ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ጥያቄ

ኃጢአትን ለካህን መናዘዝ ተገቢ ነውን? ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ የተፈቀደ ነው ወይስ ኑዛዜ አያስፈልግም?

#መልስ

ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ

† የሰው ልጅ ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ ለሰራው ኃጢአት ቅጣቱን ይቀበላል። የሰራውን ኃጢአት ለንስሐ አባቱ በመናዘዝ በካህኑ ፊት መናዘዝ በራሱ ቅጣት ነው። ኑዛዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ከጥንት ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ ሲተገበር የነበረ እና በሐዲስ ኪዳንም ተጠናክሮ የቀጠለ ንስሐን የመፈጸሚያ ሥርአት ነው።

ኃጢአትን አምኖ ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሔር መናዘዝ ነው። ኢያ 7:19 "ኢያሱም አካንን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጥ ለእርሱም ተናዘዝ ያደረከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ አለው።"

ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት የንስሐ ጥምቀትን በሚያጠምቅ ጊዜ የሰሩትን ኃጢያት ይናዘዙ ነበር። ማቴ 3:5 "ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ ይጠመቁ ነበር።" ኑዛዜ ተገቢ በመሆኑ ዮሐንስ መጥምቅ እያናዘዛቸው የንስሐን ጥምቀት አጠመቃቸው። ማር 1:5

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማሰር፣ የመፍታት እንዲሁም ኑዛዜን የመቀበል ጸጋን ለካህናት ሰጥቷቸዋል። ሉቃ 5:14 ማቴ 18:18

ሐዋርያት አባቶቻችንም ኑዛዜን በመፈጸም ኃጢአታችን እንደሚሰረይ አስተምረውናል። ያዕ 5:15–16

☞ በመሆኑም ኃጢአትን ለንስሐ አባታችን መናዘዝ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ኃጢአታችንን ለንስሐ አባታችን ተናዘን በንስሐ ሳሙና ታጥበን የንስሐ ፍሬን አፍርተን አዲስ ሰው እንድንሆን አምላካችን በቸርነቱ ይርዳን።

ይቆየን!

በወንድማችን #አቤኔዘር ማሙሸት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit