አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፍሬሙ

ፎቶዋ
የወጣትነቷ
ግድግዳው ላይ ያለ
በኔና በሷ ፊት የተንጠለጠለ
ስንቱን አሳሰበኝ

የሚያምሩት ዐይኖቿ
የሚያምሩት ጉንጮቿ
የሚያምሩት ጭኖቿ
አሉ አሁንም አምረው
በፍሬም ውስጥ ታጥረው፡፡

አጠገቧ ሁኜ
ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ
እርጅናዋን አቅፋ
ለጋነቷን ሰቅላ
እኔም ተአምር ሳይ
«ነው» ሶፋ ላይ ኾኖ
«ነበር» ግድግዳ ላይ፡፡

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