አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእሳት_እራት

በፍቅርሽ ነበልባል ነፍሴ ተቃጠለ
እቶኑ ውበትሽ ገጹን አከሰለ።
ቀልቤ ብትንትኑ ትርምስምሱ ወጣ
የልጅነት ወዜ በመውደድ ገረው።
ከዕልቆ ሥፍር ራቀ ፤ ባ'ንቺው ተመሽገ
ጕያሽ ሥር ተቀብሮ ፣ ካ'ለም ተሸሽገ።

አቤት ይኼ ልቤ . . .
ስትኼጂ ሲሟሽሽ ፣ ጠውልጎ ሲወድቅ
ስትመጪ ሲፈካ ፣ አብቦ ሲጸድቅ።
መከነ ንዳዱ ጠረንሽ አራሰው፤
ለምልሞ ጸደቀ ፤ ዙሪያሽን ሲያስሰው።

እናም ይኼ ልቤ . . .
ወጋገን ኾነችው ጸዳል እንዳለመ፣
ብርሃን ገላሽ ላይ ሲያርፍልሽ ከሰመ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