አፄ ሶምሶም
እንደ ደሊላ ለወደዷት ሀገራቸው ዐይናቸውን ሰጥተው በዓይናማነት ላቆዮት ሶምሶሞች ዛሬም ምሥጋና ይገባቸዋል ::
ሶምሶም ከተወለደ ጀምሮ በእራሱ ላይ ምላጭ አርፎበት የማያውቅ የእግዚአብሔር ኃይል በጸጉሩ ላይ ያደረበት እስራኤላውያንን ይጠብቁ ዘንድ ከተነሱ መሳፍንት መካከል ኃያሉ ናዝራዊ ሰው ነበር :: እንደ ነፍሱ የሚወዳት ደሊላ ግን ይህ ከሰው ሁሉ ልዮ የሚያደርግህ የኃይል ምሥጢር ምንድን ነው ? ከወደድከኝ ንገረኝ እያለች ዕለት ዕለት ትነዘንዘው ነበር ። መጻሕፍ ቅዱስ እንደውም ይህን ንዝነዛዋን እንዲ ሲል ይገልጠዋል “ዕለት ዕለትም በቃልዋ ነዘነዘችው አስቸገረችውም፥ ነፍሱም እስከ ሞት ድረስ ተጨነቀች”መሳ 16፥16
ኢትዮጵያዊው ሶምሶም ዳግማዊው አፄ ቴዎድሮስም ልክ እንደ ሶምሶም የእራስ ጸጉራቸውን ምላጭ ያልነካው ለኢትዮጵያ የተለዮ (ናዝራዊ) ጎንደራዊ ነበሩ :: ኢትዮጵያዊያንን ከድህነት ቀንበር ለማውጣት ከተላኩ የኢትዮጲያ አንድነት ጠንሳሽ ነገሥታት መካከልም በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሱ የኢትዮጵያ አንድነት አባት እየተባሉ የሚጠሩ አንዳርጌ ናቸው :: ውልደታቸው ከጎንደር ከተማ 12 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው " ደዋ " በምትባለው ሥፍራ ነው ዓመተ ምህረቱም 1811 ነበር ።
አባታቸው አቶ ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ ሲባሉ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ አትጠገብ ወንደሰን ይባላሉ ምንም እንኳን አባታቸው የባለ አባትነት ዘር ያላቸው ቢሆኑም እናታቸው ግን በድህነት ምክንያት ኮሶ ይሸጡ እንደነበር ልዮ ልዮ የታሪክ ፀአህፍት ይጠቅሳሉ :: ለምሳሌ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፣ ጳውሎስ ኞኞ፣ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን...ወዘተ
ቢሆንም ግን አፄ ቴዎድሮስ" በእናት እና በሀገር አይታፈርም" ሲሉ ከባለ አባት ዘር ከተከኙት ከአባታቸው ከአቶ ኃይሉ ይልቅ " የኮሶ ሻጭ ልጅ " እየተባሉ በኮሶ ሻጭ እናታቸው ስም ያለ እፍረት መጠራትን መረጡ :: ዛሬ ዛሬ አፄ ቴዎድሮስ በግፍ ይህን አደረጉ አፄ ምኒልክ የሴት እንትን ቆረጡ እያሉ አፄዎቹን ሲያብጠረጥሩ ሳይ የእውነት ይከፋኛል :: በኮሶ ሻጭ እናቱ የተጠራው ቴዎድሮስ እምዬም እየተባሉ የሚጠሩት ምኒልክ እናቶችና ሴቶች ላይ ይህ የመሰለ ድርጊት አደረጉ ብሎ ማውራት ከታሪክ መጎደል ነው ::
ሶምሶም ከደሊላ ምሥጢር ከሚያስወጣ ጥያቄዋ ለማምለጥ የራሱን ጥረት አድርጓል:: በእርጥብ ጠፈር ብታስሪኝ፣ በአዲስ ገመድም ብትቋጥሪኝ፣ የእራስ ፀጉሬን በችንካር ብትቸነክሪው ኃይሌ ከእኔ ይጠፋል እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ እያለ ምሥጢርም ሳያወጣ ደሊላንም ሳያጣ እስከ ጊዜው ለመቆየት ችሎ ነበር :: “ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት።” ምሳሌ 12፥4 እንዲል መጻሕፍ
አፄ ቴዎድሮስም ከእንግሊዞች ጋር ችግር ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋቸው ሀገራቸውን ወደ ሥልጣኔ ማማ ለማውጣ ካላቸው ከፍተኛ ጉጉት ነበር:: አማቻቸው ደጃች ውቤን ድል ካደረጉ በኃላ የካቲት ወር 1847ዓ.ም አፄ ቴዎድሮስ ተብለው በደረስጌ ማርያም ቤተ ክርስቲያን በይፋ ነገሱ ወዳጆቼ ናቸው ከሚሏቸው ሩሲያ እና እንግሊዝ ጋርም ስለ መድፍ ሥራ መጻጻፍ ጀመሩ::
እንግሊዝ ሆዬ አሻፈረኝ ስትል የአፄውን ጥሪ በእንቢታ መለሰች ይኸኔ ሥልጣኔና ትምህርት ሳይሆን ስንዴ ለምነው ቢሆን ኖሮ እሺታቸውን ባልነፈጓቸው ነበር አፄው ግን ከአንድ አፍሪካዊ መሪ የማይጠበቅ ጥያቄ ጠየቁ ስለዚህ እንቢ ተባሉ። አፄውም ደመ ፍሉ ነበሩና በሀገር ውስጥ ያሉ እንግሊዞችን በወይኒ አጎረው ዘጉባቸው ። በጋፋትም ታሳሪዎቹን መድፍ እንዲሰሩ አስገደዷቸው እኛ ወንጌላዊያን ነን ስለ መድፍ ሥራ አናውቅም አሉ መድፍ መሥራት ካላወቃችሁበት እኔም አላውቅላችሁም ሲሉ አፄው ቆራጥ ውሳኔያቸውን ቢያሳውቋቸው ወንጌላዊ ተብዬ ሆይ የመድፉን ሥራ አጣደፉሁት ወንጌልና መስቀል ይዘው የነበሩ እጆች ብረትና ባሩድ ጨበጡ:: በዚህ ተደፈርኩ ያለችሁ እንግሊዝም በውስጥ ከፋፍሎ ለመግዛት በተዘጋጁ መሳፍንት ውጥረት ግብ ድብ ውስጥ የገቡትን ቴዎድሮስ ከውጭ ሆና ለማጥቃት ምቹ ጊዜ ያገኘች መስሏት 32 ሺህ ጦር አስከትላ መጣች እጅ እንዲሰጡም አፄውን ጠየቀች አፄ ቴዎድሮስም ይህን ሲስሙ ከት ብለው ስቀው ሲያበቁ "ሀገሬን እንኳን ለነጭ ቀኝ ገዢ ለጥቁሩም ከፋፋይ የምሰጥ አይደለውም በዓለማየሁም ቢሆን ለዚህ አማላጅ የለኝም ደግሞ እጅህን ስጥ በክብር እንዝሃለን ይሉኛል? እጄ የእሳት አሎሎ መሆኑን አያውቅም!? ወትሮንስ የት ሀገር ነው ጠላት በክብር የሚያዘው!?
