የሚከላከሉትና ጥቃት የሚያደርሱት በቀንዶቻቸው አማካኝነት ነው ስለዚህ ቀንዳቸው ኃይላቸው ሥልጣናቸው ነው :: ታዲያ ይህ ለአብርሃም በይስሐቅ ፈንታ ይሰዋው ዘንድ የተሰጠው በግ እንደማንኛውም የቀንድ ከብት እራሱን ከአራጁ የሚከላከልበት ኃይልና ሥልጣን ያለው ቀንዳም በግ ቢሆንም ቀንዱ ግን በ አፀ ሳቤቅ ስለተያዘ ያን ያደርግ ዘንድ አላስቻለውም ። በሕልውና ፣በሥልጣን ፣በኃይል ከባሕሪ አባቱ ከአብ እና ከባሕሪ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል (እኩል ፣የተተካከለ) ቢሆንም ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስም በሰው ልጆች የፍቅር እጸ ሳቤቅ ተይዟልና ከልዕልና ወደ ትዕትና ዝቅ አለ ባሕሪውንም ሰውሮ እንደኛ የተገዢ የሰውን አራዐያ ነሳ። ፍቅር ሰአቡ ኃያል ወልድ እም መንበሩ ወአብጽዮ እስከ እለ ሞት / #ፍቅር ኃያል ወልድን ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው"/ የበጉ ቀንድ በእጸ ሳቤቅ ስለተያዘ ከመታረድ እንዳልሸሸ ና በቀንዴም ተዋግቼ ላምልጥ ብሎ የቀንዱን ሥልጣን እንዳልተጠቀመ ሁሉ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስም በፍቃዱ በሰው ፍቅር ተይዟልና ሥልጣን ሁሉ የእርሱ ሆኖ ሳለ ሥልጣኑን ሳይሆን ፍቅሩን ተጠቅሞ ለኛ ተሰውቶ አዳነን:: "ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?" ኢሳ 53፥7-8
#የአሮን በትር ዘኁልቁ 17÷8
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገራቸው፤ አለቆቻቸው ሁሉ አሥራ ሁለት በትሮች፥ እያንዳንዱም አለቃ በየአባቱ ቤት አንድ አንድ በትር፥ ሰጡት፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች። ሙሴም በትሮቹን በእግዚአብሔር ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው። እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች #የአሮን_በትር_አቈጠቈጠች_ለመለመችም_አበባም_አወጣች የበሰለ ለውዝም አፈራች። ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አወጣቸው፤ እነርሱም አዩ፥ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልስ፤ ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ እነርሱም እንዳይሞቱ ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ አለው።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የማክሰኞ እርሻ ትባላለች የማክሰኞ እርሻ ገበሬ ሳይኮተኩታት ውኃም ሳያጠጣት አብባ አፍርታ ተገኝታለች ይህች የማክሰኞ ዕለት እርሻ የመጀመሪያይቱ ምድር ወይም ጥንተ ምድርም እየተባለች ትጠራለች የሶሪያው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊም አክሎ በውዳሴው እንዲ ብሏታል #ሳይተክሏትና ውኃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበር እንቺ እንደርሷ ነሽ" #አባ ኤፍሬም ሶሪያዊ #ውዳሴ_ማርያም ዘ እሁድ
