#ይድረስ_ላንተ
ጀግናዬ የቤትህ ድባብ
ቢናፍቅህ አውዳመቱ፣
ምንም ባይንህ ላይ ሽው ቢል
የዘመድ አዝማድ ጨዋታ
የቤተሰብ ናፍቆቱ፣
የኩበቱ ጭስ ሽታ
የዶሮ ወጥ አምሮቱ፣
የእህት የወንድም ትዝታ፣
ያባት ጠረን የናት ሽታ
የአደይ አበባው ውበት በለው
የገበያው ድምቀቱ፣
ከአብሮ አደጎች ጋር መቃለድ
አብሮ መብላት መጠጣቱ፣
እርግጥ ነው ይናፍቅሃል
አድባር ቀዬው አውዳመቱ፡
መቻል አንተ ልማድህ ነው
ናፍቆት ችለህ መክፈል ዋጋ፣
ማንም ይወቀው ልክህን
በዋዛ አይደለም ጀግናዬ
ሞተህልኝ ነው የምታነጋ፡፡
ቤተሰብ በማእድ ዙሪያ
ስለ አውደ አመት ሲስባስብ፣
አንተ ዛሬም በድንበር ላይ
ስለ ሰላም ነው የምታስብ፡፡
ልጆች ከአባቶቻቸው . . . የገና ስጦታን ሲቀበሉ፣
ጀግናዬ ያንተ ምስኪኖች . . . አይንህን ይናፍቃሉ፣
የሃገር የቁርጥ ቀን ልጅ
አንተ ወገን አፍቃሪ፣
አንተ ስለ ሰላም ሟች
አንተ ቃልህን አክባሪ፣
አንተ የሃገር ማገሯ
አንተ ስለ ህዝቧ ኗሪ፣
ከምትክ የለሽ ህይወት ላይ
እሷኑ ለድንበር ገባሪ፣
ደስ እያለህ ያበረከትክ
ነብስን የሚያህል ስጦታ፣
ጀግናዬ የሰውነት ልክ
ወታደር የፍቅር ጌታ፣
አውደ ዓመት ሲከበር በፌሽታ፣
በድንበርህ ላይ ዘብ ቆመህ
የሚያረካህ የወገንህ ደስታ።
በማን ሆነና መንጋቱ፣
የአዲስ ዘመን ጀንበር መታየቱ፣
ዘመን እንዲብትልን
ቀናችን መሽቶ እንዲነጋ፣
አንተ ነህ ከአምላክ ቀጥሎ
የከፈልክልን ውድ ዋጋ፡፡
በለሰለሰ መኝታ ጣፋጩን እንቅልፍ የጠገብነው፣
አሸዋ ልብሱ ወጥቶ አደር
እንቅልፍህን ጾመህልን ነው፣
ቀዝቃዛ ውሃ ጠጥተን
ስለ እርካታችን ስንናገር፣
የምትጎነጨውን ውሃ ግለት
የምታውቅ ኮዳህ ትመስክር፡፡
አዎ አዲስ ዘመን ባተ
እውነት ነው መስከረም መጣ፣
ክረምቱ አልፎ ተሻገርን
አየናት ምድር አጊጣ፣
ልዩ ነው ነብስ ያስደስታል
መስጠት መቀበል ስጦታ፣
የማይደበዝዝ ሃቅ ግን
ወታደር ያንተ ውለታ፡፡
እውነት ነው ወታደርነት
ስለ ሃገር ክብር መክፈል ህይወት፣
ስለ ህዝብ ፍቅር ኖሮ መሞት፡፡
ከተጋፈጥከው ተራራ
ካቋረጥከው ቆንጥር ጀርባ፣
አዲስ ፀሃይ እኛ አይተናልተ
በመስዋእትነትህ ታጅባ፡፡
በአንተ ነው አንተ ያገሬ ልጅ
ባንተ ነው ጨለማው የነጋ፣
ሃገርና ህዝብን አስቀድመህ
በከፈልክልን ውድ ዋጋ፡፡
ሃገር እስከ ጥግ ተጠራርቶ
አንዱ ለሌላው መልካም ሲመኝ፣
ስለ ሃገሩ ወጥቶ አዳሪው
አንተን ቢረሱህ አመመኝ፡፡
አድምጠኝ ጀግናዬ ጓዴ....