ንዝነዛዋ የበዛበት ሶምሶም የልቡን ሁሉ ገለጠላት የኃይሉ ምንጭ ጸጉሩ እንደሆነና ጸጎሩን ቢላጭ ኃይሉ ከእርሱ እደሚርቅ ነገራት ደሊላም የልቡን ሁሉ እንደገለጠላት ባየች ጊዜ በጕልበትዋ ላይ አስተኛችው በተኛበትም፤ አንድ ሰውም ጠራች፥ እርሱም ሰባቱን የራሱን ጕንጕን (ቁንድላ) ላጨው። ልታዋርደውም ጀመረች፥ ኃይሉም ከእርሱ ሄደ።” ከተኛበት ቀስቅሳም ሶምሶም ሆይ ፍልስጤማውያን መጡብህ አለችው ተነስቼ እንደ ቀድሞ እሆናለው ቢል ኃይል ከእርሱ እርቆልና አንዱን በጡጫ ሌላውን በርግጫ ማለት ተሳነው:: ሶምሶምም ለምርኮ ተዳረገ ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዓይኖቹን አወጡት፤ ወደ ጋዛም አምጥተው በናስ ሰንሰለት አሰሩት፤ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር። መ.መሳፍ 16፥21
ከውስጥ እና ከውጭ ጠላቶቻቸው ጥርስ ውስጥ የገቡት ቴዎድሮስ ለነጭ ቀኝ ገዢና ለጥቁር ከፋፋይ አሳልፌ አልሰጥም ብለው ከታማኝ ወታደሮቻቸው ጋር ያሰሩትን ሴቫስቶፎል መድፍ ይዘው ወደ መቅደላ ገሰገሱ በዚያም የጠላት ጦር ገፍቶ በመምጣቱ ከአራቱም መዓዘን በአንድነት የሰበሰቧቸውን ሽፍቶች እንደ ቀድሞ በአራቱም መዓዘን ተበትነው ለጠላት የማይጨበጩ ይሆኑ ዘንድ አሰማርተው ለጠላት እጅ ሳይሰጡ በነገሱ 13 ዓመት በተወለዱ ደግሞ በ49ዓመታቸው 1860ዓ.ም በሚያዚያወር በገዛ እጃቸው እራሳቸውን ሰውተው የጀግና ሞት ሞቱ::
አልደፈር ብሎ እራሱን ገደለ
ጀግና ሰው ሰውቶ ካሳ መች ከፈለ
በመቅደላ በኩል ጮኸት በረከተ
የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሰው ሞተ
........................
አያችሁት በያ የጀግናሁን ሞት
በሰው እጅ መሞትን ነውር አድርጎት
ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው
ማረክንም እንዳይሉ ሰው የለ በጃቸው
ምን አሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው
ለወሬ አይመቹም ተንኮለኛ ናቸው
.
በትውልድ ስማቸው ካሳ ኃይሉ በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ በውትድርና ስማቸው ደግሞ መይሳው ካሳ እየተባሉ የሚጠሩት ኢትዮጵያው ሶምሶም ዳግማዊው አፄ ቴዎድሮስም እንደ ደሊላ ለወደዷት ሀገራቸው ዋጋ ከፍለዋል በፍቅሯ ጭኖች ተይዘው መቅደላ አምባ ላይ ተኝተዋል ለማዕተባቸው አድረዋል:: በግብር ፍልስጤማዊያን በሚባሉ እንግሊዛዊያን የእራስ ጸጉራቸው ቁንድላ ከእራሳቸው ላይ እንደ በግ ከነቆዳቸው ተገፏል አስክሬናቸውም በግፍ ተደብድቧል :: ደሊላ በሶምሶም ተጠቅማለች ሶምሶም ግን ከደሊላ ያተረፈው ሞት ብቻ ነው
#የግርጌ_ማስታወሻ :- እንግሊዞች ገፈው ወስደውት የነበረው የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዱላ (የተጎነጎነ የእራስ ፀጉር፣ ሹሩባ ) በአንድ ድርድር በቅርቡ ወደ ሀገር ተመልሷል::
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ነሐሴ ፳ ፰ - ፳ ፻ ፲፪ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም

Forwarded from ዐውደ ምሕረት (ተርቢኖስ ሰብስቤ)
ሰላም እንደምን አመሻችሁ ጥያቄዎቻችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ማቅረብ ትችላላችሁ!
ለጥያቄዎቻችሁ
👇👇👇👇👇
@Abenma
@YEAWEDIMERITE
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ለጥያቄዎቻችሁ
👇👇👇👇👇
@Abenma
@YEAWEDIMERITE
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ማኅደር, [06/09/2020, 00:07]
ንስሐ ሳይገቡ ጠበል መጠመቅ ይቻላል ?
1ኛ ሳሙ 7:12 αβεпεζεя, [06/09/2020, 00:25]
ጥምቀት በቤተክርስቲያናችን ብዙ ዓይነት ሲሆን ለአብነትም የልጅነት ጥምቀት ማትደገመው ከመንፈስ ቅዱስ የምንወለድበት፣ የቄደር ጥምቀት ሰው ከክህደት ሲመለስ ሚጠመቀው ፣ ከሥጋ ደዌ ለመዳን የምንጠመቀው ጥምቀት (ከተለያዩ በሽታዎችና ከእርኵስ መንፈስ ለመፈወስ) ፣ ኑሮአችን እንዲቃና ያሰብነው እንዲሳካ ዋጋ በረከት ለማግኘት ምንጠመቀው ጥምቀት እና የንስሐ ጥምቀት ይጠቀሳሉ። የንስሐ ጥምቀት ሚባለው ልክ ዮሐንስ መጥምቅ ሲያጠምቅ ህዝቡም ሲጠመቁት የነበረው ዓይነት ጥምቀት ማለት ነው። ኃጢአትን ለካህን ተናዞ ንስሐ ገብቶ ቀኖና ተቀብለው ሚጠመቁት ጥምቀት ነው። “ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።” ማቴዎስ 3፥6 እንዲል መጽሐፉ ምንጠመቀው የጥምቀት ዓይነት የንስሐ ጥምቀት ከሆነ ንስሐ ገብተን ብንጠመቅ ይመረጣል። አዲሱን አመት በአዲስ መንፈስ ከኃጢአት ርቀን በበረከት ተጎብኝተን እንድንጀምርና ዓመቱን የሰላም የጤና የደስታና የስኬት እንዲሆንልን ብለን ብንጠመቅ ምንም ሚያመጣው ችግር የለም። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የመዳን ቀን አሁን ነው ይላልና ንስሐ ገብተን ብንጠመቅ የተሻለ ነው።ማር16÷16 "ያመነ የተጠመቀ ይድናል" ማመን ምሥጢረ ክህነትንም የሚጠቀልል ነው እግዚአብሔር ለቅዱሳን ካህናት የሰጠውን የመፍታት የማሰር ሥልጣን እሺ በጄ ብሎ መቀበልም የእምነት ዋና አስኳል ነገር በመሆኑ ወደ ንስሐ አባት ሳይቀርቡ መጠመቅ ከዚህ ደገኛ ሥርዓት መጉደል ነው::“የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።”ማቴ 16፥19“ኢየሱስም፦ ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ፥ ነገር ግን ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፥ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ሙሴ ያዘዘውን መባ አቅርብ አለው።”ማቴ8፥4
አዘጋጅ:-አቤኔዘር ማሙሸት
👇👇👇👇

#የዛሬው ባለታሪክ #ግያዝ ይባላል።
የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ነበረ፤ ደግሞም ጽኑዕ ኃያል ነበረ፥ ነገር ግን ለምጻም ነበረ። ከሶርያውያንም አገር አደጋ ጣዮች ወጥተው ነበር፥ ከእስራኤልም ምድር ታናሽ ብላቴና ሴት ማርከው ነበር፤ የንዕማንንም ሚስት ታገለግል ነበር። እመቤትዋንም፦ ጌታዬ በሰማርያ ካለው ከነቢዩ ፊት ቢደርስ ኖሮ ከለምጹ በፈወሰው ነበር አለቻት። ንዕማንም ገብቶ ለጌታው፦ ከእስራኤል አገር የሆነች አንዲት ብላቴና እንዲህና እንዲህ ብላለች ብሎ ነገረው። የሶርያም ንጉሥ ንዕማንን፦ ሂድ፥ ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እልካለሁ አለው። እርሱም ሄደ፥ አሥርም መክሊት ብር፥ ስድስት ሺህም ወርቅ፥ አሥርም መለውጫ ልብስ በእጁ ወሰደ። ለእስራኤልም ንጉሥ፦ ይህች ደብዳቤ ወደ አንተ ስትደርስ ባሪያዬን ንዕማንን ከለምጹ ትፈውሰው ዘንድ እንደ ሰደድሁልህ እወቅ የሚል ደብዳቤ ወሰደ። የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ፦ ሰውን ከለምጹ እፈውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስደዱ እኔ በውኑ ለመግደልና ለማዳን የምችል አምላክ ሆኜ ነውን? ተመልከቱ፥ የጠብ ምክንያትም እንደሚፈልግብኝ እዩ አለ። የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን እንደ ቀደደ በሰማ ጊዜ፦ ልብስህን ለምን ቀደድህ? ወደ እኔ ይምጣ፥ በእስራኤልም ዘንድ ነቢይ እንዳለ ያውቃል ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ። ንዕማንም በፈረሱና በሰረገላው መጣ፥ በኤልሳዕም ቤት ደጃፍ ውጭ ቆመ። ኤልሳዕም፦ ሂድ፥ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ታጠብ ሥጋህም ይፈወሳል፥ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ። ንዕማን ግን ተቈጥቶ ሄደ፥ እንዲህም አለ፦ እነሆ፥ ወደ እኔ የሚመጣ፥ ቆሞም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፥ የለምጹንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር። የደማስቆ ወንዞች አባናና ፋርፋ ከእስራኤል ውኆች ሁሉ አይሻሉምን? በእነርሱስ ውስጥ መታጠብና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን? ዘወርም ብሎ ተቈጥቶ ሄደ። ባሪያዎቹም ቀርበው፦ አባት ሆይ፥ ነቢዩ ታላቅ ነገርስ እንኳ ቢነግርህ ኖሮ ባደረግኸው ነበር ይልቁንስ፦ ታጠብና ንጹሕ ሁን ቢልህ እንዴት ነዋ! ብለው ተናገሩት። ወረደም፥ የእግዚአብሔርም ሰው እንደ ተናገረው በዮርዳኖስ ሰባት ጊዜ ብቅ ጥልቅ አለ ሥጋውም እንደ ገና እንደ ትንሽ ብላቴና ሥጋ ሆኖ ተመለሰ፥ ንጹሕም ሆነ። እርሱም ከጭፍራው ሁሉ ጋር ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመለሰ፥ ወጥቶም በፊቱ ቆመና፦ እነሆ፥ ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ አሁንም ከባሪያህ በረከት ትቀበል ዘንድ እለምንሃለሁ አለ። እርሱም፦ በፊቱ የቆምሁት ሕያው እግዚአብሔርን! አልቀበልም አለ። ይቀበለውም ዘንድ ግድ አለው፤ እርሱ ግን እንቢ አለ። ንዕማንም፦ እኔ ባሪያህ ከእንግዲህ ወዲህ ከእግዚአብሔር በቀር ለሌሎች አማልክት የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት አላቀርብምና ሁለት የበቅሎ ጭነት አፈር እንድወስድ እሺ ትለኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።እግዚአብሔርም ለእኔ ለባሪያህ በዚህ ነገር ብቻ ይቅር ይበለኝ፤ ጌታዬ በዚያ ይሰግድ ዘንድ እጄን ተደግፎ ወደ ሬሞን ቤት በገባ ጊዜ፥ እኔም በሬሞን ቤት በሰገድሁ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በዚህ ነገር ለእኔ ለባሪያህ ይቅር ይበለኝ አለ። እርሱም፦ በደኅና ሂድ አለው። አንድ አግድመትም ያህል ከእርሱ ራቀ።
የእግዚአብሔርም ሰው ሎሌ ግያዝ፦ ጌታዬ ሶርያዊውን ይህን ንዕማንን ማረው፥ ካመጣለትም ነገር ምንም አልተቀበለም፤ ሕያው እግዚአብሔርን! በስተ ኋለው እሮጣለሁ፥ ከእርሱም አንዳች እወስዳለሁ አለ።ግያዝም ንዕማንን ተከተለው፤ ንዕማንም ወደ እርሱ ሲሮጥ ባየው ጊዜ ሊገናኘው ከሰረገላው ወርዶ፦ ሁሉ ደኅና ነውን? አለው። እርሱም፦ ደኅና ነው። አሁን ከነቢያት ወገን የሆኑት ሁለት ጕልማሶች ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ወደ እኔ መጥተዋል፤ አንድ መክሊት ብርና ሁለት መለወጫ ልብስ ትሰጣቸው ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ጌታዬ ላከኝ አለ። ንዕማንም፦ ሁለት መክሊት ትወስድ ዘንድ ይፈቀድልህ አለ፤ ግድ አለውም፤ ሁለቱንም መክሊት ብር በሁለት ከረጢት ውስጥ አሰረና ከሁለት መለወጫ ልብስ ጋር ለሁለት ሎሌዎቹ አስያዘ፤ እነርሱም ተሸክመው በፊቱ ሄዱ።ወደ ኮረብታውም በመጣ ጊዜ ከእጃቸው ወስዶ በቤቱ ውስጥ አኖራቸው፤ ሰዎቹንም አሰናበተ፥ እነርሱም ሄዱ። እርሱ ግን ገብቶ በጌታው ፊት ቆመ፤ ኤልሳዕም፦ ግያዝ ሆይ፥ ከወዴት መጣህ? አለው። እርሱም፦ እኔ ባሪያህ ወዴትም አልሄድሁም አለ። እርሱም፦ ያ ሰው ከሰረገላው ወርዶ ሊቀበልህ በተመለሰ ጊዜ ልቤ ከአንተ ጋር አልሄደምን? ብሩንና ልብሱን፥ የወይራውንና የወይኑን ቦታ፥ በጎችንና በሬዎችን፥ ወንዶችንና ሴቶችን ባሪያዎች ትቀበል ዘንድ ይህ ጊዜው ነውን?
እንግዲህስ የንዕማን ለምጽ በአንተ ላይ፥ ለዘላለምም በዘርህ ላይ ይጣበቃል አለው። እንደ በረዶም ለምጻም ሆኖ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።
#ግያዝን ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?
👉በገንዘብ ፍቅር ቢነደፉ?
👉 የዚህ ዓለም ሀብትና ነዋይ ቢያጓጓዎ?
👉 የገንዘቡ ምንጭ ምንም ካልተጎዳ ምን አለበት እኔ ብጠቀምበት የሚል ሀሳብ ቢፈታተኖት? ምን ያደርጋሉ?
👉 #ግያዝስ ስሕተቱን ከሰራ በኃላ ወደፊት ምን ያድርግ?
#ግያዝ ምክሮቻችሁን ዛሬም እየጠበቀ ነው
👇👇👇👇👇👇👇
@Abenma
@YEAWEDIMERITE
#ዓውደ_ምህረት የእናንተ

Forwarded from Girum machinary and Generator spare parts
betam kebad nw genzb yeatyate ser mnce nw
Forwarded from Nebiyu
ከባድ ነው ግን በኤልሳ ስም ከመቀበል ለራሴ የጎደለብኛ የሚያስፈልገኛ ነገር አለ ብሎ እንዲመፀውተው ቢለምነው መልካም ነበር።
Forwarded from Girum machinary and Generator spare parts
ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፥ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ፥ ከሃይማኖት ተሳስተው በብዙ ሥቃይ ራሳቸውን ወጉ።
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6 : 10
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6 : 10
Forwarded from ኢትዮጲያ ናት ሀገሬ ተዋህዶ ናት ክብሬ ኢትዮጲያ ለዘለአለም ትኖር ጠላቶችዋ ይደምሰሱ አሜን
ሰለ ትምህርቱ በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህራችን እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመን እግዚአብሔር ይባረክልን እድሜ ጸጋ ያድልል አወደ ምህርት ቻናል አገልጋዮች ሁላችሁም
ከዚህ ታረክ ላይ በጣም የምደነቀው ቤት ወሰጥ የነበረች አገልጋይ ነው የንዕማን መዳን ምክንያት የሆነችው አሁንም በእውነት በሰደት አለም ብዙ እህቶቻችን በሚሰሩበት ቦታ የታመሙ ሰዎች ሲኖሩ ወደ ኢትዮጵያ ሄዱ ልጆቻቹ ይድናሉ ሲልዋቸው በእምነታቸው እስልምና ሰለ ሆኑ ይፈራሉ ብዙ አረቦች ኢትዮጵያ መጥተው የታመሙ በሽተኞችን እንዲፈውሱ ልያደረጎ ይፈልጋሉ በእስልምና ከእስልምና ወጭ ይትም መሄድ አትችልም በዚህ የተነሳ እየወደዱ የሚተው አሉ
አንድ እህቴ የነገረችን ነገር አለ እሱም የምትሰራበት ቤት ልጁ አፈ ዲዳ ነበርና ከኢትዮጵያ የወሰደችው እምነት ቀብታ እንደ ተፈወሰ ነገረችኝ ብዙ እህቶች እንዲህ ያደረጎ አሉ በእውነት
የንዕማን ለምጸ የመዳን ምክንያት የሆነችው ልጅ ምሳሌ ነች ለእነዚህ እህቶቻችን
ወደ ጠየቃቹት ጥያቄ ሲሄድ
እኔ ብሆነ ነብዩ መሆኑ ካመንኩ ነብዩን ጠይቄ ገንዘብ ለምን አንቀበልም አንተ ባትፈልገው ለሚፈልገው ይሰጥ እል ነበር እንጅ ነብይ ሳልጠይቅ አልቀበልም ነበር ወይም ነብይ የፈቀደው እሱ በፈወሰው እኔ ለምን እቀበላለሁ እል ነበር እንጅ ገንዘቡ ወረቁም አልወሰድም ነበር
ወሰጅ ቢሆነ ኖሩ እንኳን ነብይ መጥቶ ሲገሰጸኝ ይቅርታ ጠይቅ እመልሰለት ነበር ይቅርታ ጠይቁ እንቢ የሚል ይለም ነብይም እንቢ አይልም እግዚአብሔር እንቢ አይልም

...ጷጒሜን በጥቂቱ...
ጷጒሜ ሥርወ ቃሉ "ኤጳግሚኖስ" ከሚለው የግሪክ ቃል የወጣ ሲሆን "ተጨማሪ" የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን እንደ አዋጅ ጾም ያይደለ እንደ ፈቃድ ጾም አስቀምጣልን በጾም በጸሎት በሱባኤ እናስባታለን ሀገራችን ኢትዮጵያም 13ኛ ወር አድርጋ ትቆጥራታለች ለዚህም ነው የ13 ወር ፀጋ ተብላ የምትሞገሰው። ይህች በዕድሜዎ ከሌሎቹ አስራ ሁለት ወራት ብታንስም እኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የእግዚአብሔር ገንዘቦች ልዮ አድርገን እናስባታለን ልዮ ምስጢር ይዛለችና የእግዚአብሔር መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዚህ በአራት ዓመት አንዴ ስድስት በስድስት መቶ ዓመት አንዴ ደግሞ ሰባት በምትሆነው በጷጒሜ ወር የምድር ውሆችን የውሃ አካላትን በሙሉ ይባርካቸዋል ቤተሳይዳ የነበረውን ውሃ መልአኩ እንዳናወጠው (እንደባርከው) ሁሉ ...ይህንም በሙሉ እምነት አምኖ የተጠመቀ ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ ይፈወሳል ሕጻናትንም ያሳድጋል ፤ በተለምዶም የእግዚአብሔር መድኃኒት ተብሎ የሚጠራው የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ሲመቱ በሚውልበት በጷጒሜ 3 ዕለት በሚዘንበው ጠበል ሕጻናት " ሩፋኤል አሳድገኝ " እያሉ ይጠመቃሉ አዋቂውም እንደዛው ይጠመቃል ጠበሉንም በማስቀመጫ እቃ እያስቀመጥን ቤታችንን ከጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ ክፉ ሴራ እንጠበቃለን እናቶቻችንም ጠበሉን የእንጀራ ሊጥ ውስጥ እየጨመሩ ምግበ ሥጋ ወነፍስ የሆነ እንጀራ ጋግረው ይመግቡናል። ይህን ጾም እየጾምን ፈዋሽ ጠበሉን እየተጠመቅን ወርዋን ካገባደድን መጪው አዲስ ዓመት የበረከት ፣ የረድኤት ፣ የፍቅር እና የሰላም ይሆንልናል ያድርግልንም! መልካም በዓል!!
አዘጋጅ፦ባሮክ ዘ ደብረ አሚን
ቀን 3/13/2012
አ.አ ኢትዮጵያ
#ዓውደ ምህረት የእናንተ

#ጷጉሜ የተባለችው ወር ከየት መጣች?
