ዐውደ ምሕረት
3.66K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
የማክሰኞ ዕለት እርሻ
🌲🌳🌴🌱🌿

"ዘር ያልተዘራብሽ እርሻ አንቺ ነሽ "
ሶሪያዊው ቅዱስ ኤፍሬም
ውዳሴ ማርያም ዘሰሉስ
በሥነ ፍጥረት ትምህርት በእጅ የሚለቀሙ በማጭድ የሚታጨዱ በምሳር የሚቆረጡ በሥራቸው ፣በግንዳቸው፣ በቅርንጫፋቸው የሚያፈሩ ልዮ ልዮ አትክርት ፣አዝርዕት በጠቅላላው የእጽዋት ዘሮች የተፈጠሩት በዕለተ ማክሰኞ ነው:: በግዕዙ ዕለተ ሰሉስ ይለዋል በልማዱ ማክሰኞ በትክክለኛው አጠራር ግን ማግስተ ሰኞ ነው የሚባለው የሰኞ ማግስ ማለቱ ነው::

የሰሉስ ወይም የማግስተ ሰኞ (የማክሰኞ) ዕለት ፍጡራን ከላይ የተዘረዘሩት የእጽዋት ዘሮች ሲሆኑ ነገር ግን ለመገኘታቸው ምክንያት የሚሆናቸው የዘራቸው ያጠጣቸው ያበቀላቸው ገበሬ አልነበረም ። አስገኚያቸው ፈጣሪያቸው ልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው በዚህም የማክሰኞ ዕለት እርሻ ከሌሎቹ አርሻና የእርሻ ምርቶች ለየት ይላል ። ከማክሰኞ ዕለት እርሻ በቀር ዘር ሳይዘራበት ገበሬ ሳይተክልበት አድጎ ለምልሞ የታየ የእርሻ ዓይነት የለምና ። እግዚአብሔር አምላክ ሥነ ፍጥረቱን በሦስት መንገድ ፈጥሯል ይህውም በሐልዮ ወይም (በማሰብ) ሁለተኛ በነቢብ ወይም (በመናገር) ሦስተኛ በገቢር ወይም (በተግባር ፣በሥራ ፣በመሥራት) ነው። ታድያ የዕለተ ማክሰኞ ፍጥረታት በነቢብ የተፈጠሩ ፍጥረታት ናቸው ። እግዚአብሔርም፦ ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድርም ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል አለ፤ እንዲሁም ሆነ ። ምድርም ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን እንደ ወገኑ ዘሩም ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን እንደ ወገኑ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደ ሆነ አየ። ዘፍ 1÷11-12

ይህች የዕለተ ማክሰኞ እርሻ የመጀመሪያይቱ ምድርም እየተባለችም ትጠራለች ። ገበሬ ሳይተክላት ዝናብ ለዘር ጠል ለመከር ሳታገኝ በመብቀሏ ቅድመ ምድር የመጀመሪያይቱ ምድር ተባለች :: የሚገርመው በዚህ ወቅት የብርሃናት ምንጮች ፀሐይ ጨረቃና ከዋክብት ገና አልተፈጠሩም ነበር ዝናብም በምድር ላይ ዘንቦ አያውቅም ነበር። ፀሐይ ጨረቃና ከዋክብት የተፈጠሩት በዕለተ ዕረቡ ነው ስለዚህ በመጀመሪያይቱ ምድር ለማክሰኞ እርሻ መገኘት አስተዋጽዖ አላደረጉም ያለ ውኃ ያለ ፀሐይ በቅለው ለምልመው ተገኙ እንጂ። አቡሹ ሳይንስ እጽዋት ያለ ውኃ እና ያለ ፀሐይ መብቀል እንደሚችሉ ገና አልደረሰበትም ምን አልባት ወደፊት ድሆ ድሆ ሲደርስበት እንደ ለመደው አዲስ ግኝት ብሎ በየ ሚዲያው ሠላማችንን መንሳቱ እና ከሃይማኖት ዕውቀት በላይ ነኝ በማለት ቤተ ክርስቲያንን መጨቆኑና ኃላ ቀር አድርጎ መቁጠሩ አይቀርም ። ቤተ ክርስቲያን ግን ባሕረ ጥበባት ነች አትመረመርም:: ያለ ውኃ አብቅላ ያለ ፀሐይም አብስላ ልጆቾን ከርሃበ ሥጋ ከርሃበ ነፍስ ታሳርፋቸዋለች ለምሳሌ ቢሉ ቃለ እግዚአብሔሯ አንዱና ዋናው ማሳያ ነው ማለት እንችላለን ። ቃለ እግዚአብሔር ያለ ዝናብ እና ያለ ፀሐይ የሚያለመልም የሥጋም የነፍስም ምግብ ነው “እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።” ማቴ 4፥4

በምሥጢር "ጥንተ ምድር " ወይም ይህች የመጀመሪያይቱ ምድር (የማክሰኞ እርሻ) የምትባል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነች:: በዚህም እመቤታችን ጥንተ ምድር የማክሰኖ እርሻ ተብላ ትጠራለች። ጥንተ ምድር ያለ ዘር ያለ ገበሬ ያለ ዝናብ ያለ ፀሐይ በግብረ መንፈስ ቅዱስ (በመንፈስ ቅዱስ ሥራ) ለምልማ አፍርታ እንደተገኘች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ገበሬ የሚባል ወንድ ዘር የሚባል ዘርኃ ብዕሲ ሳይጎበኛት እንዲሁ በግብረ መንፈስ ቅዱስ (በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ) ፀንሳ አብባ ተገኝታለች ። ይህ ምሥጢር በእውነት ድንቅ ነው መላከ እግዚአብሔር ለእራሷ ለድንግል ማርያም ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ የልዑል ኃይል ይጋርድሻል መንፈስ ቅዱስም ይጸልልብሻል ትጸንሻለሽ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ ሲላት እንዴት ይህ ይሆናል ሴት ያለ ወንድ ምድር ያለ ዘር ልታፈራ ይቻላታልን አለችሁ ? መላኩም ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም ጥንተ ምድርን ያለዘር ሳራን ያለ ሙቀት ልምላሜ ዘመድሽ ኤልሳቤጥን በስተ እርጅናዋ ያጸነሰ አንቺንም ያለ ወንድ ዘር ማጸነስ አይሳነውም አላት ያን ጊዜ እውነት ነው ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም "ይኩነኒ በከመ ትቤለነ " አለችሁ በዚሁ ቅጽበትም ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በማህጸኟ ተቀረጸ። ቅዱስ ጳውሎስም ይህ ያለ ዘር የመጽነስን ምሥጢር ይህ ምሥጢር ያለ ጥርጥር ድንቅ ነው ሲል ግሩም አርጎ ገልጦታል::“እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።” ሲል 1ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16 ። ሶርያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም በማክሰኞ ዕለት ውዳሴው የማክሰኞን እርሻ የምትባል መቤታችንን "ዘር ያልተዘራብሽ እርሻ አንቺ ነሽ " ብሎ በግሩም አመስግኘቀታል እርሻ እርሻ ለመባል ዘር ሊዘራበት ያስፈልገዋል እመቤታችን ግን ዘር ያልተዘራባት ግን አፍርታ የተገኘች እርሻ ነችና ዘር ልተዘራብሽ እርሻ አንቺ ነሽ አላት ያለ መታረስ ማፍራት ያለ ሰስኖተ ድንግልና መጸነስ ድንግል ሲሆኑ እናት እናትም ሲሆኑ ድንግል የመሆን ፀጋ ከሰው ልጆች መካከል ከድንግል በስተቀር ለመን ተሰጠ? ለማንም። ሆ ድንግል ሆይ አንቲ መንክረ መንክራት።

