ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
እንኳን ለዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት #ደብረ_ዘይት በሠላም አደረሳችሁ
#ደብረ_ታቦር

ደብረ ታቦር ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁለቱ ነቢያትና ለሶስቱ ሐዋርያት ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ታሪካዊ ተራራ ነው።
ጌታችንን መለኮታዊ ታሪክ የሰራባቸው ብዙ ታሪካዊ ተራራዎች አሉ።
ሀ/ ደብረ ሲና
ምሥጢረ ሥጋዌን የገለጠበት የምሥጢር ተራራ ነው
ለ/ ደብረ ቁስቋም
በስደቱ ጊዜ መላእክቱ ክንፋቸውን ዘርግተው ያመሰገኑበት የምስጋና ተራራ ነው።
ሐ/ ደብረ(ገዳመ )ቆሮንቶስ
ሶስቱ ፈተናዎችን እስከፈታኙ ድል ነስቶ አምላክነቱን የገለጠበት የድል ተራራ
ነው።
መ/ ደብረ ዘይት
ለሐዋርያቱ ወደሰማይ ሲያርግ ባርኳቸው ያረገበት የወይራ ተራራ ነው።
ሰ / ደብረ ታቦር
ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት የለመለመ ተራራ ነው።
ወደዚህ ተራራ ከነቢያት ሙሴና ኤልያስን ከሐዋርያት ዮሐንስን ያእቆብን እና
ጴጥሮስን ይዞቸው ወጥቶ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦላቸዋል።
ለምን ከነቢያት ሙሴና ኤልያስን መረጠ ቢሉ?
ነቢዩ ሙሴ በደብረ ሲና መልክህን ማየት እፈልጋለው ብሎ ጠይቆት ነበረና ዛሬ
መልኬን አታይም በሇላ ጀርባየን ታያለህ ብሎት ነበረና ጥያቄውን ለመመለስ
ነው በተራራ የተጠየቀውን በተራራ ለመመለስ ወደተራራው ወስዶታል።
ኤልያስም ተአምር አድራጊ ነቢይ ስለሆነ ጌታችን ታምራቱን አይተው ኤልያስ
ነው ብለውት ነበርና ኤልያስ እንዳልሆነ እና የኤልያስ አምላክ መሆንን
ለማስመስከር ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን አመጣ።
ከሐዋርያት ዮሐንስ ያእቆብ ጴጥሮስ ለምን ይዞ ወጣ ቢሉ?
ጌታችን ወደተራራው ወጥቼ እነግሣለው ባለ ጊዜ የዮሐንስና የያእቆብ እናት
ማርያም ልጆቸን በቀኝና በግራ አንግሥልኝ ብለው ነበረና የጠየቀችውን ጥያቄ
ለመመለስ ያእቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወጥቷል
ጴጥሮስን ለምን ይዞ ወጣ ቢሉ?
ጌታችን ሰዎች ማን ይሉኛል ባለ ጊዜ ?
ጴጥሮስ አንተ የአብ የባህርይ ልጁ ኢየሱስ ነህ ብሎት ነበረና ብርሃነ መለኮቱን
ገልጦ አምላክነቱን ሊያስረደው ወደተራራው ወስዶታል።
ሌሎችን ሐዋርያት ለምን ተዋቸው ቢሉ?
የሐትትዎ ለኀጥእ ከመ ኢይርዓይ
ስብሐተ እግዚአብሔር እንዲል
ኀጢአተኛውን የእግዚአብሔርን ብርሃን እንዳያይ ይከለክሉታል የተባለው ትንቢት
