ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ከወደቁ አይቀር .....#ለጽዮን
____________________

አንዳንድ ውድቀቶች ካለ አስፍላጊ አቋቋሞች በእጅጉ የተሻሉ ናቸው ። ለምሳሌ ከሐውልቱ እንደምናየው ለጽዮን መውደቅ በእውነቱ ዋጋ ያለውና የተሻለ አወዳደቅ ነው::

#ይህ በመጠኑና በውበቱ ከፍ ያለው ሃውልት አሁን ሳይወድቅ ቆሞ ካለውና በቅርቡ ከሮም ከመጣው ዕድሜ ይሁን በሰው ሀገር ያለ ቦታው መቆሙ የሞራል መላሸቅ ያስከተለበት የሚመስለሁ እንደ አዛውንት ጎብጦ በመደገፊያ በግድ ከቆመው ሐውልት በተለየ መልኩ በፊት ለፊቱ ወድቆ ይታያል::

ይህ የአክሱም ሐውልት ከመሐመድ ግራኝ ወራራ በኋላ የተነሳችው ሴቷ ግራኝ ዮዲት ጉዲት ካስከተለችው ጥፋቶች መካከል የጥፉቷን ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የሆነ ታሪካዊ የሀገር ቅርስ ነው :: ዮዲት በክርስቲያንኖችና በቤተክርስቲያን ላይ ባደረባት የተሳሳት ጥላቻ ኃያሌ የጭካኔ ተግባራትን በክርስቲያኖችና በቤተክርስቲያን ላይ ያስከተለች የታሪክ ጠባሳ ነች ::

#ከበዙ ጥፉቶች በኃላ ወደ እዚህ ወደ አክሱም ሐውልት መቆሚያ አካባቢ ስትደርስም ጭፍሮቿ እንደለመዱት የእክሱምን ሐውልቶች ይጥሏቸውና ይሰባብሯቸው ዘንድ ተራኮቱ ዮዲትም ሁሉንም ሐውልቶች አትጣሏቸው አንዱንና ትልቁን ለዐይንም የሚማርከውን ሐውልት ብቻ ጣሉት ሌሎቹን ግን እንዳትነኩ ስትል ትዕዛዝ አስተላለፈች ጭፍሮቿም ለምን? ሲሉ ጠየቁ


በሌሎች ቦታዎች እዳደረግን ሁሉንም ብንሰባብርና ብናወድማቸው መጪው ትውልድ ሲያቸው አንድ ጊዜ ተበሳጭቶ ብስጭቱን ይተወዋል የሚያምረውን ና ተለቅ የሚለውን ሃውልት ብቻ ብንጥለውና ሌላው ብንተውለት ግን ባየውና በሰማው ቁጥር ይህ ትልቁኮ ባይወድቅ ከነዚኞቹ በላይ ውብ የሀገር ቅርስ ሆኖ ይታይ ነበር እያለ ዘላለም ዓለሙን እየተቃጠለ ሲብሰለሰል ይኖራል ገባችሁ ስትልም አምቧረቀችባቸው::


#ሐውልቱ ግን ለትውልዱ ቁጭት ሳይሆን ትምህር ይሆን ዘንድ ወደ ጽዮን ወደቀ ተንበርከኮም ሰገደላት ። የጌታዬ እናት በፊትሽ እቆም ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እያለም ተሳለማት ሉቃ1÷43። ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ ልብ ያለውም ልብ ያድርግ "በፈሊጥ ካልገባው በፍልጥ " እንዲሉ ። ሰው ሁለት ጊዜ ይማራል ይላሉ ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን አንድ በሣር " ሀ " ብሎ ካልሆነም በአሳር " ዋ "ብሎ ። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ብራና ዳምጠው ቀለም በጥብጠው በሣር ስግደት እንደሚገባት ሲያስተምሩን ካልገባን በአሳር ጎንበስ ማለታችን አይቀርምና ከአሳሩ በፊት በሳሩ ተማሩ እንላለን።

#የአስጨናቂዎችሽም_ልጆች_አንገታቸውን_ደፍተው_ወደ_አንቺ_ይመጣሉ ፥ የናቁሽም ሁሉ #ወደ_እግርሽ_ጫማ ይሰግዳሉ፤ #የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል #ቅዱስ_የሆንሽ_ጽዮን ይሉሻል።”
#ኢሳ 60፥14


አ.አ ኢትዮጵያ
ተርቢኖስ ዘተክለ ኤል
ኅዳር 21/2013ዓ.ም የተከተበ
#24ቱ_ካህናተ_ሰማይ_25 ሆኑ !
_______

አስቀድመው ቅዱሳን ሐዋርያት 12 ብቻ ነበሩ ከመካከላቸውም ይሁዳ ገንዘብ ወዶ ዘመድ ለምዶ አገልግሎቱን ትቶ ሄደ ሐዋርያትም ወንጌል በዓለም ሳይሰበክ ቢቀር አገልግሎታችን ተስተጎግሎ መቅረቱ አይደለ ብለው እግዚአብሔር ባወቀ ይሁዳ በተዋት አገልግሎት ፈንታ ሌላ ሰው እንዲሿምላቸው በርናባስንና ማትያስን አቀረቡ መንፈስ ቅዱስም ማቲያስን መርጦ ሰጣቸው:: የሚገርመው ነገር የእግዚአብሔር ድንቅ ስጦታ ነው በአንዱ ይሁዳ ፈንታ ሁለት ምትኮችን ሰጣቸው አንዱ ማቲያስ ሲሆን ሌላው እራሱ በቃሉ ሐዲስ ሐዋርያ ብሎ የሾመው ተክለ ሃይማኖት ነው ቅዱስ ጳውሎስን ከአሳዳጅነት ቅዱስ ጴጥሮስን ከዓሳ አጥማጅነት እደጠራቸው ሐዋርያትን በጠራበት አጠራሩ አባታችን ተክለ ሃይማኖትን እንሰሳ ከሚያድኑበት ("ድ")ጠብቆ ይነበብ) ጫካ ጠርቶ በወንጌል መረብነት ሰው የሚድኑ ("ድ")ላልቶ ይነበብ አዳኝ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጉ ሾማቸው የሐዋርያት ቁጥረም 12 ቢሆንም በሐዲሱ ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ አማካኝነት ያለ ወትሮ 13 ሆነ ምነው መጻሕፍት 12ቱ ሐዋርያት አይደል የሚለው ቢሉ መጻሕፍት በቀረበው የመጥራትም ፀባይ አላቸው 12ቱን ሐዋርያት አስሩም አያለ እንደጠራቸው ማለት ነው ስለዚህ 12ሐዋርያት ስላለ 13ተኛ አይጨመርም አያሰኝም

#አባታችን ተክለ ሃይማኖት ቁጥራቸው ከሐዋርያት ወገን ብቻ ሳይሁን ከስማዕታትም ጋር ጭምር ነው ምነው ሰማዕታት ስለ ክርስቶስ ሲሉ ሥጋቸውን የቆረሱ ደማቸውን ለምስክርነት ያፈሰሱ እንደነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያሉ ሰዎች አይደሉም እንዴ ቢሉ አባታችን ተክለ ሃይማኖት መከራን አብዝቶ በመቀሎል ከሰማዕቱ በምን ተለዮ?በዳሞቱ ንጉስ እጃቸው በሰይፍ ተቆረጠች እግዚአብሔር እንደ ቀድሞ ጤነኛ አደረገላቸውጉልያድን በሚያካክሉ በሞተሎሚ በወታደሮች በሽምግልና አቅማቸው ደም በአፍና በአፍንጫቸው እስኪተፉ ተደብድበዋል በንብ ቀፎ ተደርገው ወደ ገደል ተጥለዋል ከዚህ ሁሉ ስቃይና ደም መፍሰስ በኃላ እራሱ አልበቃ ብሏቸው ወደ አደባባይ ወጥቼ ስለ ስምህ መስክሬ እንደሰማዕታት ደሜን አፍስሼ ልሞት እፈልጋለው አሉ:: እግዚአብሔር ግን ከዚህ በላይ ሰማዕትነት አንደሌለ ሲነግረን እኔ ከአንተ ሰውነት በእመምህ ምክንያት የሚወጣውን ፈሳሽ እኔ እንደ ሰማዕታት ደም አቆጥርልሃለው ብሎ ዕረፍታቸውን በሰማዕታት ዕረፍት ቆጠረው ::
#አንዳንድ ሞኝ ሰዎች ይህን በማንበብ እንዴት የተክለ ሃይማኖት በእመም ከሰውነታቸው የወጣ ፈሳሽ(ተቅማጥ)እንዴት ከሰማዕታት ደም ጋር እኩል ይሆናል? ሲሉ ይሰማሉ ጌታችን መዳኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌሉ" ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል"ሲል ተደምጧል #ማቴ 25 ÷40 ታዲያ ለሰው ማድረግ ለእርሱ እንደማድረግ ተደርጎ ከተቆጠረ ወይም የአባታችን የሰውነት ( ፈሳሽ ተቅማጥ) እንዴት አንደ ሰማዕታት ደም መቆጠሩ ስህተት አይደለም እንደውም ይህ ነገር ስህተት ነው ከማለት ይልቅ የጌታችን ምሳሌ ስህተት ይመስላል ሰው ሲራብ ማብላት ሰው ሲጠማ ማጠጣት ሰው ሲታሰር ሄዶ መጠነቅ የማይራበው እግዚአብሔር ተርቦ እንደ ማብላት የማይጠማውን እግዚአብሔርን ተጠምቶ እንደ ማጠጣት የመይታሰረው እግዚአብሔርን ታስሮ እንደተጠየቀ አድርጉ መቁጠር አንዴት ይቻላል? ሌላውና ወሳኙ ነጥብ በህመም ከሰውነት የሚወጣ ፈሳሽ(ተቅማጥ) እና ደም ከሚያስከትሉት ችግር አንጻር ምንም ልዮነት የላቸውም በሳይንሱም ዓለም አገልግሎቱን ያልጨረሰ ፈሳሽ ከሰውነት ከወጣ በቶላ በሌላ ፈሳሽ ምግቦች እንዲተካ ይደረጋል ለምሳሌ" ሀተት "የተሰኘውን የጠቅማጥ በሽታ ብንወስድ ለሁለት ሳምንት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ቀኞች ተተኪ ፈሳሽ ምግብ ሳንወስድ ዝም ብንለው ወደ ሞት ያደርሰናል ይህ ማለት ደም ሥር ተቆርጦ ብዙ ደም ከፈሰሰ በኃላ ምንም ተተኪ ፈሳሽ ሳይወስዱ እንደመቀመጥ እና እነደሚያስከትለው ችግር ሊቆጠር ይችላል:: ስለዚህ ሰማዕታት ደማቸውን አፈሰሱ ሲባል ለመኖር የሚያስችላቸውን ወሳኝ ነገር(ደም)ከሰውነታቸው ወጣ ማለት ነው አባታችን ተክለ ሃይማኖትም ልክ እንደ ደም ጥቅምነቱን ሳይሰጥ ከሰውነታቸው በመውጣቱ ደሙ ሳይፈስ ቀርቶ ቢሆን ኖሮ ሰማዕታት የክብርን አክሊል ወደ ሚቀዳጅባት ሞት እንደማይቀርቡ ሁሉ አባታችንም ለሞት ባልቀረቡ ነበር::

አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቁጥራቸው ከሐዋርያት ወይም ከሰማዕታት ወገን ናቸው ተብሎ ብቻ አይታለፍም ከካህናተ ሰማይ ከሡራፌል ጋርም ይመደባሉ ለወትሮ ካህናተ ሰማይ ሡራፌል ቁጥራቸው 24ብቻ ነበሩ ኢትዮጵያዊው አባት ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የኢትዮጵያ ሲሳይ ሐዲስ ሐዋርያ ሰማእት ወነብይ ወካህን በተወለዱ እና ባደጉ ጊዜ ግን 25ለመሆን ተገደዋል ::ኃዳር 24ቀን 24ቱ ካህናተ ሰማይ ሡራፌል እንደለመዱት ሥሉስ ቅዱስ ብለው መንበሩን አያጠኑ ሳለ ድንገት ቅዱስ ሚካኤል ከሰዎች ወገን የሆነ ሰው ሲሆን እንደ መላእክት ስድስት የፀጋ ክንፎች የተሰጡት ብርሃን ዘኢትዮጵያ የሆነውን አባታችን ተክለ ሃይማኖትን ይዞ አመጣው የወርቅ ማዕጥንትም ተሰጠው ከዙፋኑም ወዳጄ ተክለ ሃይማኖት ቁጥርህ ከንግዲህ ወዲህ ከ24ቱ ሰማያተ ካህናት ጋር ይሁን አለው:: 25ተኛ ካህንም ሆኖ የሥላሴን መንበር ሥሉስ ቅዱስ እያለ በወርቅ ማዕጥንት አጠነ: : ራዕ ዮሐ 4÷4 ገድለተክለ ሃይማኖት
*ይቆየን*****
#የአባታችን እረድኤትና ምልጃው አይለየን ለዘላለሙ አሜን!!!
#በድጋሚ የተለጠፈ
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ኅዳር 23ቀን 2012 ዓ,ም
Audio
Audio
ለማራዶና ሙት ዓመት የተጻፈ
#የእግዜር እጅ /The hand of God/

እግር ኳስ ከዓለማችን ስፖርቶች ሁሉ እጅግ ተወዳጅ የሆነ ስፖርት ነው። የስፖርት ዓይነቶች ብዙና አያሌ ቢሆኑም እንደ እግር ኳስ ስፖርት ግን የገነነ የለም ።

#የስፖርት ዜና እንይ ስንል እንኳ የእግር ኳስ ዘገባዎችን እንከታተል ማለታችን እንደሆነ ተደርጎ ብቻ ይታሰባል ። ይህም እግር ኳስ ሌሎች ስፖርቶች እንዳልተፈጠሩ አድርጎ በማስረሳት በብዝዎቻችን ልቡናና አእምሮ ላይ እንደነገሰ ያመላክታል።

እግር ኳስ ተወዳጅ ከመሆኑ አልፎ ተወዳጂና ታዋቂ ያደረጋቸው ሰዎችም አያሌ ናቸው። ከነዚህ ሰዎች መካከል አርጄንቲናዊው ማራዶና አንዱ ነው።

#እንደ_ግሪጎሪያን የዘመን ቀመር ጥቅምት 30 ቀን 1960 ዓ.ም ከዛሬ 60ዓመት በፊት ላኑስ ፣ ቦነስ አይረስ ፣ አርጀንቲና ከተማ ውስጥ የተወለደው ማራዶና ወይም በሙሉ ስሙ (Diego Armando Maradona) /ዲያጎ አርማንዶ ማራዶና/ ዓለም የምታውቀው በእግር ኳስ ነው።

ይልቁኑ የእግዚአብሔር እጅ /Hand of God/ በመባል በምትታወቀው ግቡ በስፖርቱ ወዳጆች ልብ ውስጥ አይረሴ አድርጋ አትማዋለች ።

#ዲያጎ አርማዶ ማራዶና በ1986 በሜክሲኮ የተካሄደውን ውድድርን በበላይነት መቆጣጠር ችሎ ነበር፡፡ እንግሊዝን በተሸነፈበት የ1-1 የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በዓለም ዋንጫው ውስጥ በጣም የማይረሱ ሁለት ግቦችን አስቆጠረ።

ከነዚህም አንዷ በጭንቅላቱ መግጨት እንደማይሆንለት ሲረዳ እስከሚችለው ከዘለለ በኋላ በቴክኒክ እጁን በመጠቀም ኳሷን ወደ ግብነት ቀየራት ዳኛው በጭንቅላቱን ገጭቶ እንዳገባው አስበው አጸደቁለት። በኃላ ግን በጭንቅላት ሳይሆን በእጅ እንደተቆጠረች የዓለም ሕዝብ ዐወቀ ግቧም “የእግዚአብሔር እጅ ግብ” በመባል የምትታወስ ግብ ሆነችለች፡፡ ዛሬ ድረስ ማራዶና ሲነሳ ይህች ግብ አብራው ትነሳለች።

#በሁላችንም የሕይወት እግር ኳስ ውስጥ አናስተውላትም እንጂ የእግዚአብሔር እጅ አለች ከጅምሩ አጥንት ሰክቶ ጅማት ወጥሮ ደም አሰራጭቶ ያበጃጀን ይህው የእግዚአብሔር እጅ ነው በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔር እጅ የሌለችበት ጊዜና ቦታ የለም "ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ #እጅህ_ትመራኛለች_ቀኝህም_ትይዘኛለች " እንዲል ነቢዩ መዝ138(139)÷8-10

እነ_ቫር እና ጎል ላይን ቴክኖሎጂ ሳይመጡ በፊት እግር ኳስ ከነ ወዙ መቆየት ችሎ ነበር አሁን አሁን ግን ጨዋታ ሁሉ ቆሞ በቴክኖሎጂ እገዛ ፍርድ የሚቀለበስበት ሁኔታ ተፈጥሯል ይህም የተወዳጁን የእግር ኳስ እስፖርት አዝናኝ ኩነቶች በእጅጉ አደብዝዘውታል ።

#በእግር ኳስ ጨዋታ ውስጥ ከበረኛና የእጅ ከሚወረውር ተጫዋች በቀር ኳስን ሆን ብሎ በእጅ መንካት አይፈቀድም ወይም እጅን ወደ ኳስ ማምጣትና መንኳት ክልክል ነው። ካልሆነ ግን "ማኖ" ብሎም የቅጣት ምቶችን ያስከትላል ከፍ ሲልም በቢጫና በቀይ ካርዶች ከጨዋታው ሊያስወጣ ይችላል። ታዲያ ይህች የማራዶና ግብ እንዴት ከግብ ተቆጠረች? ብለክ ታስብ ይሆናል መልሱ ቀላል ነው "የእግዚአብሔር እጅ" ስለሆነች ነው። የእግዚአብሔር እጅ ማኖ የላትም

ምድራዊ ሕግ በእጅህ እዳትነካ ቢያስጠነቅቅህም የእግዚአብሔር እጅ ካንተ ጋር ካለች እግር ኳሱን ቅርጫት ኳስ ብታደርገው እንኳ ዓላማህ ግብን ይመታል ። ባርም ጎል ላይን ቴክኖሎጂም አይቃወሙህም።

#ይህ_ሲባል ግን ወዳጄ የእግዚአብሔር እጅ አጭበርባሪውንና አታላዮን ትወዳለች ከእርሱ ጋርም ታብራለች ማለት አይደለም። የቤቱ ሁለተኛ ልጅ ብትሆንና ብኩርናን አጥብቀህ ብትሻት መሻትህን አውቆ እንደ ያዕቆብ ፊተኛ ያለው ቀዳማዊ ፣ተከታይ የሆነ መሪ ፣ታላቅ ያለው በኩር ያደርግሃል ማለቴ ነው። እንደ ዔሳው ካቃለልካት፣ በኩርናህን ካልጠበካት ፣ በምስር ወጥም ከሸጥካት ግን የመጀመሪያው መጨረሻ አንተ ትሆናለህ በእግር ብታገባው እንኳን ግብ የተሻረ ይሆናል ፊተኞች ዋለኞች ዋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ የሚለው ቃል የሚከወነው በሰው መሻትና በእግዚአብሔር እጅ እንደሆነ ዕወቅ። #ዘፍ25÷34

#የእግዚአብሔር እጅ ተንጠራርተው ከግባቸው ላልደረሱ ብቻ ትቀጠላለች እንጂ ባሉበት ቆመው ያለ ጥረት ተአምር ለሚጠብቁት አትቀጠልም ሞክረህ ባቃተ ጊዜ ብቻ እርዳታ ጠይቅ አቤቱ ከአርያም ክድህን ስደድልኝ በለው።

በባለጋራዬ በሥጋ ፍቃድ፣በሰይጣን ፈተና ፣ በዓለም መውጊ ተውግቼ መሸነፍ አልፈልግም አድነኝ ብለ ጥራው እነሆ፥ የእግዚአብሔር እጅ ፈጥና ታድንለች በጠላቶችህ ላይም ድልን ታቀዳጅሃለች። “ #እነሆ_የእግዚአብሔር_እጅ ከማዳን አላጠረችም ፤ ጆሮውም ከመስማት አልደነቈረችም "
#ኢሳ 59፥1

#እኔም_እንደ_ፔሌ አንድ ቀን በሰማይ ኳስ እንገፋለን ባልለውም ይህን የዓለማችን የእግር ኳስ ፈርጥ ግን ነብስህን ይማራት ሳልል ማለፍ አልፈልግም 🙏!

#Thank_you Armando

ኃ/ማርያም
አ.አ ኢትዮጵያ
ጥር 3/2013 ዓ.ም
Forwarded from Biniam kalayu
Audio
Forwarded from Biniam kalayu
Audio
#አብሳሪው_መላእክ_ቅዱስ_ገብርኤል ሆይ እውነተኛ የሰላም ብሥራት ለኢትዮጵያም አብስራት !
" #ደስታ_ተክለ_ሃይማኖት_ተወለደ"

#የሚገቡት
እንኳን ማርያም ማረችሽ ፣
አሜን!
እንኳን ማርያም ሁለት አረገችሽ
አሜን!
#የሚወጡት
ማርያም ጭንሽን ታሙቀው
አሜን!
ማርያም በሽልም ታውጣሽ.......ይሏታል
የእመጫቷ መልስ አሜን !አሜን! የሚል ብቻ ነው። ይህ የእግዚእኃረያ ቤት ነው። ባሏ ፀጋ ዘአብ ደስታውን መቋቋም አቅቶታል ቤቷ በወዳጆቻቸው እና በጠያቂዎቻቸው እንዲሁም ባለ መውለዳቸው እንደ ኃጢያተኛ ቆጥሮ ይጠቋቆሙባቸው በነበሩ ሰዎች ተጨናንቃለች መካን ሚስቱ ወንድ ልጅን ወልዳለችና ። ለሁሉም እንደ ማዕረጋቸው ምሳ አደረጉላቸው ማጋረጃ ገልጠው እናቲቱንና ልጇን ቅቤ እስኪቀቡ የቸኮሉ ሳይኖሩ አይቀሩም ሌላው ግን ስለ አወላለዷ ለመረዳት ሰሀናቸውን ይዘው የወላዲቱ አልጋ አጠገብ ጠጋ ብለው የተቀመጡም አልጠፋም ።

#እርሷም_የእግዚአብሔርን ቸርነት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት እየመሰከረች ከሞተለሚ ምርኮ እንዴት ባለ ተአምር እደዳነች እያወራች ከባሏ ከፀጋ ዘአብም ጋርም ወንድ ልጅ ስለ መውለዷ አስቀድመው ዕራይን እንዳዮ እየነገረቻቸው ቀኑን በደስታ አሳለፈች ደስታ የሆነ ልጅ ወልዳለችና ።

*ስሙንስ ማን አላችሁት ?
ፍስሐ ጽዮን ( የጽዮን ደስታዋ) ብለነዋል ። ነገር ግን መላእኩ እንደነገረን ስሙ ሌላ ነው ከእናንተም የተሰወረ በልበ ሥላሴ የተጻፈ አዲስ ስም ይወጣለታል ብሎናል። "ተክለ ሃይማኖት"! ሕጻናት እንደሚያለቅሱም አያለቅስም ነበር "ቅኖች ሰዎች ሁል ጊዜ ደስ ይላቸዋል" እንደሚል

"ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለእራስህ አዘጋጀህ " አንደተባለም ሕጻኑ ፍስሐ ጽዮን በተወለደ ገና በሦስተኛው ቀን ከእናቱ እቅፍ ወርዶ "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ ሥላሴን በአንድነት በሦስትነት አመስግነ:: መዝ 9÷2

#ልጆች_የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው የእግዚአብሔር ስጦታ ሁሉ ደግሞ ደስ ያሰኛል ። ይልቁኑ እግዚአብሔር በእነርሱ አድሮ ድንቅ ሥራውን ይሰራባቸው ዘንድ ያዘጋጃቸው የቅዱሳን ሰዎች ልደታቸው ብቻ ሳይሆን እነርሱ እራሳቸው ደስታ ናቸው :: " በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ተድላና ደስታም ይሆንልሃል" ዮሐ1፥14 ተብሎ እንደተጻፈ እውነት ነው በመወለዱ ብዙዎች ደስ ብሎናል በሉቃስ ወንጌል ላይ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል በመጥምቀ መለኮት በቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ደስ እንደሚሰኙ አስረግጦ ነግሮናል።

እነሆ ዛሬ ደግሞ እንደ ዮሐንስ በድንግልና የኖረ እንደ መጥምቁ ካህን ያውም ሰማያዊ የሆነ እንደ አዋጅ ነጋሪው በምድረ ኢትየጵያን ሁሉ እየዞረ ወንጌልን የሰበከ ለእናትና ለአባቱ እንዲሁም ለብዝዎቻችን የደስታ ምንጭ የሆነ የጽዮን ደስታዋ የተባለ ፍስሐ ጽዮን ተወለደ እነሆ እኛም እንደ ተስፋው ቃል ዳግማዊው ዮሐንስ ተወልዶልናልና ደስ አለን::
#መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰለሞን" ጻድቃን በበዙ ቁጥር ሕዝብ ደስ ይለዋል" እንዳለ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በተወለዱ ሰዓት ክርስቲያኖች ደስ ብሏቸዋል ምክንያቱም ጻድቁ ሕሙማነ ነፍስን በትምህርታቸው ሕሙማነ ሥጋን በተአምራታቸው እያዳኑና እየፈወሱ ለሕዝብ ደስታ ምንጭ ሆነዋል ያን ጊዜ ብቻም ሳይሆን ዛሬም በአፀደ ነፍስ ሳሉ ለኛ ለክርስቲያኖች የደስታችን ምንጭ ናቸው " የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለችና " ስለኛ የጽድቅ ሕይወት የሰላም እጦት የሃይማኖት ጉለት የምግባር ዝቅጠት ዕለት ዕለት ወደ ፈጣሪ እየጸለዮ ያማልዱናልና ነው #ያዕቆ 5÷16

በጻድቃን መወለድ ሕዝብ ደስ የሚለው በተወለዱበት ዘመን እና ወር ብቻ አይደለም አንዴ ጻድቃን ከተወለዱ በኃላ ሕዝብ ለዘለአለሙ ደስ ይለዋል ጻድቃን በአፀደ ሥጋም በአፀደ ነፍስም በምልጃቸው ደስ ያሰኛሉና ..... .. ልክ እንደዛሬው......

" #እኔ ግን ለዘለዓለሙ ደስ ይለኛል
ለያዕቆብ( #ለተክለ_ሃይማኖት )
አምላክም ዝማሬን አቀርባለው" #መዝ76÷9
...........ይቆየን........

የጻድቁ አባታችን የተክለ ሃይማኖት እረድኤትና በረከት በሀገራችን ኢትዮጵያ ጸንታ ትኑር
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ታኅሳስ 24/2014 ዓ.ም