#ፍቅር_ይዞኝ_እንጂ
መች አስቤው እንደ ሥራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
ጭው ባለው በረሃ ውስጥ
መንከራተቴ ያለ እፎይታ
ቀጥ ባለው ተራራ ላይ
ላቤን ማፍሰሴ ጠዋት ማታ
መች አስቤው እንደ ስራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
የልጆቼ ዓይን በዓይኔ ላይ
ያለ እረፍት ሲመላለስ
ልቻለው ከሃገሬ አይበልጡም
እያልኩኝ የምንከላወስ
ዘመን በዘመን ሲቀየር
በዓል አውድ ዓመት ሲመጣ
ለእንጀራዬ ብዬ ነው እንዴ
ከበረሃ የማልወጣ?
ከዘመድ አዝማድ የማልበላ
ከአብሮ አደጎቼ የማልጠጣ
የያዘ ይዞኝ እንጂ
የሀገር ፍቅር----- የሚሉት ልክፍት
እኔ ሁለት ሆድ የለኝ
እስክሞት የሚንከራትት
መች አስቤው እንደ ሥራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
ላቤ በጀርባዬ ላይ
የጨው አምድ መስሎ እስኪታይ
ከእረፍት ከእንቅልፍ ተፋትቼ
የማጣው የቅጽበት ፋታ
ቀናትን በእግሬ የምኳትን
ጫማዬን ከእግሬ ሳልፈታ
ለእንጀራዬ ብዬ ነው እንዴ
ቀዝቃዛ ውሃ እየናፈቀኝ
ትኩስ መመገብ እያማረኝ
ጨዋማ ውሃ እየጠጣሁ
በድካም ጨው የሚያልበኝ
ለእጀራዬ ብዬ አይደለም
ርቄ ከመሃል ማዶ
በቀበሮ ጉድጓድ ሆኜ
ምሰማው የናቴን መርዶ
ለእንጀራዬ ብዬ አይደለም
በእህቴ ሰርግ የማልገኝ
በወንድሜ ህመም የማልመጣ
ከሃገሬ አስተሳስሮኝ እንጂ
ወታደር የመሆኔ እጣ
ለእንጀራዬ ብዬ አይደለም
የምቃጠል በበረሃ
የሚያነደኝ ቦምብ ፈንጂ
ቃልኪዳኔ ከሆነችው
ከሀገሬ ፍቅር ይዞኝ እንጂ
🔘ሻለቃ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
መች አስቤው እንደ ሥራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
ጭው ባለው በረሃ ውስጥ
መንከራተቴ ያለ እፎይታ
ቀጥ ባለው ተራራ ላይ
ላቤን ማፍሰሴ ጠዋት ማታ
መች አስቤው እንደ ስራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
የልጆቼ ዓይን በዓይኔ ላይ
ያለ እረፍት ሲመላለስ
ልቻለው ከሃገሬ አይበልጡም
እያልኩኝ የምንከላወስ
ዘመን በዘመን ሲቀየር
በዓል አውድ ዓመት ሲመጣ
ለእንጀራዬ ብዬ ነው እንዴ
ከበረሃ የማልወጣ?
ከዘመድ አዝማድ የማልበላ
ከአብሮ አደጎቼ የማልጠጣ
የያዘ ይዞኝ እንጂ
የሀገር ፍቅር----- የሚሉት ልክፍት
እኔ ሁለት ሆድ የለኝ
እስክሞት የሚንከራትት
መች አስቤው እንደ ሥራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
ላቤ በጀርባዬ ላይ
የጨው አምድ መስሎ እስኪታይ
ከእረፍት ከእንቅልፍ ተፋትቼ
የማጣው የቅጽበት ፋታ
ቀናትን በእግሬ የምኳትን
ጫማዬን ከእግሬ ሳልፈታ
ለእንጀራዬ ብዬ ነው እንዴ
ቀዝቃዛ ውሃ እየናፈቀኝ
ትኩስ መመገብ እያማረኝ
ጨዋማ ውሃ እየጠጣሁ
በድካም ጨው የሚያልበኝ
ለእጀራዬ ብዬ አይደለም
ርቄ ከመሃል ማዶ
በቀበሮ ጉድጓድ ሆኜ
ምሰማው የናቴን መርዶ
ለእንጀራዬ ብዬ አይደለም
በእህቴ ሰርግ የማልገኝ
በወንድሜ ህመም የማልመጣ
ከሃገሬ አስተሳስሮኝ እንጂ
ወታደር የመሆኔ እጣ
ለእንጀራዬ ብዬ አይደለም
የምቃጠል በበረሃ
የሚያነደኝ ቦምብ ፈንጂ
ቃልኪዳኔ ከሆነችው
ከሀገሬ ፍቅር ይዞኝ እንጂ
🔘ሻለቃ ወይን ሐረግ በቀለ🔘