______ (በአለቃ ዕፁብ ማናዬ)____________
ብዙዎቻችን ስለ ዓመት ስንናገርና ለልጆቻችን ስናስተምር አንድ ዓመት 365 ¼ ቀንት፣ 52 ሳምንታት እና 12 ወራት በማለት እንናገራለል፡፡ እውነትም ልክ ነው፤ ነገር ግን 365 ¼ ማለት ምን ማለት ነው? ¼ የሚባል ቀን አለን? 12 ወራት በሠላሳ በሠላሳ ቀናት የተከፋፈሉ ሆነው ድምራቸው 12X30 = 360 ነው፡፡ ታዲያ 5ቀናት እና ¼ የተባለው ከየት መጣ? ጷጉሜስ የተባለችው ወርስ ከየት መጣች? ለሚባሉትን ጥያቄዎች አስተዋዮች ይጠይቃሉ፡፡ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ግን እንደሚከተለው ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ አስቀምጠውልናል፡፡(ይህ መልስ ብዛት ካላቸው የብራና ጽሑፎች ተውጣቶ ቀለል ባለ ዘዴ የቀረበ ነው፡፡) ይህ ትምህርት የሚገኘው አቡሻኽር በተባለው የቤተክርስቲያን ትምህርት ነው ፡፡ ትምህርቱ ሰፊ ነው፡፡ አብዛኛውም የሒሳብ ስሌት ያለበትም ነው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ወደተነሳንበት ስንመለስ ስንት ወቅቶች አሉን ከተባለ አራት ናቸው፡፡ እነሱም
#1 ክረምት(ከሰኔ26 መስከረም25)፣
#2 መፀው/መከር(ከመስከረም26- ታኅሣሥ25)፣ #3 በጋ/ሐጋይ (ከታኅሣሥ26 - መጋቢት25)፣
#4 ጸደይ/በልግ(ከመጋቢት26 - ሰኔ25) ነው፡፡ እያንዳንዱ ወቅት ደግሞ ሦስት ወራትን ይዟል፡፡ 3X30=90 ነው፡፡ 90 ሲባዛ በ4 ደግሞ 360 ነው፡፡ እንግዲህ የስሌቱ ነገር የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው፡፡
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ከላይ አንድ ወቅት 90 ቀን ሳይሆን 91 ቀን 7ሰዓት እና 30 ደቂቃ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው የየወሩ ቀን ማጠር እና መርዘምን ተከትሎ በሚመጣ ልዩነት ነው፡፡ #ለምሳሌ
መስከረም ላይ 12 ሰዓት አይመሽም ብርሃን ነው፡፡
ታኅሣሥ ላይ ግን 12 ሰዓት ጭልምልም ይላል፡፡ ሌሊቱም ረዥም ነው፡፡ ለምሳሌ እነዚህ ቀረቡ እንጂ እያንዳንዱ ወር የተለያየ ልዩነት አለው፡፡ ስለዚህ ጠቅላላውን አራቱንም ወቅቶች ስንደምራቸው የምናገኘው ውጤት አንድ ዓመትን ያስገኙልናል፡፡
🚩ክረምት 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
🚩መፀው 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
🚩በጋ/ሐጋይ 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
🚩ጸደይ 91 ቀን 7 ሰዓት ከ30 ደቂቃ
::::::::::::::::::::::::::
ጠቅለል አድርገን ስንደምረው ዘጠና ዘጠናው ቀን ስንደምረው 90 X 4 = 360 ይሆናል፡፡ ይህ የአሥራሁለት ወሩን ያዘ ማለት ነው፡፡ የየወቅቱን አንዳንድ ቀን ስንደምር 1 X 4 = 4 ይሆናል፡፡ ይህም የጷጉሜ አራቱ ቀናት ናቸው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የቀሩትን 7 ሰዓት እና 30 ደቂቃዎች ስንደምራቸው 30ሰዓት ይመጣል፡፡ ወደ ዕለት ሲቀየር 1 ቀን እና 6 ሰዓት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከላይ ካገኘነው 4 ጋር ሲደመር 5 ቀናት እና 6 ሰዓት ይሆናል ማለት ነው፡፡
#በጠቅላላ አንድ ዓመት 365 ከ6ሰዓት ወይም ¼የሚባለው ለዚህ ነው ይህ ስድስት ሰዓት በአራት ዓመት አንድቀን ሆኖ ጷጉሜ ስድስት እንድትሆን ያደርገዋል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ጳጉሜ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ጭማሪ” ማለት ነው ፡፡ በግእዝ “ወሰከ – ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ተውሳክ (ተጨማሪ) ማለት ነው፡፡ ምዕራባዊያኑ ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ቀን አድርገዋታል፡፡ እኛ ግን የዓመት ተጨማሪ ወር አድርገናታል፡፡ ይህቺ ወር በ600 ዓመት 7 ትሆናለች ነገር ግን ሊቃውንት ይቺን የትርፍ ትርፍ ናትና ከስሌት ውጪ የማይኖርባት በማለት ይገልጧታል፡፡
#ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ጷጉሜ ፫/፳ ፻- ፲፪ ዓ.ም