#ደብረ_ታቦር
ደብረ ታቦር ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁለቱ ነቢያትና ለሶስቱ ሐዋርያት ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ታሪካዊ ተራራ ነው።
ጌታችንን መለኮታዊ ታሪክ የሰራባቸው ብዙ ታሪካዊ ተራራዎች አሉ።
ሀ/ ደብረ ሲና
ምሥጢረ ሥጋዌን የገለጠበት የምሥጢር ተራራ ነው
ለ/ ደብረ ቁስቋም
በስደቱ ጊዜ መላእክቱ ክንፋቸውን ዘርግተው ያመሰገኑበት የምስጋና ተራራ ነው።
ሐ/ ደብረ(ገዳመ )ቆሮንቶስ
ሶስቱ ፈተናዎችን እስከፈታኙ ድል ነስቶ አምላክነቱን የገለጠበት የድል ተራራ
ነው።
መ/ ደብረ ዘይት
ለሐዋርያቱ ወደሰማይ ሲያርግ ባርኳቸው ያረገበት የወይራ ተራራ ነው።
ሰ / ደብረ ታቦር
ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት የለመለመ ተራራ ነው።
ወደዚህ ተራራ ከነቢያት ሙሴና ኤልያስን ከሐዋርያት ዮሐንስን ያእቆብን እና
ጴጥሮስን ይዞቸው ወጥቶ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦላቸዋል።
ለምን ከነቢያት ሙሴና ኤልያስን መረጠ ቢሉ?
ነቢዩ ሙሴ በደብረ ሲና መልክህን ማየት እፈልጋለው ብሎ ጠይቆት ነበረና ዛሬ
መልኬን አታይም በሇላ ጀርባየን ታያለህ ብሎት ነበረና ጥያቄውን ለመመለስ
ነው በተራራ የተጠየቀውን በተራራ ለመመለስ ወደተራራው ወስዶታል።
ኤልያስም ተአምር አድራጊ ነቢይ ስለሆነ ጌታችን ታምራቱን አይተው ኤልያስ
ነው ብለውት ነበርና ኤልያስ እንዳልሆነ እና የኤልያስ አምላክ መሆንን
ለማስመስከር ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን አመጣ።
ከሐዋርያት ዮሐንስ ያእቆብ ጴጥሮስ ለምን ይዞ ወጣ ቢሉ?
ጌታችን ወደተራራው ወጥቼ እነግሣለው ባለ ጊዜ የዮሐንስና የያእቆብ እናት
ማርያም ልጆቸን በቀኝና በግራ አንግሥልኝ ብለው ነበረና የጠየቀችውን ጥያቄ
ለመመለስ ያእቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወጥቷል
ጴጥሮስን ለምን ይዞ ወጣ ቢሉ?
ጌታችን ሰዎች ማን ይሉኛል ባለ ጊዜ ?
ጴጥሮስ አንተ የአብ የባህርይ ልጁ ኢየሱስ ነህ ብሎት ነበረና ብርሃነ መለኮቱን
ገልጦ አምላክነቱን ሊያስረደው ወደተራራው ወስዶታል።
ሌሎችን ሐዋርያት ለምን ተዋቸው ቢሉ?
የሐትትዎ ለኀጥእ ከመ ኢይርዓይ
ስብሐተ እግዚአብሔር እንዲል
ኀጢአተኛውን የእግዚአብሔርን ብርሃን እንዳያይ ይከለክሉታል የተባለው ትንቢት
ይፈፀም ዘንድ ይሁዳ ብረሃነ መለኮቱን እንዳያይ ነው።
በሱ ምክንያት ስምንቱም በእግረ ደብር ቀርተዋል ለሶስቱ ሐዋርያት የተገለጠው
ምሥጢር ለስምንቱ ሐዋርያት ተገልጦላቸዋል ።
ይሁዳን ትቶ ሁሉን ይዞ እንዳይወጣ ከምሥጢሩ ቢለየኝ ከሞቱ ገባሁበት
እንዳይል ነው።
ከነቢያት ካገቡትም ካላገቡትም
ከሐዋርያትም ካገቡትም ካላገቡትም ይዞ ወጥቷል።
* ከነቢያት ያገባው ሙሴ
ያላገባው ኤልያስ ነው።
* ከሐዋርያት ያገባው ጴጥሮስ
ያላገቡት ያእቆብና ዮሐንስ ናቸው።
የደናግል የሕጋዉያንም አምላክ እንደሆነ ለመግለፅ ህጋውያንን ደናግላንን ይዞ
ወጥቷል
አንድም ደብረ ታቦር የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት
መንግስተ ሰማያት የህጋውያንም የደናግልም እንደሆነች ለመግለጽ።
አምስት መሆናቸው ስለምን ነው ቢሉ?
