ብስራተ ገብርኤል
ገብርኤል ማለት የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው። አባቶች ሊቃውንት ገብርኤል የሚለውን ስም ገብር (አገልጋይ፣ ሰው) ኤል አምላክ በአንድ ላይ አምላክ ወሰብ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ የሚል ነገረ ሥጋዌውን የሚያወሳ ስመ ትርጓሜ ሰጥተውታል።
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓለመ መላእክት አምላካቸውን በመፈለግ በታወኩ ጊዜ "ንቁም በበ ህላዌነ እስክ ንረክቦ ለእግዚእነ ወአኅድኦሙ መልአክ ሰላም ገብርኤል በቃሉ ለሠራዊተ መላእክት መንፈሳዊያን። ዛሬ መልካም ጎልማሳ ጦር ሲፈታ ድል ሲመታ አይቶ አይዞህ በያለህበት ቁም ብሎ ጦሩን እንዲያጸና እንዲያራጋጋ ሁሉ ቅዱስ ገብርኤልም በመላእክት ሽብር ሲጸናባቸው ባየ ጊዜ አይዟችሁ ፈጣሪያችን ፈጥሮ አይጥለንምና እስክናገኘው እስክናውቀው ድረስ በያለንበት እንቁም ብሎ አጸናቸው አረጋጋቸው።" በዚህም መላእክት የቅዱስ ገብርኤልን ቃል ሰምተው በያሉበት ጸንተው ቆመዋል።
ይህ አጽናኝ መልአክ ጥንት ዓለመ መላእክትን እንዳጸናቸው የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ ደግሞ እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃል ኪዳን በመፈጽም ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ፍጹም ሰው በመሆን ዓለሙን እንዲያድን የብስራቱን ዜና ለሰው ልጆች እንዲያበስር ወደ እመቤታችን ተላከ።
ይህ ብስራታዊ መልአክ ከስድስት ወር በፊት በመወለዱ ብዙዎች ደስ የሚሰኙበት የጌታን መንገድ የሚጠርግ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንደሚወለድ ለካህኑ ዘካርያስ አብስሮት ነበር። ከስድስት ወር በኋላ ደግሞ እመቤታችንን አብስሯታል።
እስኪ እነዚህን ሁለት ብስራቶች እንመልከት።
መልአኩ የብስራቱን ዜና ለካህኑ ሲያበስረው "ይህ እንዴት ይሆናል? እኔ አርጅቻለው። ሚስቴም ሙቀት ልምላሜ ተለይቷታል።" በማለት ተቃውሞታል። መልአኩም "አኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ገብርኤል ነኝ። የነገርኩህን አላመንክምና ሕፃኑ እስኪወለድ ድረስ ዲዳ ትሆናለህ።" በማለት መልአኩ ለእግዚአብሔር ቀንቶ ካህኑን ቀጥቶታል። በአንጻሩ እመቤታችንን በሚያበስራት ጊዜ እርሷም "ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?" የሚል ጥያቄ ጠይቃው ነበር። መልአኩም ካህኑ ዘካርያስን እንደቀጸፈው እርሷን ግን ሊቀስፋት አልደፈረም። ይልቁንም የዘመዷ ኤልሳቤጥ ከሸመገለች ካረጀች የመውለጃ ጊዜዋ ካለፈ በዋላ የመጸነሷን ማስረጃ ማቅረብ ተያያዛ። በስተ መጨረሻም "እስመ አልቦ ነገር ዘይስሀኖ ለእግዚአብሔር። ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም።" ብሎ ሲረታት እርሷም "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ። እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ይደረግልኝ።" በማለት የብስራቱን ዜና ተቀበለች። በዚህች ቅስፈት ከሦስቱ አካል አንዱ አካል ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማኅጸን አደረ። የአዳም የድኅነቱ መንገድም እነሆ ተጀመረ። ይህም የሆነው በመጋቢት 29 ቀን ነው። አባቶች በቀኖና በዓሉን ታኅሳስ 22 እንዲከበር አውጀዋል።
ከመልአኩ ከቅዱስ ገብርኤል ከእናታችን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት ይክፈለን።
መልካም በዓል።
ይቆየን።
አዘጋጅ #አቤኔዘር_ማሙሸት
👉 @AwediMeherit