አንተ ባለህበት በረሃ
ባይኖርም እርጥብ ቄጠማ፣
ክትፎውን ከቁርጥ ባታማርጥ
ቀዝቃዛ ውሃን ብትጠማ፣
ወታደር ባንተ ልፋት ነው
መድመቁ በአል አውደ አመት፣
ለጥቁር አፈርህ ክብር
አፈር መስለህ የደከምክበት፡፡
እየሞትክ የምታቆማት ሃገር
ዛሬ ዘመኗን ስትቀይር፣
እንኳን አደረሰህ ልልህ ወደድኩ
ክብር ምስጋና ላንተ ይሁን
ለራስህ ያልኖርከው ወታደር፡፡
🔘ሻለቃ ወይንሐረግ በቀለ🔘
ጀግናዬ የቤትህ ድባብ
ቢናፍቅህ አውዳመቱ፣
ምንም ባይንህ ላይ ሽው ቢል
የዘመድ አዝማድ ጨዋታ
የቤተሰብ ናፍቆቱ፣
የኩበቱ ጭስ ሽታ
የዶሮ ወጥ አምሮቱ፣
የእህት የወንድም ትዝታ፣
ያባት ጠረን የናት ሽታ
የአደይ አበባው ውበት በለው
የገበያው ድምቀቱ፣
ከአብሮ አደጎች ጋር መቃለድ
አብሮ መብላት መጠጣቱ፣
እርግጥ ነው ይናፍቅሃል
አድባር ቀዬው አውዳመቱ፡
መቻል አንተ ልማድህ ነው
ናፍቆት ችለህ መክፈል ዋጋ፣
ማንም ይወቀው ልክህን
በዋዛ አይደለም ጀግናዬ
ሞተህልኝ ነው የምታነጋ፡፡
ቤተሰብ በማእድ ዙሪያ
ስለ አውደ አመት ሲስባስብ፣
አንተ ዛሬም በድንበር ላይ
ስለ ሰላም ነው የምታስብ፡፡
ልጆች ከአባቶቻቸው . . . የገና ስጦታን ሲቀበሉ፣
ጀግናዬ ያንተ ምስኪኖች . . . አይንህን ይናፍቃሉ፣
የሃገር የቁርጥ ቀን ልጅ
አንተ ወገን አፍቃሪ፣
አንተ ስለ ሰላም ሟች
አንተ ቃልህን አክባሪ፣
አንተ የሃገር ማገሯ
አንተ ስለ ህዝቧ ኗሪ፣
ከምትክ የለሽ ህይወት ላይ
እሷኑ ለድንበር ገባሪ፣
ደስ እያለህ ያበረከትክ
ነብስን የሚያህል ስጦታ፣
ጀግናዬ የሰውነት ልክ
ወታደር የፍቅር ጌታ፣
አውደ ዓመት ሲከበር በፌሽታ፣
በድንበርህ ላይ ዘብ ቆመህ
የሚያረካህ የወገንህ ደስታ።
በማን ሆነና መንጋቱ፣
የአዲስ ዘመን ጀንበር መታየቱ፣
ዘመን እንዲብትልን
ቀናችን መሽቶ እንዲነጋ፣
አንተ ነህ ከአምላክ ቀጥሎ
የከፈልክልን ውድ ዋጋ፡፡
በለሰለሰ መኝታ ጣፋጩን እንቅልፍ የጠገብነው፣
አሸዋ ልብሱ ወጥቶ አደር
እንቅልፍህን ጾመህልን ነው፣
ቀዝቃዛ ውሃ ጠጥተን
ስለ እርካታችን ስንናገር፣
የምትጎነጨውን ውሃ ግለት
የምታውቅ ኮዳህ ትመስክር፡፡
አዎ አዲስ ዘመን ባተ
እውነት ነው መስከረም መጣ፣
ክረምቱ አልፎ ተሻገርን
አየናት ምድር አጊጣ፣
ልዩ ነው ነብስ ያስደስታል
መስጠት መቀበል ስጦታ፣
የማይደበዝዝ ሃቅ ግን
ወታደር ያንተ ውለታ፡፡
እውነት ነው ወታደርነት
ስለ ሃገር ክብር መክፈል ህይወት፣
ስለ ህዝብ ፍቅር ኖሮ መሞት፡፡
ከተጋፈጥከው ተራራ
ካቋረጥከው ቆንጥር ጀርባ፣
አዲስ ፀሃይ እኛ አይተናልተ
በመስዋእትነትህ ታጅባ፡፡
በአንተ ነው አንተ ያገሬ ልጅ
ባንተ ነው ጨለማው የነጋ፣
ሃገርና ህዝብን አስቀድመህ
በከፈልክልን ውድ ዋጋ፡፡
ሃገር እስከ ጥግ ተጠራርቶ
አንዱ ለሌላው መልካም ሲመኝ፣
ስለ ሃገሩ ወጥቶ አዳሪው
አንተን ቢረሱህ አመመኝ፡፡
አድምጠኝ ጀግናዬ ጓዴ....
አንተ ባለህበት በረሃ
ባይኖርም እርጥብ ቄጠማ፣
ክትፎውን ከቁርጥ ባታማርጥ
ቀዝቃዛ ውሃን ብትጠማ፣
ወታደር ባንተ ልፋት ነው
መድመቁ በአል አውደ አመት፣
ለጥቁር አፈርህ ክብር
አፈር መስለህ የደከምክበት፡፡
እየሞትክ የምታቆማት ሃገር
ዛሬ ዘመኗን ስትቀይር፣
እንኳን አደረሰህ ልልህ ወደድኩ
ክብር ምስጋና ላንተ ይሁን
ለራስህ ያልኖርከው ወታደር፡፡
🔘ሻለቃ ወይንሐረግ በቀለ🔘