ይፈፀም ዘንድ ይሁዳ ብረሃነ መለኮቱን እንዳያይ ነው።
በሱ ምክንያት ስምንቱም በእግረ ደብር ቀርተዋል ለሶስቱ ሐዋርያት የተገለጠው
ምሥጢር ለስምንቱ ሐዋርያት ተገልጦላቸዋል ።
ይሁዳን ትቶ ሁሉን ይዞ እንዳይወጣ ከምሥጢሩ ቢለየኝ ከሞቱ ገባሁበት
እንዳይል ነው።
ከነቢያት ካገቡትም ካላገቡትም
ከሐዋርያትም ካገቡትም ካላገቡትም ይዞ ወጥቷል።
* ከነቢያት ያገባው ሙሴ
ያላገባው ኤልያስ ነው።
* ከሐዋርያት ያገባው ጴጥሮስ
ያላገቡት ያእቆብና ዮሐንስ ናቸው።
የደናግል የሕጋዉያንም አምላክ እንደሆነ ለመግለፅ ህጋውያንን ደናግላንን ይዞ
ወጥቷል
አንድም ደብረ ታቦር የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት
መንግስተ ሰማያት የህጋውያንም የደናግልም እንደሆነች ለመግለጽ።
አምስት መሆናቸው ስለምን ነው ቢሉ?
ደብረ ታቦር የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት
በቤተ ክርስቲያን የሚቀድሱ ካህናት አምስት እንዲሆኑ ስርዓት ለመስራት ነው
አንድም በአምስቱ አእማደ ምሥጢር ምሳሌ ነው።
ከሞቱት አንስቶ ካሉት ጠርቶ ለህያዋንም ለሙታንም ብርሃነ መለኮቱን
የገለፀው
የሙታንም የህያዋንም አምላክ መሆኑን ለመግለፅ ነው።
ደብረ ታቦር ከዘጠኙ ዓበይት የጌታችን በዓላት አንዱ ነው
ይህ በአል መለኮታዊ አምላካዊ ላእላዊ ሰማያዊ በአል ነው።
ደብረ ታቦር በእስራኤል ውስጥ የሚገኝ የለመለመ ተራራ ሲሆን በአሉ በተራረው
ተሰይሞ ይከበራል
ከሌሎቹ ነቢያት ሙሴና ኤልያስን መርጦ ገልጦላቸዋል ምክንያቱም ሙሴ
ፊትህን ማየት እፈልጋለው ብሎ ሲጠይቀዉ ገፅየሰ ኢያስተርኢ ለከ ወድህረሰ
ትሬኢ ገፅየ ዛሬ ፊቴን አታይም ኋላ ታያለህ ባሎት ነበርና ቃሉን ለመፈፀም
ከመቃብር አምጥቶ ደብረ ታቦር ላይ ገለጠለት
ሙሴ መሆኑ በምን ይታወቃል ቢባል በልቱትነቱ
ሙሴ በቤተ ፈርዖን ሲያድግ የፈርኦንን ግፍ አይቶ ንጉሡ ፈርዖንን በጥፊ ተማቶ
የሞት ፍርድ ቢፈርድበት
የንጉሡ አማካሪዎቹ ልጅ ነው ምን ያውቃል ብለው እሳት እና ፍትፍት ይቅረብለት
እና እሳቱን ትቶ ፍትፍቱን ከበላ ይገደል ክፉና በጎን ያውቃል ፍትፍቱን ትቶ እሳቱን
ከጎረሰ ገና ስላላወቀ አይፈረድበት ብለው ፍትፍትና እሳት አቀረቡለት ፈትፍቱን ትቶ እሳቱን ጎርሶ ነበርና አፉ ተብታባ ነበር በዚህ ታውቋል አንድም ሙሴ ገና
ሲወለድ ከፊቱ ላይ ብርሃን ተስሎበት ተወልዶ ነበርና በዚህ ታውቋል
ኤልያስ መሆኑ በምን ይታወቃል ቢሉ?
በጠጉሩ ኤልያስን ዘፀጓር ብእሲሁ ይለዋልና አንድም ኤልያስ ሲወለድ በእሳት ሰፋድል ተጠቅልሎ ነበር በዚህ ታውቃል ኤልያስን የመረጠበት ምክንያት ኤልያስ ሲያርግ ከኤልሳዕ በቀር ያየው
አልነበረመና በህይወት ማረጉን ለመግለፅ ነው ማቴ17÷1
[ከመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ]

#ቡሔ

የደብረ ታቦር በዓል በኢትዮጵያውያን ዘንድ የቡሄ በዓል በመባል ይጠራል። ቡሄ
ማለት መላጣ [ገላጣ] ማለት ነው።
በሃገራችን ክረምቱ፤ አፈናው ተወግዶ፤ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በዚሁ በዓል
አካባቢ ስለሆነ ቡሄ ያሉት ለዚህ እንደሆነ ይነገራል።
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ህፃናት ይህ በዓል ከመድረሱ በፊት ጅራፍ
ሲገምዱና ሲያጮሁ ይሰነብታሉ፤ እናቶችም ለዚሁ በዓል የሚሆን ዳቦ ለመጋገር
ዝግጅታቸውን ያደርጋሉ።
በዓሉ እንደ ነገ ሊሆን እንደ ዛሬ በዋዜማው ዕለት የሰርፈር ህፃናት በየቤቱ እየዞሩ
ቡሄ ቡሄ እያሉ ይጨፍራሉ። በዚህ ጊዜም እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሱ
ይሰጧቸዋል።
የጅራፉ ማጮህ ተምሳሌቱ የጅራፉ ድምፅ ሲጮህ ማስደንገጡ የሐዋርያትን
[የጴጥሮስን፣ የያዕቆብንና የዮሐንስን] በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውን
ለማስታወስ ነው።
በአንዳንድ አካባቢዎች በቡሄ ዋዜማ ዕለት ችቦ ያበራሉ። ይህም የሚደረገው
በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው ።
የቡሄ እለት ለዘመድ አዝማድ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ በልጆቹ ልክ ዳቦ ይሰጣል።
በተጨማሪም ለክርስትና ልጅ፣ ለጡት ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ የቅርብ እውቂያ
ላለው ሁሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል።
በቆሎ ትምህርት ቤት ደግሞ ደብረ ታቦር የተማሪዎች በዓል ነው። ተማሪዎች
ቀደም አድርገው ስለ "ደብረ ታቦር" እያሉ እህሉን ጌሾውን ብቅሉን ይለምናሉ፣
ህዝቡም ባህሉን ስለሚያውቅ በገፍ ይሠጣቸዋል።
እነዚህም ተማሪዎች የደብረ ታቦር እለት ጠላውን ጠምቀው ቆሎውን ቆልተው፣
ዳቦውን ጋግረው ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን ሁሉ ከቅዳሴ በኋላ
ይጋብዛሉ።

