ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
እንኳን ለሊቀ መልአክ #ለቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#መዝሙር #ከሚካኤል_በቀር

#በእህታችን #ሜሮን_ደመቀ

#ከሚካኤል_በቀር የሚያጽናናኝ የለም
ረዳቴ እርሱ ነው በመከራዬ ቀን

ሀዘኔ እጅግ በዝቶ ከሚካኤል በቀር
የሚያጽናናኝ ሳይኖር በስደቴ ዘመን
ሰላም ከኔ ርቆ ከሚካኤል በቀር
ጭንቀት አስጠብቦኝ በዙርያዬ ከቦኝ
ዛሬ ግን አጽናኜ ከሚካኤል በቀር
ሚካኤል ደረሰ ጠላት አፈረልኝ
ሚካኤል ነው የዳዊት ረዳት ከጎልያድ ያዳነው
ሚካኤል ነው መንፈሳዊ ብርታት ኃይልንም የሰጠው

ቃልኪዳኑ ግሩም ከሚካኤል በቀር
ዝክሩን ለዘከሩት ስሙንም ለጠሩት
አጋንንት አይቀርቡም ከሚካኤል በቀር
ስዕሉ ካለበት ድርሳኑን ቢደግሙት
በረከት ይገኛል ከሚካኤል በቀር
በእርሱ ሲማጸኑ ከለመኑት በእውነት
ሚካኤል ነው በትረ መስቀል ይዞ የሚጠብቀኝ
ሚካኤል ነው ከአንበሶች መንጋጋ የሚታደገኝ

በኑሮአችን ሁሉ ከሚካኤል በቀር
እርሱ ይረዳናል ፈጥኖ ይደርስልናል
ፈርኦንን ድል ነስቶ ከሚካኤል በቀር
ከግብጽ አውጥቶናል ከንዐን ደርሰናል
የኤርትራን ባሕር ከሚካኤል በቀር
ከፍሎ እንዳሻገረን ከንዐን ገብተናል
ሚካኤል ነው ከበልዐም እርግማን እስራኤልን ያዳነው
ሚካኤል ነው ዛሬም በሐዲስ ኪዳን ክብሩ የገነነው

ክራር #በወንድማችን #አቤኔዘር

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit