ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ጊፍት ሪል እስቴት

በ መሃል አዲስ አበባ #bole atlas ና #CMC ጊዜውን የጠበቁ ውብ መንደሮች ላይ ያሉ  አፓርትመንት ቤቶችንና የንግድ, ሱቆችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል::

እጅግ ዘመናዊ ና ጥራታቸውን የጠበቁ አፓርትመንት ቤቶችን የከተማውን  የሞቀ እንቅስቃሴ ከቤቶ ሁነው ማየት የሚያስችሉ ለመኖር የምያጓጉ #bole atlas ና #CMC

#ባለ 3 መኝታ አፓርትመንት�
#ባለ 2 መኝታ አፓርትመንት�
ቦሌ አትላስ የሱቅ ሽያጭ ተጀምረናል
®Two bed room  👉#144.66m2=16,873,232.3 birr
   first down payment👉20%=3,374,646.46
#151.12m2=17,627,171.5 birr
     first down payment 👉20%=3,525,434.3  #134.10m2=15,641,218.81 birr
  first down payment👉20%=3,128,243.8
®Three,bed room 👉👉
#206.66m2=24,104,617.71 birr
  first down payment👉20%=4,820,923.542
   #216.36m2=25,236,356.51birr
    first down payment👉20%=5,047,271.30
For more information call.....
🏢ጊፍት ሪል እስቴት ለንግድ ምቹ  በሆነው በቦሌ
እስታንደራቸዉን በጠበቀ ሁኔታ እየተገነቡ ያሉ ሲሆን ለተለያዩ ንግዶች:-ለካፌ,ለሱፐርማርኬት,ለቢሮ ለተለያዩ የንግድ አገልግሎት  ይሆናሉ::
👉 ሱቆች ከግራውንድ   ጀምሮ በተለያዩ የካሬ አማራጭ /36ካሬ-137ካሬ/ጀምሮ አለን።
👉ቅድሚያ ለመጣ ቅድሚያ እንሰጣለን!!!
👉ለበለጠ መረጃ በስልክ መስመራችን ይደውሉልን
0910132087
0703271972
👉BOLE Atlas shops

👉Ground floor shops
👉Area
👉36m2
👉48.4m2
👉50.5m2
👉65.2m2
👉61m2
👉74.6m2

👉First floor shops
👉41m2
👉45.3m2
👉53m2
👉90m2
👉137m2
👉Dowen payment 20%
👉pprice270,000/m2

#Contact us

Good luck! ☎️
  +251910132087
  +251703271972
ባለማወቅ ማወቅ !
" #አንቺ የፈጠርሽኝ ማርያም .... "

ደመና ከማረግ ከማይጋርደው ከእናቶቻችን ጸሎቶች መካከል አልፎ አልፎ የምንሰማው ንግግር ነው። አንቺ የፈጠርሽኝ ማርያም ፣ አንተ የፈጠርከኝ ሚካኤል ....ወ.ዘ.ተ
ታድያ ይህን የየዋሃን ጸሎት የሰማ እንደኔ ያለ በማወቅ ያላወቀ ሰው "እናቴ የፈጠረሽኮ እግዚአብሔር ነው ለምን እንደሱ ትጸልያለሽ ? " ብሎ ለማረም ይቃጣዋል።

በርግጥም ሥነ ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ካለመታየት ወደ መታየት አምጥቶ የፈጠረው ፈጣሪ ዓለማት እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሆኖም ግን ይህ የእናቶቻችን የዋህትን ገንዘብ ያደረገች ንግግራቸው በኃያሌው ትክክል ነች ! እንዴት የሚል ካለ ጥቂት ያንብብ ።

#እናቶቻችን የመረዳት እምነት ሲኖራቸው እኛ ደግሞ የማወቅ እምነት አለን ። እውቀት ተኮር እምነት ለሰዋሰው ፣ ለንግግር ጠባይ ፣ ለነጠላና ብዙ ቁጥር እንዲሁም መደብን ጠብቆ አሳክቶ መናገር ወይም መጻፍ ሲሆን ይህን ያላሞላ ንግግርና ጽሁፍም ስሕተት እንደሆነ እናስባለን ስለዚህ የእናቶቻችን ንግግሮችና ጸሎቶች የሚሰምር አይመስለንም። የመረዳት እምነት ያላቸው እናቶቻችንና አባቶቻችን ግን ትክክለኛውን የእምነት መሠረት በልባቸው ይዘው እና አውቀው ማለትም #እግዚአብሔርን ፈጣሪ #እመቤታችንን እመ ፈጣሪ /የፈጣሪ እናት/ እንደሆኑና እንደሚባሉ እያወቁ ለቋንቋ አጠቃቀማቸው ሳይጨነቁ እርሱ የማያውቀው የለም በማለት በየዋህነት ብቻ አንዱን በአንዱ ሊጣሩበት ይችላሉ።
ለምሳሌ እግዚአብሔር ጠባቂያችን ነው ። ቅዱሳን መላእክትም ጠባቂዎቻችን ናቸው። ታድያ አንድ ሰው ተነስቶ ጠባቂዎቼ ቅዱሳን መላእክ ሆይ ብሎ ቢጸልዬ መላእክቱን ፈጣሪ አደረጋቸው አያሰኝም ።ከፈጣሪ ጋር የሚያመሳስላቸውን አንድ ዘርፍ መርጦ ለጸሎት ተጠቀማቸው እንጂ ፈጣሪና ፍጡርን አስተካለ እኩል አደረገም አያሰኝም። በተመሳሳይ እናቶቻችንም የፈጠርሽኝ እመቤቴ ሲሉ እንደ ፈጣሪ የሆንሽ ፈጣሪን የምትመስይ ማለታቸው ነው። የእመቤታችን የማርያም መልክ የአምላክን መልክ ይመስላል እንደሚል /ተአምረ ማርያም መቅድም / አያይዞም ዓለሙ ሁሉ የተፈጠረው ስለ ድንግል ማርያም እንደሆነ ሲያስረዳ አዳምና ሔዋንም እመቤታችን ከነርሱ (ዘር) እንድትወለድ ተፈጠሩ ይላል።
#ሌላው አዳሪ በማኅደሩ ማኅደርም በአዳሪው ይጠራል። ለምሳሌ ሰይፍ በሰገባው ያድራል ይህን የሚያውቅ ሰው ሰይፉ የተለየው ሰገባን ቢያይና ሰይፉ በሰገባው እንደሌለ ባያስተውል ሰገባውን ሰይፍ ብሎ በአዳሪው ሊጠራው ይችላል ።በተመሳሳይ ዳዊት የሌለው ማኅደር ያየ አንድ ሰውም ማኅደሩን አይቶ ብቻ ዳዊቱን አቀብለኝ ብሎ ማኅደሩን ዳዊት ብሎ ሊጠራው ይችላል ትክክል ነው አዳሪ በማኅደሩ ማኅደሩም በአዳሪው መጥራት ልማድ ነውና ሰውየውን ከመግባባት አያግደውም ።
እናቶቻችንም እመቤታችንን አንቺ የፈጠርሽኝ ማርያም ሲሉ ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣሽን ፈጥረሽ የምትመግቢን በኃላም እንደ ብራና ጠቅልለሽ ዓለምን የምታሳልፊ ፈጣሪያችን ነሽ ማለታቸው አይደለም 9ወር ከ5ቀን በማኅጸንሽ ያደረብሽ (የተዋሕደሽ ) ሦስት ዓመት በጀርባሽ ያዘልሽው ሁለት ዓመት ከድንግልና የተገኘ አሊበ ወተት ያጠባሽው እመ ፈጣሪ የፈጣሪ እናት ነሽ፤ እንደ ፈጣሪ የሆነሽ ማለታቸው ነው።
#በርሷ ባደረ በፈጣሪ ልጇ እርሷን ፈጣሪተ ዓለም /የመፈጠር ምክንያት/ ብሎ እንደ መጥራት ነው። ልክ ሰገባውን ሰይፍ ማኅደሩንም ዳዊት ብሎ እንደመጥራት ያለ አጠራር። አንድም በቀደመች ሔዋን እናታችን አማካኝነት ሞት ወደ ዓለም መጣ በዳግሚት ሔዋን በእመቤታችን አማካኝነት ደግሞ በዳግም ተፈጥሮ ሕይወት ተሰጠን ።
ስለሆነም እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የመዳን ምክንያት ብቻ ሳትሆን አዳምና ሔዋንም (የሰው ልጅ ሁሉ) ድንግል ማርያምን ለማመስገን የተፈጠሩ በመሆናቸው የመፈጠራችን ምክንያት ናትና የተፈጠርንብሽ ብለው መጥራታቸው ለእውነት የቀረበ እንጂ ስሕተት አይደለም። ይህን በመሰለችሁ በመረዳት ላይ በተመሠረተችሁ የዋህትን ገንዘብ ባደረገች የእናቶቻችንና የአባቶቻችን ንጽህት ሃይማኖት እናምናለን እንታመናለን !።

ዋቢ :- #ተአምረ ማርያም መቅድም ዘዘወትር
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ጥቅምት 10/2015 ዓ.ም
Audio
Audio
Audio
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ደቂቃ :- #15 ደቂቃ 11 ሰከንድ
መጠን :- # 3.6 m.b ብቻ
Audio
Audio