መልካም በዓል
Audio
#መንፈሳዊ ውይይት

#በወንድማችን ብሩክ መልሳቸው እና
#በወንድማችን ተርቢኖስ ሰብስቤ
ይዘት :- #ደብረ ታቦር
👉የት ይገኛል?
👉በእርሱ ምን ምን ነገር ተገለጠ?
👉ለነማ ተገለጠ?
👉የቡሄ ታሪካዊ ድኃራ ምንድነው?
👉እንዴት እናክብረው?
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ነሐሴ 13/2012
" #መስቀለኛዋ አንባ "
ግሸን ማርያም ደብር በወሎ ክፍለ ሀገር በአምባሰል አውራጃ ውስጥ የምትገኝ ደብር ናት፤ ይህች ደብር በሐይቅና በመቅደላ፤በደላንታ፤ በየጁ መካከልና በበሸሎ ወንዝ አዋሳኝ የሆች ስትሆን። በርዋ አንድ ዙሪያውን በገደል የተከከበች አምባ ናት፡፡ በበርዋ ከተገባ በኋላ ግቢዋ ከላይ ሜዳና መስቀለኛ ቦታ ነው፡፡ በትግራይ እንደ ደብረ ዳሞ በበጌምድር እንደዙር አምባ በመንዝ እንደ አፍቅራ ናት ፡፡ ወደዚህች ደብር ለመሔድ በረሐ አቋርጦ በሸሎን በመሻገር ፫ ሰዓት መንገድ አቀበት በመውጣት አንድ ቀን ሙሉ ተጉዞ ማታ ፲፪ ሰዓት ይገባል ፡፡ግሸን ማርያም በፊት #ደብረ_እግዚአብሔር ትባል ነበር ፡፡ ይህ ደብረ እግዚአብሔር የሚለው ስያሜም በጻድቁ ንጉሥ ላሊበላ እጅ ከቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ቤተ መቅደስ #በእግዚአብሔር_አብ ስም ስለነበረ #ደብረ_እግዚአብሔር ተብሎ ተጠራ፡፡ ከዚያም በዓጼ ድግናዣን ዘመን መንግሥት የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ሲመሠረት ሐይቅ ደብር ነጎድጓድ ተብሎ ሲሰየም ግሸን የሐይቅ ግዛት ስለሆነች #ከደብረ_እግዚአብሔር ደብረ ነጎድጓድ ተብላለች ፡፡
ከዚያም በ ፲፬ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ በዓጼ ዘርአ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት የክርስቶስ ግማደ መስቀሉ ግሸን ገብቶ ሲቀመጥ ከደብረ ነጎድጓድ ደብረ ከርቤ ተብላለች የደብሩ አስተዳዳሪም መምህረ እሥራኤል ዘደብረ ከርቤ ይባል ነበር ፡፡ ከደብረ ከርቤ ተመልሳ ግሸን ማርያም ተብላለች፡፡ ይህች ግሽን የተባለች አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረፃት የተዋበች መስቀልኛ ቦታ ነቸና ለግማደ መስቀሉ ማረፊያ ትሆን ዘንድ ተመረጠች ፡፡
በዚያም ዘመን የነበሩት የኢትዮጵያ ጳጳሳት የነበሩት አባ ሚካኤልና አባ ገብርኤል የተባሉ ከንጉሡ ከዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ጋር ሆነው የምህረት ቃል ኪዳን ለመቀበል በዚህች በግሸን ደብር ሱባዔገቡ ። በሱባዔአቸውም በመጨረሻ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾ " ይህች ቦታ እኔ ተወልጄ ያደኩባትን ኢየሩሳሌምን ትሁን፣ የተሰቀልኩባትንም ቀራንዮን ትሁን ፣ የተቀበርኩባትንም ጎልጎታን ትሁን ። በዚች ቦታ እየመጣ የሚማፀነውን ሁሉ ቸርነቴ ትጎበኘዋለች ጠለ ምህረቴንም አይለይባትም ፤ ከሩቅም ሆነ ከቅርብ መጥቶ የተቀበረ ኢየሩሳሌም እንደተቀበረ ይሆንለታል "። የሚል የምህረት ቃል ኪዳን ተገለጸላቸው። ስለዚህም ግሸን ደብረ ከርቤ ዳግሚት ኢየሩሳሌም (ሁለተኛይቱ ኢየሩሳሌም )ተብላ ትጠራለች ። አፄ ዘርያቆብም ከአባታቸው ከአፄ ዳዊት በተቀበሉ አደራ መሠረት በዚያች አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋያተ ቅድሳቱን በየማዕረጋቸው የክብር ቦታ መድበው አስቀመጧቸው ዘመኑም በ፲፬ ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው::

#ምንጭ:- መጻሕፈ ጤፉት፣
ዲ/ን መልአኩ እዘዘው ጽሁፍ

"ሰብ ይቀድስ ለመካን መካን ይቀድስ ለሰብ"
"ሰው ቦታን ይቀድሳል ቦታም ሰውን ይቀድሳል"
#መስከረም ፩ ፭/ ፳ ፻-፩ ፫ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
#ዓውደ_ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)

#ብርሃን_ዘኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ብጡል
_____________________________
« #ብርሃን_ዘ_ኢትዮጵያ » በሚል ቅፅል ስም የታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብ ዳር ነሐሴ ፲ ፪ ቀን ፲ ፰ ፻ ፴ ፪ ዓ/ም በጌምድር ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ።
በ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በተወለዱ በ ፹ ቀናቸው ጥቅምት ፳ ፯ ቀን ፲ ፰ ፻ ፴ ፫ ዓ/ም በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሡ።

#በልጅነት ዘመናቸው በዚሁ ደብር ውስጥ ዳዊትን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ በጊዜው ይሰጡ የነበሩትን ሌሎች የሃይማኖት ትምህርቶች በየታላላቁ አድባራት በመዘዋወር ያጠናቀቁ ስለመሆናቸው ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ። የተማሩባቸውም መፃሕፍት ተጽፈው ይገኙ የነበረበትን የግዕዝ
ቋንቋ አጣርተው ያውቁ ነበር። እናታቸው ወይዘሮ የውብዳር ከባለቤታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም ከሞቱ በኋላ በጅሮንድ መዩ የተባሉትን የ ዓፄ ቴዎድሮስን ባለሟል አግብተው ነበር። እሳቸውም ጣይቱ ብጡል ትምህርት እንዲቀስሙ ለማድረግ ልዩ መምህር ቀጥረውላቸው እንደነበር ይታወቃል።
#እቴጌ_ጣይቱ በማኅደረ ማርያም ሆነው ሲማሩና መፃሕፍትን ይቀጽሉ በነበሩበት ጊዜ ለቤተክርስቲያን መጋረጃ መሥሪያ በትርፍ ጊዜያቸው ፈትል እየፈተሉ ያቀርቡ ነበር። በ በገና ቅኝትና ድርደራም በኩል የታወቁ ባለሙያ እንደነበሩ ይተረክላቸዋል።

ከ ንጉሥ ምኒልክ ጋር ጋብቻ እንደመሠረቱ
________________________
#የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በሸዋ የዓፄ ቴዎድሮስ እንደራሴ ከነበሩት አቶ በዛብህ ጋር ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፰፻፶፯ ዓ/ም በጋዲሎ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ድል አድርገው ወደ አንኮበር ገብተው በ ነሐሴ ፳፬ ቀን ነገሡ። በነገሡም በአሥራ ሁለት ዓመታቸው የፋሲካ ን በዓል በ ባሕር ዳር አቅራቢያ ሱሉልታ ላይ ዋሉና ደብረ መይ በጣይቱ ብጡል እናት በወይዘሮ የውብዳር ቤት ከጣይቱ ብጡል ጋር ተጫጭተው ስለጋብቻቸው ተነጋገሩ። ከዚያም ዋና ከተማቸው ወደነበረችው ደብረ ብርሃን ተመልሰው መጡ።
ከተጫጩ ከሁለት ዓመት በኋላ ወይዘሮ ጣይቱን ለማስመጣት በቤተ መንግሥቱ በተደረገው ምክር መሠረት አለቃ ተክለማርያም ወልደ ሚካኤል ደብዳቤ ተሰጥቷቸው ተላኩ። በዚያም አስፈላጊው ሁሉ በተፋጠነ ሁኔታ ተሟልቶ በ ጐጃም በኩል ደንገጡሮችና አሽከሮች አስከትለው ጉዞውን ጀመሩ።

#ደብረ_ብርሃንም በገቡ ጊዜ ንጉሡ /ምኒልክ/ ታላቅ አቀባበል አደረጉላቸው። ከዚያም ጣይቱ ወንድማቸው ራስ ወሌ ብጡል ዘንድ ለጥቂት ዓመታት ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የጋብቻቸው ስነ-ሥርዓት የ ፋሲካ ዕለት ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፸፭ ዓ/ም በ አንኮበር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ተጋቡ።

አፈወርቅ ገብረ ጊዮርጊስ “ዳግማዊ አጤ ምኒልክ” በተባለው መጽሐፋቸው ገጽ ፴ ፱-- ፵ ፩ ላይ “ከልዢነት ጀምረው ሲመኟት እንደ ህልም ሲአልሟት ትኖር የነብረችው ጣይቱ ብጡል በ ፲፰፻፸፭ ዓ/ም ደብረ ብርሃን ገባች ንግሥተ ሸዋ ሆነች ወዲያው የፋሲካ ለት አንኮበር መድኃኔ ዓለም ቆርበው ሁለቱ ተጋቡ። … ፀሐይቱ ለማለት ጣይቱ ተባለች ነገር ግን ከጣይቱ እጣይቱ ለመባል ይገባታል።” [2] ይላሉ