 ቅዱስ ዳዊት “ምድር ፍሬዋን ሰጠችእግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል”(መዝ.66፥6)
ተብሎ እግዚአብሔር የሚመሰገንበት ሳምንት ነው፡፡ ፍሬውም ከቁር ከበረዶና ከትል ተርፎ ለጎተራ እንዲበቃ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጸሎተ ቅዳሴዋ “በእንተ ፍሬ ምድር ናስተበቊእ ከመ እግዚአብሔር ይሁብ ፍሬሃ ለምድር፣ ለዘርና ለመከር ሊሆን እግዚአብሔር ለምድር ፍሬዋን ይሰጣት ዘንድ ስለምድር ፍሬ እንማልዳለን” በማለት አምላኳን ትማጸናለች፡፡

ልጇቿ ምእመናንም “ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ” (ማቴ. 24፥20) ሲል መድኃኔዓለም እንዳስተመረው የሃይማኖት ፍሬ ምግባርን፣ ቱሩፋትን ሳይሠሩ በልምላሜ (በሃይማኖት) ብቻ ሳሉ እንዳይጠሩ ለንስሐ ለሥጋ ወደሙ እንዲበቁ በማስተማር ነገረ ምጽአቱን በማዘከር “ድልዋኒክሙ ንበሩ፣ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ ” በማለት ታስተምራለች፡፡ ስለዚህ ይህ ክፍለ ክረምት የዕለተ ምጽአት ምሳሌ ነው፡፡ ወቅቱ የአዝመራ ወቅት ነው፡፡ ፍሬ መለያ እንደሆነ ሁሉ የሰው ሥጋ ከተቀበረና ትቢያ ከሆነ በኋላ ተነስቶ በዕለተ ምጽአት በጽድቅና በኃጢአት ይለያልና፡፡(ማቴ.25፥32)

“በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች።” ማቴዎስ 21፥19 ሰው በሃይማኖቱ ቀጥተኛ እውነተኛ ከሆነ አይፈረድበትም በምግባሩ ግን ይኮነናል ሃይማኖት ቅጠል ምግባር ፍሬ ነች:: “ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።” ያዕቆብ 2፥26 “አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።” ማቴዎስ 3፥10
ቅዱስ ጳውሎስም ክርስቲያኖች በሃይማኖት ሲኖሩ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬን እንዲያፈሩ ምግባራትን እንዲያደርጉ
" የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። ሲል ማፍራት ብቻ ሳይሆን ምን ዓይነት ፍሬም ማፍራት እንደሚገባ ዘርዝሮ ነግሮናል ገላ5÷22 አስቀድሞ በኢሳይያስ ነቢይ ላይም አድሮ " እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ እንቢ ብትሉ ብታምጹ ግን ሰይፍ ይበላችዋል " ብሎ እሺ ብለን ታዘን የምድርን በረከት እንድንበላ አስቦናል ኢሳ 1÷19 ወላዲ መጥቅ ዮሐንስም በምስክርነቱ “መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።” ማቴዎስ 3፥12 ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ዋግ እንዳልመታው ውርጭም እንዳላገኘው ንጽሕ ስንዴን ያቀረበ የአቤልን መሰዋይት ያሳረገች እኛንም ንጽሕ ስንዴ አድርጋ ጎተራ በተባለች መንግስተ ሰማያት እንድንገባ የማክሰኞ እርሻ የእመቤታችን በረከት ይደርብን:: አሜን🙏.....ይቆየን......

@YEAWEDIMERITE
አዘጋጅ :- ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
ሐምሌ 21 ቀን 2012ዓ,ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

#ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ጥቁር እንግዳ

ሀገራችን እያጋጠሟት ካሉ ተደራራቢ ችግሮች መካከል የአንበጣ መንጋ ወረሽኝ አንዱ ችግር ነው :: ኢትዮጵያ እርሻ ለማረስ እህል ለማብቀል ዘር ለማምረት የተመቸ መልከዓ ምድራዊ ስጦታ የተሰጣት ሀገር ብትሆንም ቅሉ ግን ዛሬ ድረስ ሕዝቧን በበቂ ሁኔታ ልትመግብ አልቻለችም:: ሀገሪቱ የብዙ የዘባነ ምድርና የከርስ ምድር ሃብቶች ባለቤት ሆና ሳለ በዚህ መጠን መቸገሯ የዓለማችን የከበረች ደኀ ሀገር ነች ማለቱ ይበልጥ ይገልጣታል:: 85% ከመቶ በላይ ሕዝቧ አፈር ገፊ ( ገበሬ) ወይም አርሶ አደር ሆኖ ሳለም በልዮ ልዮ ጊዜም የርሃብ ዋና መናገሻ ከተማ ሆና ቆይታለች ። ታድያ ብዙ ገበሬ እንጂ ብዙ እህል በሌላት ሕዝቧን እንኳ ቢያንስ በቀን ሁለቴ መመገብ ባልቻለች በዚህች ምስኪን ሀገር ላይ አንበጣ በእንግድነት መምጣቱና ምግብ ታቀርብለት ዘንድ መከጀሉ አንበጣውን ያልታሰበ ጥቁር እንግዳ አሰኝቶታል ::
ልጆችዋ ዘር በመዝራት ምርታማነት ላይ ሳይሆን ዘር በመቁጠር የመለያያየት አጥር በማጠር ላይ ተወጥረው የከረሙባት በሌላ በኩል ደግሞ Covid 19 ተበዬው በዜና ብቻ የምናውቀው የፕሮፓጋንዳ በሽታ ሲያምሳት የሰነበተችሁ ቤተኛዋ ኢትዮጵያ ጥቁሩን እንግዳ የአንበጣውን መንጋ ልታስተናግደው አትችልም።
የርሃብ ተምሳሌት በሆነች ደኃ ሀገር ላይ ለመስተንግዶ መምጣት ጊዜ ና ጉልበትን ማባከን መሆኑን ለአቶ አንበጣ ማን በነገረውም ያሰኛል :: ለዚህ ማሳያው ቆየት ባሉ የOxford ዲሽክነሪዎች ላይ ረሃብ የሚለውን ተርምኔሽን(ፈቺ )ካስቀመጠ በኃላ For examples ብሎ በአሳዛኝ መልኩ Ethiopia ብሎ ለርሃብ አብነት አድርጎ ይጠቅሳታል :: በእውነቱ በተረፈ ዓለሙ ኢትዮጵያ የምትታወቀው በርሃብ ተምሳሌነነት መሆኑን መስማት እጅግ ያማል። አንበጣውም ይህን አለማንበቡና አለማወቁ ይገርማል :: ቢያንስ ቢያንስ የሚያስተራርድ በቂ የዘር ክፍፍል እንጂ የሚያስተዳድር በቂ የእህል አቅርቦት እንደ ሌለን ቢያውቅ ኖሮ ጥንብ አንሳ (አሞራ)እንጂ አንበጣ አይመጣም ነበር ለነገሩ ሆድ ብቻ የሆነ ፍጡር ስለ ሆድ እህል እንጂ ስለ አእምሮ ምግብ ስለ ንባብ መች ይጨነቃል :: ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እንዲሉ :: በማያነብ ማህበረሰብ ውስጥ የሚያነብ አንበጣ እንዲመጣ መጠቁ በእራሱ አለ ማንበብ ነው ። ያው አለ አይደል የሀገሪቱን ሥር የሰደደ ድህነት ዓለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ምሥጢር በመሆኑ ይህ አይጠፋውም ከሚል እሳቤ ነው :: እንደውም አሁን አሁን በነ አበበ ቢቂላ በነ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በአጠቃላይ በአትሌቲክሱ ፈርጦች ይህ በርሃብ የጠለሸ ስሟ ትንሽ ፈገግ እያለ መጣ እንጂ ቀሪው ዓለም ኢትዮጵያዊያን ሆዳቸውን ለመሙላት ካልሆነ በቀር ሮጠን ነጭን የምናሸንፍ ና የወርቅ መዳልያ ማጥለቅ የምንችል አይመስላቸው ነበር:: አፍና ሆድ ብቻ እንጂ ሮጦ የሚያሸንፍ እግር ሰርቶ የሚያድር እጅ እንዳለን የሚጠራጠሩም ብዙ ነበሩ :: እንዲያውም አንድ የስፖርት ጋዜጠኛ የእግር ኳስ ጨዋታ ለመዘገብ ወደ ውጪ በሄደበት አጋጣሚ ፈረንጆቹ ከየት እንደመጣና ለምን እንደመጣ ይጠይቁታል ጋዜጠኛውም ለዘገባ ከኢትዮጵያ የመጣ የእስፖርት ጋዜጠኛ መሆኑን ይገልጥላቸዋል ነጮቹም በአግራሞት ሆነው እንዲህ ሲሉ ይጠይቁታል ኳስ እኮ የሚያየው የጠገበ ሕዝብ ነው እናንተ ዳቦ ጠግባችሁ ኳስ ታያላችሁ??::
አረ አዎን በደንብ እናያለን ለዛውም በየ ዲኤስ ቲቪው ወኪሎቻችሁ ለሮኒ በሳምንት እረብጣ ገንዘብ እየከፈልን ጠንክረን ሳናርስ ጠንክረን አርሰናልን እየደገፍን እየራበን እናያለን እያዛጋን እንከታተላችዋለን እያንቀላፋን እናፈጥባችዋለን በልማት ሰበብ ታሪካዊ ና ጥንታዊ የአባቶቻችን ሃውልቶች ሲፈርሱ በሌላ ሲቀየሩ ሲሸናባቸው ለምን? እንዴት? እስከ መቼ ? ብለን ሳንጠይቅ ሳንከራከር የፋብሪጋዝ የታኬታ ቁጥር ያነታርከናል በውጤቱ ከተደሰትን ሻማ እናበራላችዋለን ከተከፋን ደግሞ ካገኘን በገጀራ ካጣን በአጣና እንፋጅላችዋለን ከዚህ በላይ መጥገብ አለ?::
እስራኤል አለቅም እግዚአብሔርንም አላውቅም ብሎ ፈርዖን በጠገበ ጊዜ ሀገሩ በጓጉንቸር(በእንቁራሪት)፣በቅማል ፣በቁንጫ መንጋ ተመቶ ነበር የሚገርመው ጓጉንቸሮቹ ወይም እንቁራሪቶቹ ከወንዝ ወጥተው የመይገቡበት የሀገሪቱ ክፍል ወይም ቦታ አልነበረም ኦሪት ዘጸአት ስለዚህ ነገር እንዲ ሲል ይናገራል
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³ ወንዙም ጓጕንቸሮችን ያፈላል፥ ወጥተውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህም፥ ወደ ባሪያዎችህም ቤት፥ በሕዝብህም ላይ፥ ወደ ምድጆችህም፥ ወደ ቡሃቃዎችህም ይገባሉ፤ ⁴ ጓጕንቸሮችም በአንተ በሕዝብህም በባሪያዎችም ሁሉ ላይ ይወጣሉ። ዛሬም በጠገበ ሕዝብና መንግሥት ላይ አንበጣ ፈሷል:: እንዲውም ተመስገን ማለቱ አይከፋም ወደ እንጀራ ማሳችን እንጂ ወዳቦካነው ወደ እንጀራ ሊጣችን ወደ ቦአቃችን አልገቡምና ፈርዖንን ያስቸግረው የነበረው የጓጉንቸር (የእንቁራሪት )መንጋ ብቻ አልነበረም በፍርድ በአደባባይ በተቀመጠበ ጊዜ ሁሉ እያሳከኩ ያሰቃዮ የቁንጫ መንጋና የቅማል መንጋም ወርዶበታል :: ታዲያ ለዚህ ሁሉ የተዳረገው እስራኤልን አለቅም እግዚአብሔርን አላውቅም ማለቱ ነበር ዛሬም የሕዛብን የነጮችን ማዳመሪያ ተጠቀሙ እያለ ሀገር በቀል የእህ ዘሮችን ካልፈረንጃችሁ የሚል ጭፍን ገልባጭ መንግሥት የአዛብን የማዳበሪያ ስሌት ካለቀቀ በመሰል መንጋ የዳበርኩ ያለው ሰብል በአንበጣ በውደዉ አይቀርም ዝናብን ለዘር ጠልን ለመከር ያልከለከለ ፈጣሪ እያለ የነጭን የላብራቶሪ ውጤት መሞከሪያ ማድረግ ፈጣሪን ማሳጣት ነው የጉዳዮ አሳሳቢት በዚሁ የሚያበቃ አይደለም ወደ ሰው ልጆችም ያድጋል የፋፋና የዳበረ ልጅ እንድትወልዱ ይህን ማዳበሪያ እንክብ እናትየው ትጠቀም እያሉ የሚያቅሙንስ ክኒን ጤነኛ ነውን? ወደፊት በዚሁ ከቀጠልን በሐበሻ ምድር ሐበሻዊ ጤፍ ሳይሆን መጥፋቱ አይቀርም ሐበሻዊ ባልና ሚስትም የፈረነጀ ሐበሻ መውለዳቸው አይቀርም ምን ይደረግ መደበሪያው ነዋ:: እግዚአብሔር ከማህጸን ጀምሮ የሚጠብቀውል ልጅ ስንፈላሰፍና ፈረንጃዊ ስብከት አሳምኖ ሲያጠምቀን ለማደበሪያ ልጅ ለመውለድ መገደዳችን አይቀርም :: በመጠን ያነሰና በመልክ የጠቆረ ነገር ሁሉ ጥቅም አልባና የማይረባ ኃላ ቀር ያደረገው ማነው?ከጥቁር ጤፍ ይልቅ ለነጭ ጤፍ ቦታ መስጠት ከስንዴ ዳቦ ይልቅ የፍርኖ ዳቦን መመገብና መጋገር የትልቅነት ልኬት ማድረግ ከሐበሻ ዶሮ ይልቅ የኤልፎራ ዶሮን ማንጠልጠል እንደ መዘመን መቁጠር ከዶ/ር ገቢሳ እጄታ ድርቅን ተቆቁሞ ብዙ ምርቶችን በጥቂት ግንዶች ላይ ማፍራት የሚችሉ የማሽላ ዘሮችን ከመጠቀም ይልቅ ውኃ ጨራሽ የሆነ የቻይናን የሩዝ ምርትን የአሜሪካንን የተቀቀለ ስንዴ ቅልውጥ የምወድ የኛ ስንዴ የኛ በቆሎ የኛ ማሽላ የኛ በግ የኛ ዶሮ የኛ እንቁላል ሁሌ ከፈረንጅ ያሱ መስለው የሚሰመኑ እስከ መቼ ነው? የተሰጠንን የናቅን ያልሰጠንን የዘን የማንለቅ ግብዙ ፈርዖኖች ዛሬም ነገም ይህን አስተሳሰባቸውን እስካልለቀቁ ድረስ በመንጋ ከመውረር እያመልጡም እግዚአብሔርን ካላወቁ አያርፋም ምን አልባትኮ እግዚአብሔር እነዚህ የአንበጣ መንጎች ያዘዘው በማደበሪያች ምክንያት የበቅሉ ሰብሎቻችን ሰው ቢመገባቸው ውሳጣዊና እረቂቅ ችግሮችን የሚያስከትሉ የሰው ጠንቅ የሆነ አዘመራዎች ሆነው ይሆናል ወደፊት በማዳበሪያ የሚወለዱ ሕጻናትም ካሉ ሰው የሚበሉ የአንበጣ መንጎች መላካቸውም አይቀሬ ማሳያ ነው...ይቆየን:: ኑሮዬ ይበቃኛል ባዬች ያድርገን አሜን!“ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚ
ለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤” 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥6


      @YEAWEDIMERITE
አዘጋጅ :- ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
ሐምሌ 18 ቀን 2012ዓ,ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
  
        #ዓውደ ምህረት የእናንተ
           👇👇👇👇👇👇   
           @AwediMeherit
           @AwediMeherit
ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይበልጡኑ ደግሞ ለክርስቲያኖች እንኳን ደስ ያለኘን !
"ስለ ሰማዮ ንፋስ ስለ ወንዞችም ሙላት እንማልዳለን"

እነሆ ከአሁኟ ሰዓት ጀምሮ ያሎትን ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ
#እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ ! አሜን🙏

የመልዕክት ሳጥን
@YEAWEDIMERITE
በኩል ይስደዱልን!

#ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Forwarded from Betsebay Amare
በአሁን ሰዓት በኛ ቤተክርስቲያን ልጆች እየተደረገ ያለው ግድያ እንዴት ይታያል እንደ ቤተ ክርስትያን አስተምሮ?
ስለጠየቁ እናመሰግናለን በተለይ ደግሞ ወቅቱንና ጊዜውን ያገናዘበ ዘመኑን የዋጀ ጥያቄ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ነው ::በርቱልን:: የቤተ ክርስቲያን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር የሕይወትን ቃል ያሰማልን::
ምላሽ :- ወደ አተታውና ወደ መደመደሚያው ከመሄዳችን በፊት አጠር ያለና ቀጥተኛ ምላሽ እንስጥ :: ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ እየደረሰባቸው ያለውን ግድያ እንዴት ታየዋለች ? ለሚለው ጥያቄ ቤተ ክርስቲያን የልጆቿን ሞት እንደ ሰማዕታት ሞት ታየዋለች:: የሚል ግልጽ መልስ እንሰጣለን :: ሰማዕታት ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን የሐዘኟ ምንጮች ፣የጠባሳዋ ማስታወሻዎች ፣ የቁስሏ ጥዝጣዜዎ ሳይሆኑ ጌጦቿ ናቸው ::ጌጥን ደግሞ ሁል ጊዜ ስለ እርሱ እያወሱ ያጌጡበታል ይዋውበታል እንጂ አፍረው አይሸሽጉትም ቤተ ክርስቲያንም በጌጦቿ አታፍርባቸውም ከዛ ይልቅ ቤተ ክርስቲያ አንጻ ፣ታቦት ቀርጻ፣ ገድል ጽፋ ፣ቀን ቆጥራ ዘላለም ስታዘክራቸው ትኖራለች::

ሰማዕትነት የራሱ የሆነ ሃይማኖታዊ ፋይዳና ረብ ያለው የቅድስና ማግኛ አንዱ መንገድ ነው :: ቢሆንም ግን ሁሉም ክርስቲያን አንገቱን ለሰይፍ ሰቶ ሃይማኖቱን ያለ ተከታይ ቤተ ክርስቲያንን ያለ ቀዳሽ ሀገርን ያለ ወራሽ ባዶ አርጎ ያስቀራት ማለት አይደለም :: ክርስትና ቀኝ ጉንጭህን ለሚመታህ ግራህን ደግሞ አዙረህ ስጠው የምትል የፍቅር ሕግ ብትሆንም ቅሉ ዝም ብለህ ስትጠፈጠፍ ሁለ ግባ ማለት ግን አይደለም የእግዚአብሔር መቅደስ የሆነ ሰውነታችን ማንም እንዲጠፈጥፈው አይደለም በአምሳሉ አክብሮ የፈጠረን :: እንዲያውም አንድ አባት አንድ ወጠጤ መቶ በጥፊ ፊታቸውን ይመታቸዋል እርሳቸውም እንደ ወንጌሉ ብለው ሌላው ጉንጫቸውን አዙረው ይሰጡታል ያም ደፋር ወጠጤ ያለ እርህራሄ ደግሞ በዚህ በኩልም ይመታቸዋል ጥፊው በጣም ያመማቸው አባም መልሰው የሁለት ጥፊ እጥፍ በሚሆን ቦክስ መተው መሬት ላይ ይዘርሩታል ወጠጤውም እንዴ አባ ወንጌል ተላለፉ እኮ ቢላቸው ውይ ልጄ አዙረ ስጠው እንጂ ደጋግመህ ስጠው አላለም አሉት ይባላል። ሰማዕትነት የራሱ ወግና ሥርዓት ያለው እንጂ ዝም ብሎ ሄዶ ከእሳት መማገድ፣ በሰይፍ ማለቅ በጥይት መደብደብ ማለት አይደለም ስለዚህ ክርስቲያኖት በወንድሞቻችን እየደረሰ ያለሁን መከራ እያየን እየተሳቀቅን ሃይማኖት መለወጥ ወደ ኃላ ማፈግፈግ ወይም እንደ ሰማዕታት ብለን ደግሞ ተገዝግዘን ማለቅ ብቻ የለብንም ክርስቲያን አንድ የሀሳብ ጽንፍ ይዞ የሚቆም ጽንፈኛ አይደለም ነገሮችን በማገናዘብ በሚዛናዊነት ይቆማል እንጂ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያስተማረን “እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።” ብሎ ነው ማቴዎስ 10፥16 ::
በተአምረ ኢየሱስ ላይ ተጽፍ እንደምናነበው ህጻኑ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ህጻናት ጠባይ ሲጫወት ሲታዘዝ ሲወድቅ ሲነሳ እናያለን በዚሁ የህጻናት ጠባይም ትምህርት ቤት ገብቶ ሳለ የመምህሩን የመጻፊያ ቀለም ሳያውቅ ጥቁሩን ከነጩ ይደባልቀዋል መምህሩም ቁጡ ነበርና የምጽፍበትን ቀለም ደፋህ ይልቁኑ ጥቁሩን ከነጩ ደባለክብኝ ብሎ ህጻኑን ኢየሱስ ክርስቶስን በጥፊ መታው ይህን ጊዜ ግን ግራ ጉንጭህን ለሚመታህ ቀኝህን ደግሞ አዙረ ስጠው ብሎ የሚያስተምር አምላክ ሆኖ ሳለ አዙሮ ግይ ጉንጩን ሲሰጠው አንመለከትም ከዛ ይልቅ መምህሩን ጠየቀው :: እንዲ ሲል መምህር ያጠፋሁብህ እንደሆነ አስተካክል ትለኛለ እንጂ ለምን ትመታኛለህ ??? አለው ። የተደባለቀውንም ጥቁርና ነጭ ቀለምም በተአምራት ለየ ብቻ ለይቶ ሰጠው:: እንደ ሰውነቱ አጠፋ እንደ አምላክነቱ ጥቁሩን ከነጭ ለይቶ ሰጠው :: ታዲያ ከዚህ የምንማረው ቀኝ ጉንጭህን ለሚመታ ግራህን ደግሞ አዙረ ስጠው የሚለውን ይዞ ሲጠፋጠፉሁ መዋል ፍጽም አግባብ አይደለም ሰማዕታትም አያሰኝም ከዛ ይልቅ ለምን ትመታኛለህ ማለቱና እራስን ማስከበሩ የተገባ ነው ። ዛሬም በልዮ ልዮ ዱላ የሚመቱን ቁጡ መመህራኖች በዝተውብናል ለምን ትመቱናላችሁ ብለን ልንጠይቅ ይገባል።። “ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።” ሮሜ 8፥36 ::

ታድያ ምን እናድርግ?
#ስለ ቀናች ሃይማኖት #መጋደል አለብን::
ክርቲያኖች በሃይማኖታችን ጸንተን መሞት ብቻ ሳይሆን መኖርም ተፈቅዶልናል “ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።” ይሁዳ 1÷3
ማስታወሻ :- መጋደል ሲባል ቆሞ መገደል ማለት አይደለም ባንገል እንኳ እንዳንሞት እራሳችንን መከላከል መቻል ማለት ነው :: ልክ ድብድብ ስንል የሁለት ሰዎች ሱታፌ ያለበት ኩነት እንደሆነ ሁሉ መጋደልም እንዲሁ ማለት ነው አንዱ ወገን ብቻ የሚያጠቃበት ከሆነ ድብደባ እንጂ ድብድብ አያሰኘውም ::
እኛ ክርስቲያኖች ሙስሊሙ ያርደናል ፖለቲካው ያቃጥለናል ሰይጣን ይሸምቅብናል መለያየት ያተኩሰናል ጴንጤው ያሰናክለናል ነገር ግን ይህ የክርስቲያኖች ጠባይ ነው በመቱን ቁጥር እንደ ሚስማር እንጠብቃለን በገፉሁን ቁጥር እንደ ቅቤ ከፍ እንልና የራስ አክሊል እንሆናለን የሰማዕታት ደም ዘር ነውና ሊቀንሱን ሲያርዱን 30፣60፣100 ፍሬ ሆነን በዝተን እናፈራለን ።
#በጸሎት እንትጋ
ክርስቲያኖች በሃይማኖት ነቅ የሌለባቸው ጻድቃኖች(እውነተኞች) ናቸው ። በመሆኑም በእምነት ሆነው የሚጸልዮት ጸሎት ተሰሚነት አለው ጸሎት የክርስቲያኖች ዋነኛ መሳሪያ ነው::“እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።” ያዕቆብ 5፥16
#ስለ ሀገራችን ጸልዮ
#ሰለ ሃይማኖታችን ጸልዮ
#ስለ አንድነታችን ጸልዮ
“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው።” ማቴ26፥41
“በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤” ኤፌሶን 6፥18
#ቀርበን እንወቃት እንማራት
የማያውቁትሀገር አይናፍቅም ነውና ይበልጥ ተቆርቋሪዎቿ ለመሆን ከፈለግን ወደ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀርበን እንማር ታሪኳን እናጥና ያሳለፈችሁን የመከራ ዘመን እንዴት እንዳለፈችሁ መርምረን ለነገ ችግሯ መፍትኤ እናብጅላት::

" የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ። እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ #እርሱም_የእግዚአብሔር ቃል ነው።" ኤፌ 6 ÷11-17 ይቆየን

ሐምሌ 26 ቀን ዕለተ እሁድ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ ማርያም
@YEAWEDIMERITE

ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ሰብስክራይብ ያድርጉ ይጠቀማሉ ይማራሉ
ፍልሰታ ለማርያም ድንግል
🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓ.ም በ፷፬
ዓመቷ ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድና ድካም ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን
ሐዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሔዱ፡፡ በዚህ ጊዜ
አይሁድ ‹‹እንደ ልጇ ‹ተነሣች፤ ዐረገች› እያሉ እንዳያውኩን በእሳት
እናቃጥላት›› ብለው ሥጋዋን ሊያጠፉ በዓመፃ ተነሡ፡፡ ታውፋንያ
የሚባል አይሁዳዊም አጎበሩን ይዞ ሊያወርዳት ሲል የእግዚአብሔር
መልአክ ሁለት እጆቹን ቀጣው፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ
ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ጨምሮ እመቤታችንን በደመና ነጥቆ ወደ
ገነት ወስዶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጣት፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም
እመቤታችን ያለችበት ቦታ እንዲገለጥላቸው ባረፈች በስምንተኛው
ወር ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምረው ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት
መጠየቅ ጀመሩ፡፡
ከዚህ ላይ ‹‹ስምንት ወር ሙሉ ምን ይዘው ቆይተው ነሐሴ ላይ ሱባዔ
ገቡ?›› የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችላል፡፡ በመሠረቱ ቅዱሳን ሐዋርያት
ከስብከተ ወንጌል፣ ከጾም፣ ከጸሎት፣ ከገቢረ ተአምራት ተለይተው
እንደማያውቁ መንፈሳዊ ሕይወታቸው ምስክር ነው፡፡ በመኾኑም
እመቤታችን ካረፈችበት ቀን ከጥር ወር ጀምሮ እስከ ነሐሴ ድረስ
ጥያቄያቸውንና ጸሎታቸውን ባያቋርጡም ከሰው ተለይተው ሱባዔ
ገብተው ጾም ጸሎት የጀመሩት ግን ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምረው ነው፡፡
ቀድሞስ የክብር ባለቤት የጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ኾነው እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም
ተሰውራባቸው እንዴት ዝም ብለው ይቀመጣሉ? ቅዱሳን ሐዋርያት
ሁለት ሱባዔ (ዐሥራ አራት ቀናት) ካደረሱ በኋላም የነገሩትን
የማይረሳ፣ የለመኑትን የማይነሳ እግዚአብሔር አምላካችን ጸሎታቸውን
ሰምቶ ነሐሴ ፲፭ ቀን የእመቤታችንን ሥጋ ሰጥቷቸው በክብር ገንዘው
በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል፡፡ በሦስተኛው ቀንም እንደ ልጇ እንደ ጌታችን
አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይታ
ተነሥታለች፡፡ ትንሣኤዋን ‹‹ከመ ትንሣኤ ወልዳ፤ እንደ ልጇ ትንሣኤ››
ያሰኘውም ይህ ምሥጢር ነው፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ሲሰብክ ቆይቶ ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ
ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ እመቤታችን ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ወደ
ሰማይ ስታርግ ጠፈር ላይ አገኛት፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹ቀድሞ የልጅሽን
ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁን?›› ብሎ ትንሣኤዋን
ባለማየቱ ኀዘን ስለ ተሰማው ከደመናው ይወድቅ ዘንድ ወደደ፡፡
‹‹ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ›› እንዲል፡፡ እመቤታችንም ‹‹አይዞህ!
አትዘን፤ ባልንጀሮችህ ሐዋርያት ያላዩትን ትንሣኤዬን አንተ አይተሃልና
ደስ ይበልህ!›› ብላ ከሙታን ተለይታ መነሣቷንና ማረጓን ለሐዋርያት
እንዲነግራቸው አዝዛ የያዘቸውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው፡፡ ከዚያም
እርሷ ወደ ሰማይ ዐረገች፤ እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም ወረደ፡፡ ቅዱስ
ቶማስ ትእዛዟን ተቀብሎ በክብር ከተሰናበታት በኋላ ወደ ሐዋርያት
ሔዶ እንዳልሰማ እንዳላየ መስሎ ‹‹የእመቤታችን ነገር እንደምን
ኾነ?›› ሲል ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ‹‹አግኝተን ቀበርናት›› ሲሉት ‹‹ሞት
በጥር በነሐሴ መቃብር እንዴት ይኾናል?›› አላቸው፡፡
በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ከዚህ በፊት የክርስቶስን ትንሣኤ
መጠራጠሩን ጠቅሶ እየገሠፀ መከራከሩንና መጠራጠሩን ትቶ ስለ
እመቤታችን መቀበር እነርሱ የሚነግሩትን ዅሉ አምኖ መቀበል
እንደሚገባው ለቅዱስ ቶማስ አስረዳው፡፡ ቅዱስ ቶማስም የያዘውን
ያውቃልና ጸጥ ብሎ ሲሰማው ቆየ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ተቈጥቶ
የእመቤታችንን ክቡር ሥጋ ለቅዱስ ቶማስ ለማሳየት ሔዶ መቃብሯን
ቢከፍት የእመቤታችንን ሥጋ ሊያገኘው አልቻለም፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱስ
ጴጥሮስ ደንግጦ ቆመ፡፡ ቅዱስ ቶማስም ‹‹ወንድሞቼ! አታምኑኝም
ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ከሙታን ተለይታ ተነሥታ ስታርግ
አግኝቻታለሁ›› ብሎ እመቤታን የሰጠችውን ሰበን ለሐዋርያት
ሰጥቷቸዋል፡፡ እነርሱም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ትንሣኤና ዕርገት እየተደሰቱ ሰበኑን ለበረከት ተካፍለውታል፡፡
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስተምሩን በቅዳሴ ጊዜ ሠራዒ
ዲያቆኑ በሚይዘው መስቀል ላይ የሚታሠረው መቀነት መሰል ልብስ፤
እንደዚሁም አባቶች ካህናት በመስቀላቸው ላይ የሚያደርጉት ቀጭን
ልብስና በራሳቸው ላይ የሚጠመጥሙት ነጭ ሻሽ የእመቤታችን ሰበን
ምሳሌ ነው፡፡
በዓመቱ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹ቶማስ የእመቤታችን ትንሣኤዋንና
ዕርገቷን አይቶ እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን?›› ብለው ከየሀገረ
ስብከታቸው ተሰባስበው ሥጋዋን ይሰጣቸው (ያሳያቸው) ዘንድ
ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ጌታችንን ጠየቁት፡፡ እርሱም
ልመናቸውን ተቀብሎ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችንን መንበር፤ ጴጥሮስን
ተራዳኢ ካህን፤ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ
እመቤታችንንም ሐዋርያትንም አቍርቧቸዋል፡፡ እነርሱም
እመቤታችንን በዓይናቸው ከማየት ባሻገር አብረው ሥጋውን ደሙን
ተቀብለዋል (ነገረ ማርያም፤ ትርጓሜ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ
ማርያም)፡፡
ይህንን ትምህርት መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን ያለው ሁለት ሱባዔ
ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ኾኖ በምእመናን ዘንድ መጾም እንደሚገባው
ሥርዓት ሠርተውልናል (ፍት.ነገ.አን.፲፭)፡፡ ይህ ጾምም ‹‹ጾመ
ማርያም (የማርያም ጾም)›› ወይም ‹‹ጾመ ፍልሰታ ለማርያም
(የማርያም የፍልሰቷ ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ‹ፍልሰት› የሚለው
ቃል ‹‹ፈለሰ ሔደ፤ ተሰደደ›› ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን
ትርጕሙም ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር መሔድን ያመለክታል፡፡
‹ፍልሰታ ለማርያም› ሲልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ካረፈች በኋላ ከጌቴሴማኒ ወደ ገነት መወሰዷን (ማረጓን) የሚያስረዳ
መልእክት አለው፡፡
በጾመ ፍልሰታ ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን በየቀኑ በማኅሌቱ፣
በሰዓታቱና በቅዳሴው በሚደርሰው ቃለ እግዚአብሔር ነገረ ማርያም
ማለትም የእመቤታችን ከመፀነሷ ጀምሮ እስከ ዕርገቷ ድረስ ያለው
ታሪኳ፣ ለአምላክ ማደሪያነት መመረጧ፣ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ክብሯ፣
ርኅርራኄዋ፣ ደግነቷ፣ አማላጅነቷ፣ ሰውን ወዳድነቷ በስፋት ይነገራል፡፡
እመቤታችንን ከሚያወድሱ ድርሳናት መካከልም በተለይ ምሥጢረ
ሥላሴን፣ ምሥጢረ ሥጋዌንና ነገረ ድኅነትን ከነገረ ማርያም ጋር
በማዛመድ የሚያትተው ቅዳሴ ማርያም፤ እንደዚሁም ነገረ ድኅነትን
ከምሥጢረ ሥጋዌ (ከነገረ ክርስቶስ) እና ከነገረ ማርያም ጋር
በማመሣጠር የሚያትተው ውዳሴ ማርያምም በስፋት ይጸለያል፤
ይቀደሳል፤ ይተረጐማል፡፡ በሰንበታት የሚዘመሩ መዝሙራት፤ በየዕለቱ
በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም እመቤታችን
ቅድስት ድንግል ማርያም በእግዚአብሔር ለተዋሕዶ መመረጧን፣
ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን፣ ክብሯን፣ ቅድስናዋን፣ ንጽሕናዋን የሚያወሱ
ናቸው፡፡
በጾመ ፍልሰታ ባሕታውያን ብቻ ሳይኾኑ ዓለማውያንም
በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእመቤታችን አማላጅነት የሰይጣንን ፈተና
ድል ለማድረግ እንዲቻላቸው ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በየገዳማቱና
በየአብያተ ክርስቲያናቱ በዓት አዘጋጅተው፣ ሱባዔ ገብተው፣ ፈቃደ
ሥጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው አስገዝተው ይጾማሉ፤ ይጸልያሉ፡፡
እንደዚሁም ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበላሉ፡፡ ይህ ጾም
ለእመቤታችን ያለንን ፍቅርም የምንገልጽበት ወቅት ነው፡፡ በተለይ
ኦርቶዶክሳውያን ሕፃናት በአብዛኛው ትምህርተ ወንጌል የሚማሩት፤
ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የሚቀበሉት በዚህ በጾመ ፍልሰታ ነው፡፡
ጌታችን በስሙ ሁለትም ሦስትም ኾነን ለጸሎትና ለመልካም ሥ

ብንሰባሰብ እርሱ በመካከላችን እንደሚገኝ የገባልንን ቃል ኪዳን
መሠረት በማድረግ (ማቴ. ፲፰፥፳)፣ ዅላችንም በጾመ ፍልሰታ
ሳምንታት በጌታችን፣ በእመቤታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት ስም በቤተ
ክርስቲያን ተሰባስበን ቅዱሳት መጻሕፍትን ከመማር ባሻገር ብንጾም፣
ብንጸልይ፣ ብናስቀድስ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ደሙን ብንቀበል
በበረከት ላይ በረከትን፤ በጸጋ ላይ ጸጋን እናገኛለን፡፡ በኋላም
ሰማያዊውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንችላለን፡፡
ስለኾነም የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ በማሰብ ከልጇ ከወዳጇ
የሚገኘውን ጸጋና በረከት ተስፋ በማድረግ የአባቶቻችንንና
የእናቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በየዓመቱ ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን፤
የምንችል ደግሞ ንስሐ ገብተን አስቀድሰን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር
ደሙን እንቀበላለን፡፡ ነገር ግን በሕግ የተከለከለ እስኪመስል ድረስ
በዚህ ወቅትም ኾነ በሌላ ጊዜ ሥጋውን ደሙን የሚቀበሉ ወጣቶች
ጥቂቶች ናቸው፡፡ ስለዚህም አረጋውያንና ሕፃናት ብቻ ሳይኾኑ
ወጣቶችም ጭምር የመቍረብና የመዳን ክርስቲያናዊ መብት
እንዳለን በመረዳት ራሳችንን ገዝተን፣ ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውንና
ክቡር ደሙን በመቀበል መንግሥቱን ለመውረስ መዘጋጀት
ይኖርብናል፡፡ አምላካችን በማይታበል ቃሉ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ፤
ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው›› በማለት ተናግሯልና
(ዮሐ. ፮፥፶፬)፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት
ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት
አይለየን፡፡

ምንጭ :-ዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው
ሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም( ማህበረ ቅዱሳን)
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
#ሱባዔ

ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ቆየ ሰነበተ ዘገየ ሰባት ማለት ሲሆን ምሥጢራዊ ትርጓሜውም ደግሞ አንድ ሰው ከዚህ ቀን እከዚህ ቀን ድረስ ፈጣሪዬን በጸሎት እገናኛለሁብሎ የሚያቅደው ዕቅድ ነው። ሰባት ቁጥር በእስራኤላዊያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው ፈጣሪ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር አረፈ እንዲል በጸሎት የሚተጉ ምዕመናንም በቀን ሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል ። ሱባዔ የተጀመረው ከመጀመሪያው ሰው አዳም ውድቀት በኋላ ነው ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት እንዴት እንደሚጸለይ እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ። ለአዳምም የጸሎት ጊዜያትን አስተምረውት አስተምረውት ነበርና ጥፈቱን አምኖ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔርም በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል ኪዳን ገባለት ።



ሱባዔ ለምንምክንያት እንገባልን ቢሉ የመጀመሪያው የሚሆነው የሰው ልጅ በባህሪው ኃጢአት የሚስማማው ነው በሥጋ ሰውነቱ ፈጣሪን ይበድላል በፈጸመው በደል / ኃጢአት/ ሕሊናው ይወቅሰዋል በዚህም ያዝናል ይጸጸታል በሰራው ኃጢአትም ልቡ ይደነግጣል በዚህ ጊዜ የፈጣሪን ይቅርታ ለማግኘት ሲል ሲል ሱባዔ ይገባል ።እግዚአብሔርን ለመማፀን የሚገባ ሱባዔ አለ ። ማንኛውም ሰው ሱባዔ በገባ ቁጥር ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማጽኖ ሊኖረው ይገባል ምንም የምንለምነውና የምንጠይቀው ነገር ሳይኖር ሰባዔውን ብንገባ የምናገኘው ምንም አይነት መልስ አይኖርም
ስለዚህ ተማፅኖ ሊኖረን ይገባል ። ያለ ምንም ቅድመ ሆኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔው በኋላ ምን እንደተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖራቸው ሱባዔ በመግባታቸው የሚገኙት ነገር አይኖርም ይህን ተገንዝበው ከመግባታቸው በፊት የሚገቡበትን ምክንያት ራሳቸውን መጠየቅ አለባቸው ። ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳት እናቶቻችን ደማቸውን ካፈሰሱበት አጥንታቸውን ከከሰከሱበት ድንቅ ድንቅ ገቢረ ተአምራት የሰሩበት ቦታ ገዳማቸውና አድባራት ላይ የሚገባ ሱባዔ ከቅዱሳኑ ረድኤት ተካፋይ ይደርጋል ። ሱባዔ የተደበቀን ምሥጢር የሚገለጥበት ቁልፍ የቤተክርስቲያን ሥርዓት ነው ቅዱሳን አባቶቻችን ያዩት እራይ ምሥጢሩና ትርጉሙ አልገለጥ ሲላቸው ሱባዔ ይገቡ ነበር እግዚአብሔርም በንጽሕና ሆነ ነው የገቡትን ሱባዔ ተመልክቶ ምሥጢሩንና ትርጉሙን ይገልጥላቸዋል ። ነቢዬ ዕዝራ የመጽሐፍታት ምሥጢር እንዲገልጥለት ሱባዔ ገባ እግዚአብሔር አምላክም ሁሉን ገለጸለት የጠፉትን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍታት ደግሞ ለመጻፍ ችሏል ይህ ምሥጢር የተገለጠለት በሱባዔ ነው ።

ከብሉይ ጀምሮ ያሉ የሱባዔ አባቶቻችን የገቡት ሱባዔ ሱባዔ አዳም ፣ ሱባዔ ሔኖክ ሱባዔ ነብያት
፣ሱባዔ ዳንኤል ሱባዔ ዳዊት በተጨማሪም የግል ሱባዔ የማኀበር ሱባዔ የአዋጅ ሱባዔ በመባል ይታወቃሉ በሐዲስ ኪዳን ከአራት ቀን በኋላ የምገባ ሐዋርያት የገቡት ሱባዔ ነው የፍልሰታ ሱባዔ በዚህ ሱባዔ ተሰውሮ የነበረውን የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋ የተገኘበት ትንሣኤዋ እንዲገለጥላቸው የተገባ ሱባዔ ነው ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን 14 ቀን ያክል በጻም በጸሎት ተማጽነው ትንሣኤዋን ገለጠችላቸው ። እንግዲህ ሱባዔ ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል ወቅቱ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ ስባዔ እንደ መሆኑ መጠን እኛም የሐዋርያቱን ፈለግ በመከተል በንጹሕ ልቦና በትሁት መንፈስ ሆነን የእናታችን ትንሣኤ ይገለጥልን ዘንድ በሱባዔው እንትጋ ። ለሐዋርያቱ በሙሉ የልባቸውን መሻት የፈጸመች የጌታችን እናት ድንግል ማርያም የእኛንም የልባችንን ትፈጽምልናለች። ወቅቱን የጾም፣የጸሎት፣የስግደት፣ የምጽዋት፣ ስለ ሀገራችን ኢትዮጲያ የምናለቅስበት ነው ። ስለዚህ ሁላችን በሱባዔው እንበርታ

“በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።”
— ሐዋርያት 2፥42
#ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit

.....ይቆየን.......
ምንጭ :-እናት ማህበሬ ምክሐ ደናግል ሰሌዴ መጽሔት ሐምሌ ና ነሀሴ2010ዓ.ም የተለጠፈ
#ሱባዔ ነቢያት

እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃል ኪዳን መሠረት በማድረግ ቀደምት ነቢያት በተነሡበት ዘመን ቅደም ተከተል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆንና ዳግም መምጣት ትንቢት ተናግረዋል፡፡ ሱባዔም ቆጥረዋል፡፡ ኢሳ.7.14፡፡ መዝ.49.3፡፡ ዘካ.13.6፤ ዘካ.14.1፡፡ የአንዱ ነቢይ ትንቢታዊ ንግግርና ሱባኤ በአነጋገርና በአቆጣጠር ከሌላኛው ነቢይ ጋር ይለያያል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ትንቢቱን ሲያናግር ምሳሌውን ሲያስመስል ጐዳናው ለየቅል በመሆኑ ነው፡፡ «ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናገረ፡፡» እንዲል፡፡ ዕብ.1.1፡፡ የአቆጣጠር ስልታ ቸውና የሱባዔ መንገዳቸው ቢለያይም ዓላማና ግባቸው ግን አንድ ነው፡፡

#ሱባዔ አዳም

አዳም ትንቢት በመናገርና ሱባዔ በመቁጠር የመጀመሪያውን ሥፍራ ይይዛል፡፡ ምክንያቱም በገነት ሰባት ዓመት ከአንድ ወር ከዐሥራ ሰባት ቀን በተድላና በደስታ ከኖረ በኋላ ሕግ በማፍረሱና የፈጣሪውን ቃል በመጣሱ ያለምንም ትካዜና ጉስቁልና ከሚኖርበት ዔደን ገነት ተባርሯል፡፡ ዘፍ.3.24፡፡ እርሱም ፈጣሪው እንዲታረቀው፣ በዐይነ ምሕረት እንዲጐበኘው፣ ቅዝቃዜው ሰውነት ከሚቆራርጥ ባሕር ውስጥ በመቆም ለሠላሳ አምስት ቀን /አምስት ሱባዔ/ ሱባዔ ገብቷል፡፡ በባሕርዩ የሰውን ልጅ እንግልት የማይወድ ቸሩ ፈጣሪ የአዳምን ፈጽሞ መጸጸት ተመልክቶ «በኀሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርህብከ ወእቤዝወከ በመስቀልየ ወበሞትየኸ በአምስት ቀን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ» ብሎ ተስፋውን ሰጠው፡፡ አዳም የተሰጠውን ተስፋ ይዞ በዓለመ ሥጋ ለዘጠኝ መቶ ሠላሳ አመት ከኖረ በኋላ መከራና ችግር ከበዛበት ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
በወንጀል ተከሶ በወኅኒ የተፈረደበት ሰው ከእስር የሚፈታበትን ዕለት በማውጣት በማውረድ ወራቱንና ዓመታቱን እንደሚቆጥር፣ አዳምም በሞት ቢለይም በሲኦል የነፍስ ቅጣት ካለበት ሥፍራ ይኖር ስለነበር የተሰጠውን ተስፋ በማሰብ ሱባዔውን እየቆጠረ የተናገረውን የማያስቀር የማያደርገውን የማይናገር ጌታየ «እነሆ አድንኀለሁ» ብሎ የገባልኝ ዘመን ተፈጸመ፤ ሰዓቱ አሁን ነው፤ እያለ ሲያወጣ ሲያወርድ ቸር አምላክ ሰው ኾኖ ሥጋ ለብሶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ፡- «ተንሥኡ ለጸሎት ለጸሎት ተነሡ፤ ሰላም ለኩልክሙ፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን» በማለት አዳምን ከነልጅ ልጆቹ ነጻ አውጥቶታል፡፡ አዳምን በመከተል ልጆቹም አበው ቅዱሳን ነቢያት ሱባዔ በመግባት የተስፋን ዘመን በመቁጠር በመልካም ግብር ተከትለውታል፡፡ በዚህም መሠረት በርካታ ነቢያት በተለያየ ስልት ሱባዔ ቆጥረዋል፤ እኛም ሱባዔ ከቆጠሩ ነቢያት የተወሰኑትን በዚህ ጽሑፍ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

#ሱባዔ ሔኖክ

ጻድቁ ሔኖክ፣ የያሬድ ልጅ ሲሆን፣ በትውልድ ከአዳም ሰባተኛ ነው፡፡ እርሱም በሕይወቱ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ቤት ንብረቱን በመተው በሱባዔና በትሕርምት እግዚአብሔርን አገልግሏል፡፡ ፍጹም አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ሰው በመሆኑ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መልካም ግብር ተመስክ ሮለታል፡፡ «ሔኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፡፡» ዘፍ.5.22፡፡ ይህም በመሆኑ እግዚአብሔር የሱባዔውን ዋጋ ቅዱስ መንፈሱን በረድኤት ስለ አሳደረበት ትንቢት ተናግሯል፤ ሱባዔ ቆጥሯል፡፡ በሰማይ ተሰውሮ ሳለ ስለ ቅዱሳን መላእክት፣ ስለ መሲሕ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ፀሐይና ጨረቃ አመላለስ /ዑደት/ የሚተርክ በስሙ የተሰየመውን መጽሐፍ ጽፏል፡፡ ዘፍ.5 21-24፡፡ ይሁዳ ቁ.14፡፡ ሔኖክ 1.9፡፡
ሱባዔ ሔኖክ የሚባለው ነቢዩ ሔኖክ በመስፈርት የቆጠረው ሱባዔ ነው፡፡ መስፈርቱ /ማባዣ ቁጥር/ 35 ሲሆን 35'19 ሲበዛ በውጤቱ 685 ዓመት ይሆናል፡፡ 685'12 ስናባዛው 7980 ይሆናል፡፡ ይኸውም ሐሳብ የሚያስረዳው ስለክርስቶስ ምጽአት ነው፡፡
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አሁን የደረስንበት ዘመን 7497 ይሆናል፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በ5500 ዓመት ላይ 1997 ዓመትን መደመር ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ከላይ ያስቀመጥነውን 7497 ዓመት ይሰጠናል፡፡ በነቢዩ ሔኖክ አቆጣጠር መሠረት ምጽአተ ክርስቶስ በ7980 ይሆናል፡፡ ከላይ ሔኖክ የቀመረውን ቁጥር ይዘን ከ7980 ዓመት ላይ አሁን ያለንበትን ዘመን /1997/ ስንቀንስ 483 ዓመት እናገኛለን፡፡ ስለዚህ በሔኖክ ሱባዔ መሠረት ምጽአተ ክርስቶስ ሊሆን 483 ዓመት ይቀራል፡፡

#ሱባዔ ዳዊት

ነቢዩ ዳዊት ከእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ታላቅና ተወዳጅ ንጉሥ ነበር፡፡ ዘመነ መንግሥቱ 1011-971 ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደ ነበር ይታመናል፡፡ ነቢዩ ዳዊት ልበ አምላክ እንደ መሆኑ ትንቢት ተናግሯል፡፡ ሱባዔ ቆጥሯል፡፡ ይኽውም ቀመረ ዳዊት በመባል ይታወቃል፡፡ «እስመ ዐሠርቱ ምእት ዓመት በቅድሜከ፤ ከመ ዕለት እንተ ትማልም ኃለፈት፤ ሺ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትላንት ቀን»፡፡ /መዝ.89.4/ የሚለውን መምህራን ሲቆጥሩት 1140 ዓመት ይሆናል፡፡ ይኸውም በጌታ ዘንድ 1140 ዓመት እንደ አንድ ቀን እንደሆነ ነቢዩ ዳዊት ተናግሯል፡፡ ይህም ለዳዊት ሱባዔ መቁጠሪያ /መሥፈሪያ/ ሆኖ አገልግሏል፤ 1140’7= 7980 ዓመት ይሆናል፡፡ ይህም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በ7980 ዓመት ክርስቶስ ዳግም እንደ ሚመጣ የሚያመለክት ነው፡፡

#ሱባዔ ዳንኤል

ነቢዩ ዳንኤል ምድቡ ከዐበይት ነቢያት ነው፡፡ እስራኤል ወደ ባቢሎን ሲማረኩ ተማርኮ ወደ ባቢሎን ወርዷል፡፡ እርሱም ስለ ክርስቶስ መምጣት ትንቢት ተናግሯል፤ ሱባዔም ቆጥሯል፡፡ «ሰብአ ሰንበታተ አድሞሙ ለሕዝብከ፤ ሰባ ሰንበት ወገኖችህን ቅጠራቸው፡፡» ይኸውም ክርስቶስ ከ490 ዓመት በኋላ ሰው መሆኑን የሚያመለክት ትንቢት ነው፡፡ እንዲሁም «እስከ ክርስቶስ ንጉሥ ትትሐነፅ መቅደስ ወእምዝ ትትመዘበር፤ እስከ ንጉሥ ክርስቶስ ድረስ መቅደስ ትታነፃለች በኋላም ትፈርሳለች» ሲል ተናግሯል፡፡
የአቆጣጠር ስልቱም በዓመት ሲሆን ይኸውም ሰባቱን ዓመት አንድ እያሉ መቁጠር ነው፡፡ ይኽውም ሱባዔ ሰንበት ይባላል፡፡ ዳንኤል ሱባዔ ከቆጠረበትና ትንቢት ከተናገረበት ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ሚወለድ 490 ይሆናል፡፡ መስፈርቱ /ማባዣው/ ሰባት ስለሆነ 7’70 ስናባዛው 490 እናገኛለን፡፡ ይኸውም ነቢዩ ሱባዔ ከቆጠረና ትንቢት ከተናገረ ከ490 ዓመት በኋላ የክርስቶስን መወለድ ያመለክታል፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው ቅዱሳን ነቢያት አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረግ ሱባዔ ገብተው በትሕርምት በመኖራቸው ድንቅ የሆነውን የክርስቶስን ልደትና ዳግም ምጽአት ለመተንበይ ችለዋል፡፡ ሱባዔ መግባት የራቀን ለማቅረብ የረቀቀን ለማጉላት ብቃትን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስገኝ መንፈሳዊ ጥበብ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡

**** ይቀጥላል*****