#የኖህ መርከብ ዘፍ 6፥14
በኖህ መርከብ ፍጥረት ከጥፋት እንደተረፈ በእመቤታችንም ከጥፋት ድኗል ። የኖህ መርከብ ሦስት ክፍሎች ነበሯት እመቤታችንም በሦስት ነገሯ ንጽሕት ነች በሥጋዋ ፣በነፍሷ፣ በሕሊናዋ የጋስጫ ፍሬ አባ ጊዮርጊስ "በመኑ ወበ አምሳለ መኑ ናስተማስለኪ " ድንግል ሆይ በምንና በምን እንመስልሻለን ምሳሌን የለሽም" እንዳለ ምሳሌዎች ሁሉ እመቤታችንን አይመስሏትም(አይመጥኗትም)
#የኖህ መርከብ ስምንት ሰዎችና ብዙ ዐይነት እንሰሳት ገብተውባታል ወጥተውባታል
#በእመቤታች ግን ከኃያላ ከጌታ በቀር ወደ እርሷ ገብቶ የወጣ የለም
#በኖህ መርከብ ሲገባም ሲወጣም በሮቹአን ከፍተው ዘግተው ነው
#እመቤታችን ግን ማንም ለዘላለሙ የተዘጋች ገነት የታተመች ፈሳሽ ነችና ዘላለም እትዕምት ፣ዝግ ፣ድንግል ነች ። ጌታችንንም የጸነሰችው እንዲሁ ዝግ ሆና ነው ስትወልደውም እንዲሁ ዝግ ሆና ነው። " ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።" ሕዝ 44÷1-2
#ወደ ኖህ መርከብ የገቡት እንሰሳት እንሰሳዊ ጠባያቸውን ሳይለቁ ነው የወጡት ለምሳሌ ወደ ኖህ መርከብ የገባ አንበሳ ሲወጣም የአንበሳነቱን ሥጋ ቦጫቂነቱን ሳይለቅ ወጣ ፣ነብሩም ደም መጣጭነቱን ሳይተው ወጣ ፣በግም ውኃም መጎንጨቱን ሳር ጋጪነቱን ሰይለውጥ ወጣ ::
#በእመቤታችን ምልጃ አምኖና ተማምኖ አማልጂኝ ብሎ በሥሯ የተጠለለባት ሰው ግን እንዲሁ እንደ ኖህ መርከብ በቀደመ ግብሩ አይቆይም ንፉጉ ለጋሽ፣ጨካኙ እሩሩ ፣ ዘማዊው ድንግል ሆኖ ተለወጦ ይገኛል ስለዚህ እመቤታችን ከኖህ መርከብ በእጅጉ ትልቃለች ትበልጥማለች :: ዝም ብለን እንደ ሊቁ
......በመኑ ወበ አምሳለ መኑ ናስተማስለኪ........ እንበላት።
.............ይቆየን..............
እረድኤትና ቃልኪዳኗ አማላጅነቷም ለዘለዓለሙ ከኛ አይራቅ ...አሜን!
ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE
#ዓውደ ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
👆👆👆👆👆👇

ባለ ታሪክ ኃያሉ ሶምሶም
#ለፍቅር_የተከፈለ መሰዋህትነት
ሶምሶም ከተወለደ ጀምሮ በእራሱ ላይ ምላጭ አርፎበት የማያውቅ የእግዚአብሔር ኃይል በጸጉሩ ላይ ያደረበት እስራኤላውያንን ይጠብቁ ዘንድ ከተነሱ መሳፍንት መካከል ኃያሉ ናዝራዊ ሰው ነበር ::
ከዚህም በኋላ በሶሬቅ ሸለቆ የነበረች ደሊላ የተባለች አንዲት ሴትን ወደደ። የፍልስጥኤማውያንም መኳንንት ወደ እርስዋ ወጥተው፦ እርሱን ሸንግለሽ በእርሱ ያለ ታላቅ ኃይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛስ እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ የምናሸንፈው በምን እንደ ሆነ እወቂ፤ እኛም እያንዳንዳችን ሺህ አንድ መቶ ብር ሺህ አንድ መቶ ብር እንሰጥሻለን አሏት።
ደሊላም ሶምሶምን ይህ ከሰው ሁሉ ልዮ የሚያደርግህ የኃይል ምሥጢር ምንድን ነው ? ከወደድከኝ ንገረኝ እያለች ዕለት ዕለት ትነዘንዘው ጀመር ። መጻሕፍ ቅዱስ እንደውም ይህን ንዝነዛዋን እንዲ ሲል ይገልጠዋል “ዕለት ዕለትም በቃልዋ ነዘነዘችው አስቸገረችውም፥ ነፍሱም እስከ ሞት ድረስ ተጨነቀች”መሳ 16፥16
ሶምሶም ከደሊላ ምሥጢር ከሚያስወጣ ጥያቄዋ ለማምለጥ የራሱን ጥረት አድርጓል:: በእርጥብ ጠፈር ብታስሪኝ፣ በአዲስ ገመድም ብትቋጥሪኝ፣ የእራስ ፀጉሬን በችንካር ብትቸነክሪው ኃይሌ ከእኔ ይጠፋል እንደ ሌላም ሰው እሆናለሁ እያለ ምሥጢርም ሳያወጣ ደሊላንም ሳያጣ እስከ ጊዜው ለመቆየት ችሎ ነበር :: “ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሴት ግን በአጥንቱ ውስጥ እንደ ቅንቅን ናት።” ምሳሌ 12፥4 እንዲል መጻሕፍ አንተ፦ እወድሻለሁ እንዴት ትለኛለህ፥ ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም? ስታታልለኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኃይልህም በምን እንደ ሆነ አልነገርኸኝም አለችው። ዕለት ዕለትም በቃልዋ ነዘነዘችው አስቸገረችውም፥ ነፍሱም እስከ ሞት ድረስ ተጨነቀች።
ንዝነዛዋ የበዛበት ሶምሶም የልቡን ሁሉ ገለጠላት የኃይሉ ምንጭ ጸጉሩ እንደሆነና ጸጎሩን ቢላጭ ኃይሉ ከእርሱ እደሚርቅ ነገራት ደሊላም የልቡን ሁሉ እንደገለጠላት ባየች ጊዜ በጕልበትዋ ላይ አስተኛችው በተኛበትም፤ አንድ ሰውም ጠራች፥ እርሱም ሰባቱን የራሱን ጕንጕን (ቁንድላ) ላጨው። ልታዋርደውም ጀመረች፥ ኃይሉም ከእርሱ ሄደ።” ከተኛበት ቀስቅሳም ሶምሶም ሆይ ፍልስጤማውያን መጡብህ አለችው ተነስቼ እንደ ቀድሞ እሆናለው ቢል ኃይል ከእርሱ እርቆልና አንዱን በጡጫ ሌላውን በርግጫ ማለት ተሳነው::ሶምሶምም ለምርኮ ተዳረገ ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዓይኖቹን አወጡት፤ ወደ ጋዛም አምጥተው በናስ ሰንሰለት አሰሩት፤ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር። መሳፍ 16፥21
በጣም ያሳዝናል ሶምሶም ስለ ሴት ፍቅር ሲል ፍቅር እግዚአብሔርን አጥቶታል ኃይሉም ከእርሱ እርቆ ዐይኖቹ ወጥተው ለግዞትም ተዳርጓል
👉ወንድሞች ሶምሶምን ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር! ?
*ስለ ወደዳችዋት ሴት ምሥጢሩን ታወጡ ነበር?
👉እህቶችስ ደሊላን ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር?
*ለገንዘብ ብላችሁ ሶምሶምን ትከዱትና ታዋርዱት ነበርን?
❤ እርሶ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?
#ለነፃ_ሀሳብዎ_እነዚህን_ይጠቀሙ
👇👇👇👇
@Abenma
@YEAWEDIMERITE
🤦♀ደሊላና ሶምሶም ዛሬም በጸጸት ሆነው ሀሳቦቻችሁን እየጠበቁ ነው🤦♂
#ዓውደ_ምሕረት_የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
👆👆👆👆👆👆

Forwarded from ፅሐይ
እኔ ደሊላን ብሆን ለገንዘብ ብዬ አልክደዉም ምክንያቱም ብር አላፊ ጠፊ ነው ስለዚህ እሱን ከምክድ ገንዘቡን ቢቀርብኝ እመርጣለሁ
Forwarded from Deleted Account
ሰላም ለእናንተ የክርስቶስ ቤተሰቦች የእማምላክ ወዳጆች በያላችሁበት ሰላማችሁ ብዝት ይበል
እኔ ደሊላ ብሆን ለገንዘብ ብዬ ሶምሶምን አሳልፌ አልሰጠውም ፍልስጤማውያንም እጅጉን ቢያስቸግሩኝ ሊገድሉኝም ቢመጡ እንኳን ሶምሶን የእግዚአብሔር ሀይል ስላለው ይከላከልልኛል ።
ፀጋውን ለማወቅ ፈልጌ እጠይቀዋለሁ ቢነግረኝ ባነግረኝም ግን በምንም ምክንያት አሳልፌ አልሰጠውም ።