስ ሉቃስም በእናቲቱ አገላለጽ ጽንሱ በማህጸኟ በደስ ዘለለ ብሎ ሰጊዱን ጻፈልን ሉቃ1÷41

🚩*ለጌታ ለምን ዘለለ ? ( በሌላ አገላለጽ ይህ ጥያቄ ለጌታው ለምን ሰ