ደብረ ታቦር የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት
በቤተ ክርስቲያን የሚቀድሱ ካህናት አምስት እንዲሆኑ ስርዓት ለመስራት ነው
አንድም በአምስቱ አእማደ ምሥጢር ምሳሌ ነው።
ከሞቱት አንስቶ ካሉት ጠርቶ ለህያዋንም ለሙታንም ብርሃነ መለኮቱን
የገለፀው
የሙታንም የህያዋንም አምላክ መሆኑን ለመግለፅ ነው።
ደብረ ታቦር ከዘጠኙ ዓበይት የጌታችን በዓላት አንዱ ነው
ይህ በአል መለኮታዊ አምላካዊ ላእላዊ ሰማያዊ በአል ነው።
ደብረ ታቦር በእስራኤል ውስጥ የሚገኝ የለመለመ ተራራ ሲሆን በአሉ በተራረው
ተሰይሞ ይከበራል
ከሌሎቹ ነቢያት ሙሴና ኤልያስን መርጦ ገልጦላቸዋል ምክንያቱም ሙሴ
ፊትህን ማየት እፈልጋለው ብሎ ሲጠይቀዉ ገፅየሰ ኢያስተርኢ ለከ ወድህረሰ
ትሬኢ ገፅየ ዛሬ ፊቴን አታይም ኋላ ታያለህ ባሎት ነበርና ቃሉን ለመፈፀም
ከመቃብር አምጥቶ ደብረ ታቦር ላይ ገለጠለት
ሙሴ መሆኑ በምን ይታወቃል ቢባል በልቱትነቱ
ሙሴ በቤተ ፈርዖን ሲያድግ የፈርኦንን ግፍ አይቶ ንጉሡ ፈርዖንን በጥፊ ተማቶ
የሞት ፍርድ ቢፈርድበት
የንጉሡ አማካሪዎቹ ልጅ ነው ምን ያውቃል ብለው እሳት እና ፍትፍት ይቅረብለት
እና እሳቱን ትቶ ፍትፍቱን ከበላ ይገደል ክፉና በጎን ያውቃል ፍትፍቱን ትቶ እሳቱን
ከጎረሰ ገና ስላላወቀ አይፈረድበት ብለው ፍትፍትና እሳት አቀረቡለት ፈትፍቱን ትቶ እሳቱን ጎርሶ ነበርና አፉ ተብታባ ነበር በዚህ ታውቋል አንድም ሙሴ ገና
ሲወለድ ከፊቱ ላይ ብርሃን ተስሎበት ተወልዶ ነበርና በዚህ ታውቋል
ኤልያስ መሆኑ በምን ይታወቃል ቢሉ?
በጠጉሩ ኤልያስን ዘፀጓር ብእሲሁ ይለዋልና አንድም ኤልያስ ሲወለድ በእሳት ሰፋድል ተጠቅልሎ ነበር በዚህ ታውቃል ኤልያስን የመረጠበት ምክንያት ኤልያስ ሲያርግ ከኤልሳዕ በቀር ያየው
አልነበረመና በህይወት ማረጉን ለመግለፅ ነው ማቴ17÷1
[ከመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ]
#ቡሔ
የደብረ ታቦር በዓል በኢትዮጵያውያን ዘንድ የቡሄ በዓል በመባል ይጠራል። ቡሄ
ማለት መላጣ [ገላጣ] ማለት ነው።
በሃገራችን ክረምቱ፤ አፈናው ተወግዶ፤ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በዚሁ በዓል
አካባቢ ስለሆነ ቡሄ ያሉት ለዚህ እንደሆነ ይነገራል።
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ህፃናት ይህ በዓል ከመድረሱ በፊት ጅራፍ
ሲገምዱና ሲያጮሁ ይሰነብታሉ፤ እናቶችም ለዚሁ በዓል የሚሆን ዳቦ ለመጋገር
ዝግጅታቸውን ያደርጋሉ።
በዓሉ እንደ ነገ ሊሆን እንደ ዛሬ በዋዜማው ዕለት የሰርፈር ህፃናት በየቤቱ እየዞሩ
ቡሄ ቡሄ እያሉ ይጨፍራሉ። በዚህ ጊዜም እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሱ
ይሰጧቸዋል።
የጅራፉ ማጮህ ተምሳሌቱ የጅራፉ ድምፅ ሲጮህ ማስደንገጡ የሐዋርያትን
[የጴጥሮስን፣ የያዕቆብንና የዮሐንስን] በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውን
ለማስታወስ ነው።
በአንዳንድ አካባቢዎች በቡሄ ዋዜማ ዕለት ችቦ ያበራሉ። ይህም የሚደረገው
በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው ።
የቡሄ እለት ለዘመድ አዝማድ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ በልጆቹ ልክ ዳቦ ይሰጣል።
በተጨማሪም ለክርስትና ልጅ፣ ለጡት ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ የቅርብ እውቂያ
ላለው ሁሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል።
በቆሎ ትምህርት ቤት ደግሞ ደብረ ታቦር የተማሪዎች በዓል ነው። ተማሪዎች
ቀደም አድርገው ስለ "ደብረ ታቦር" እያሉ እህሉን ጌሾውን ብቅሉን ይለምናሉ፣
ህዝቡም ባህሉን ስለሚያውቅ በገፍ ይሠጣቸዋል።
እነዚህም ተማሪዎች የደብረ ታቦር እለት ጠላውን ጠምቀው ቆሎውን ቆልተው፣
ዳቦውን ጋግረው ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን ሁሉ ከቅዳሴ በኋላ
ይጋብዛሉ።
መልካም በዓል