አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያንቺ_ፍቅር_ሰይጣን

#ያንቺ_ፍቅር_ሰይጣን
ካህን የማይፈራ
ፅናፅል ስዕሉን
ቀርቦ ያናናቀ
ያደረገ ተራ

#ያንቺ_ፍቅር_ሰይጣን
ቁርባን አስደንግጦት
ታቦት ያላራደው
የመንፈስ ነበልባል
የመንፈስ እሳቱ…
ስሜት የማይሰጠው

#ያንቺ_ፍቅር_ሰይጣን
በክፋት ተስሎ ፥ በስሎ የመጠቀ፤
በፀበል ፣ በፀሎት ፥ ቦታ ያለቀቀ።

#ያንቺ_ፍቅር_ሰይጣን
ዓይን የሚሰውር ፥ እንስት የሚጋርድ፤
ካንቺ ገላ ውጪ ፥ ሌላ ‘ማያስወድድ።
.
#ያንቺ_ፍቅር_ሰይጣን
ሀሳብ የሚሰልብ ፥ የመንፈስ ጠበኛ፤
በቅናት ጠፍሮ ፥ ሌት ‘ማያስተኛ።
.
#ያንቺ_ፍቅር_ሰይጣን
ደቁኖ የቀሰሰ!
ከሰዋራ ገዳም…
ዓለም በቃኝ ብሎ
ሙቶ የመነኮሰ።
.
#ያንቺ_ፍቅር_ሰይጣን
ይለቅ እንደሁ ብለው….
እምነት እየቀቡ ፥ በላይ ቢለውሱት፤
ሰይፈ ሚካኤል ፥ ተዓምረ ማርያም፤
እያነባነቡ ፥ በሽብር ቢያምሱት፤
እጣን አጫጭሰው ፥ ዜማ እያወረዱ፤
ቅዳሴ ቀድሰው!
ከበሮ ደልቀው !
ልቡንም ቢያርዱ ...............
“እንቢኝ ፥ አሻፈረኝ”! አለቅም እያለ፤
እንዲያ እንዳልተኩራራ……
እንዲያ እንዳልፎከረ ……….

አንቺን ከሌላ ሰው ፥ ያየሽ ‘ለት ደንብሮ፤
እኔን ለቆ ጠፋ ፥ ቀድሞ ከቀጠሮ ።

🔘ሚካኤል አስጨናቂ🔘
👍4