« #ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» ተብለው ዘውድ ስለ መጫናቸው
_________________________
ንጉሡ «አፄ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ» የሚለውን ስም በተቀዳጁ በማግሥቱ ጥቅምት ፳ ፯ ቀን ፲ ፰ ፻ ፹ ፪ አ/ም ወይዘሮ ጣይቱ ብጡል እቴጌ ተብለው ተሰየሙ።

#የሥርዓተ ዘውዱ አፈፃፀም በከፍተኛ መሰናዶ የተጠናቀቀ በመሆኑ እጅግ ደማቅ እንደነበር ከተፃፉ ፅሁፎች ለማወቅ ይቻላል። እቴጌ ጣይቱም ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ከንጉሠ ነገሥቱ እጅ የተቀበሉትን ዘውድ ደፉላቸው።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በታወቁበት «እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ» በሚል የክብር ስም ማኅተም ተቀረፀላቸው። እነዚሁ ታሪካዊ ሂደቶች እቴጌይቱን በኢትዮጵያ ዱኛዊ፣ ወታደራዊና ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ ከፍተኛና ብሩህ ሚና ለመጫወት የቻሉ አድረገዋቸዋል።
#እንኳን_ለአባታችን_የፍልሰተ_አጽሙ_በዓል_በሰላም_አደረሰን 🙏
#ከደብረ_አስቦ (አሰቦት) ወደ #ደብረ_ሊባኖስ

#ኢትዮጵያዊው_ኤልሳዕ
በአጽሙ ሙት ያስነሳ
፪ኛ ነገሥት ፲ ፫÷፳ -፳ ፩
ገ/ተ ሃይማኖት ም/፶ ፫
አጥንት በመጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌነት ሲጠቀስ ሦስት ነገሮችን ያመለክታል።
፩ የሰው ኃይልን ያመላክታል መዝ ፶ ፫፥፭ ኢሳ፴ ፰፥፲ ፫
፪ የቅርብ ዝምድና መግለጫ ሆኖ ቀርቧል ዘፍ ፳ ፱÷፲ ፬ ሳሙ ፱÷፪
፫ የሞተ ሰውን ክብር ያስረዳል ዘፍ ፶÷፳ ፭ ዕብ ፲ ፩÷፳ ፪
# ይበልጡኑ_የቅዱሳን_ሰዎች ሞት /አጥንት (አጽም)/ እጅግ የከበረ ነው ። መዝ ፻ ፲ ፭ (፻
፲ ፮) ÷፲ ፭ ለአብነትም ተቀብሮ የነበረው የኤልሳዕ አጥንት /አጽም/ ሌላ የሞተ ሰው ከሞት እንዳስነሳ መመልከት በቂ ነው። ከሞዓብም አደጋ ጣዮች በየዓመቱ ወደ አገሩ ይገቡ ነበር።ሰዎችም አንድ ሰው ሲቀብሩ አደጋ ጣዮችን አዩ፥ ሬሳውንም በኤልሳዕ መቃብር ጣሉት፤ የኤልሳዕንም አጥንት በነካ ጊዜ ሰውዮው ድኖ በእግሩ ቆመ። ፪ኛ ነገሥት ፲ ፫÷፳ - ፳ ፩
በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊው ኤልሳዕ ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖትም የሥጋ ድካም ከትጋቱ እንዳያስታጉለው በስምንት ሰለታም ጦር እራሱን ከቦ ከደብረ አስቦ ዋሻ ከቆመ ሳይቀመጥ
ከዘረጋ ሳያጥፍ ፳ ፪ ዓመት ሲጋደል ሳለ ከመቆም ብዛት አንዲቷ የእግሩ አገዳ ተሰበረችና ከሰውነቱ ተለይታ ወደቀች።

# ደቀ_መዛሙርቱም እንደ ማንም መስሏቸው ስባረ እግሩን ከመቃብር ሥፍራ ወረወሯት የኤልሳዕን አጽም ሲነካው ከሞት ድኖ እንደተነሳው ሰው የአባታችን የእግራቸው አጥንት
የነካው በመቃብሩ ሥፍራ ተቀብሮ የነበረ አንድ ሰው አፈፍ ብሎ ድኖ በእግሩ ቆመ ። ገ/ተ ሃይማኖት ፶ ፫
የአባታችንንም ስባረ አጽም (ስባረ እግር) እያመሰገነ ሰላምታ ሰጠ " ይህን ያዮ ደቀ
መዛሙርቶቻቸውም የጻድቁ ስባረ አጽም ገባሬ ተአምራት መሆኗን አውቀው ከመንበሩ እግር በታች አክብረው በሰበን ጠቅልለው ቀብረዋታል:: " #የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል። እግዚአብሔር
አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥ ከእነርሱም አንድ አይሰበርም። " መዝ ፴ ፫{፴ ፬}÷፲ ፱-፳

ይህ የቅዱሳን አጥንት (አጽም) #እግዚአብሔር የማይለየውና ሌት ተቀን የሚጠብቀው ነውና ቅዱሳን ጻድቃን ካረፉበት ሄዶ መሳለም በረከትን ያሰጣል ከሥጋም ከነፍስም ህመም አድኖ በጤና ያቆማልና የአጽማቸውን በዓል ማክበር እጅግ የሚገባ ነው ::

ቅዱስ ጳውሎስ በልብሱ ጨርቅ " (ሐዋ፲ ፱÷፲ ፩-፲ ፪) ቅዱስ ጴጥሮስ በሰውነቱ ጥላ ድውያንን ሁሉ ይፈውሳቸው ነበር ። ( ሐዋ ፭÷፲ ፭ ) ቅዱሳን የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው፣ የሥጋቸው ቅድስና ለለበሱት ልብስና ለአካላቸው ጥላ ተርፎ ድንቅ ተአምራትን የሚሰራ ከሆነ እግዚአብሔር የሚጠብቀው አጽማቸውማ እንዴት አብልጦ ድንቆችን አይሰራ?!:: #አጥንት_ለሰዉ ልጅ ተክለ ሰውነት ወሳኝ ድርሻ አለው። ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች
መካከል የተወሰኑት ብንዳስስ፤ ለሰዉነታችን ቅርፅ ለመስጠት፣ የሰዉነት የውስጥ አካላት (Organs) ከአደጋ ለመከላከል #ለምሳሌ ደረት የሚያርፍበት ክፍለ አጥንት ለሳንባና
ለልብ ከለላ(covering) ይሰጣል፤ የራስ ቅል አጥንት አንጎል ምንም አይነት ጉዳት
እንዳይገጥመው ጠንካራ ልባስ ሆኖ ይከላከላል ፣ ሥጋና ጡነቻዎቻችንን አጣብቆ ለመያዝና የካልስየም ንጥረ ነገርን ለማጠራቀም ይረዳል፡፡

ክቡር የሆነ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖትም ለቀናች ሃይማኖቱ አጥንት ነው። አጥንት የሌለው አካል ጤፍ እንደሌለው ማዳበሪያ መቆም አይቻለሁም:: ሀገሪቱና ቤተክርስቲያኒቱ ዶግማ ቀኖናና ትውፊቷን ይዛ ቅርጻን ሳትለቅ ቀጥ ብላ እንድትቆም አድርጓታልና።

#ምዕመኗ ልዮ ልዮ በሆነ በእግዳ ትምህርት ከበረትቷ እንዳይኮበልሉ ኖላዊ ትጉሁ ሆኖ በጾም በጸሎቱ የሀገር ዋልታ በመሆንም አካል ለምትባል ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደ አጥንት ጋሻ፣ መከታ፣ ጥላ ፣ከለላ ሆነላት። የሃይማኖት ማነስ የምግባር ጉድለት እንዳያጋጥማትም በቃሉ ትምህር በእጁ ተአምራት በበረከቱ ሞላት፤ በረድኤቱ ጋረዳት እንደ አጥንት የሃይማኖት መፍሰሻ ነቅ የወንጌል መፍለቂያ ምንጭም አደረጋት።

ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ጥር ፳ ፬\፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም # ለስባረ አጽሙ ከጻፍኩት በከፊል የተወሰደ::