አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
የሚከፍሉን
አልያም ደግሞ እሱ የዛሬውን አዳር ሂሳብ ከከፈለ የቀጣዩን እዳር ሂሳብ ሚስቱ ትከፍላለች፡፡ ፈረንጆት
ዘንድ የጾታ እኩልነት እና ግለኝነት እስከዚህ ድረስ እንደሆነ በፍጹም አልገመትኩም፡፡ በ5 ቀኑ የሌሊት
ቆይታዬ ያስተዋልኩት ያንን ነው
ሆ፡ a Problem shared is a problem halved) ከሚለው የራሳቸው
አባባል በተቃራኒ የቆመ a pleasure shared is a pleasure doubled የሚል ብሂል አላቸው

ለማንኛውም ጥንዶቹ የሚፈልጉኝ ለማህጸን ኪራይ ነው::”ሮዛ ካናዳ አብረሽን እንድትሔጅ እንፈልጋለን

በጣም ነው የወደድንሽ፡፡ ፈጣሪ ውበትና እውቀትን አሟልቶ ሰጥቶሻል፡፡ ስለዚህ ከእኛ እንድትለዬ አንፈልግም፡፡ ያ እንዲሆን ግን በአንድ የጋራ ጉዳያችን እንድትተባበሪን እንፈልጋለን፡፡ አንድ ችግር አለብን፡፡ ፍላጎቱ ካለሽ የጋራ ችግራችንን አንቺ መፍታት ትችያለሽ፣ እኛ ደግሞ ያንቺን መጠነኛ ችግር በከፊል እንፈታለን፡፡ ጥያቄያችን ቅር እንደማያሰኝሽ ተስፋ እናደርጋለን፡፡”

ሚስስ ዊልያም ልክ እንደዚህ ስትል ጥንዶቹ እየተሳለቁብኝ ነበር የመሰለኝ፡፡ እንደተመለከትኩት የገንዘብም፣ የእውቀትም፣ የስራም ሆነ የወሲብ ችግር የለባቸውም፤ ምርጥ የሚባል ወሲባዊ መጣጣመ እንዳላቸው ከአምስቱ ሌሊት የገስት ሀውስ ቆይታዬ ተመልክቻለሁ፡፡ ታዲያ እነዚህ ጥንዶች ሌላ ምን
አይነት ችግር ይኖርባቸዋል? እንዲያውም እነሱ አቅቷቸው እኔ የምፈታላቸው ችግር!ታዲያ ይሄ ሹፈት እና ስላቅ አይደለም? አዎ በወቅቱ ልክ እንደዚያ ነበር ያሰብኩት፡፡ የሚስቱን ሀሳብ ተከትሎ ሚስተር ዊልያም ቀጠለ፡፡

“ይሄውልሽ ሮዛ! ባለቤቴ ሜሊሳ መኻን ናት፤ መውለድ አትችልም፡፡ ሁለታችንም ልጅ እንዲኖረን አጥብቀን
እንመኛለን፣ ይህን ችግራችንን አይተሽ እንድትተባበሪን ነው:: ለውለታሽ ካናዳ መውሰድ ብቻ ሳይሆን
የምትጠይቂውን ክፍያም እንከፍላለን፡፡ እዚህ የቤተሰቦችሽን ህይወት ለዘለቄታው ቀይረሽ እኛ ጋር ካናዳ
ብትሄጂ ምን ይመስልሻል?”
ዊልያሞቹ የምሁር ጨዋነት እና ይሉኝታ እያጠቃቸው እንጂ “ማህጸንሽን አከራዪን! ካንቺ ማህጸን የወጣው
ልጅ በኛ ወላጅነትና ተንከባካቢነት ያድጋል እያሉኝ ነው፡፡በኃላ አንብቤ እንደተረዳሁት ይህን ነገር በነሱ
ቋንቋ surrogate mother ይሉታል፡፡

ያሳዝናል !ልተባባራቸው አልችልም፡፡ እነሱ አስቀድመው እንደገመቱት፣ እስከዚህ ድረስ የዘቀጠ የኅሊና ሽርሙጥና ውስጥ አልገባሁም፡፡ ምናልባት የተገኘሁት በችግር ከተጠፈነገና በርካታ እህትና ወንድም ካሉበት ሰፊ ቤተሰብ ውስጥ ቢሆን ኖሮ ለቤተሰቤ ስል ከባዱንና ፈታኙን ጥያቄያቸውን እቀበል ነበር
በቸልታና በስሜት ጡዘት ከማንም መናጢ ድሀስ ይወለድ የለም? ስንቷ ቆንጆስ ዲቃላ ትታቀፍ የለ ?
ጥሩው ነገር እኔ ከአንድ ራሴ ሕይወት ውጪ የማስብለት ልጅም ሆነ ቤተሰብ የለኝም፡፡ ዊሊያሞቹ በመደለያነት የተጠቀሙበትን ያህል የገንዘብ ችግርም የለብኝም፡፡ ዊልያሞቹን ጥያቄም
እንደማልቀበል እንደነሱ በስርአትና በጨዋ ደንብ ነግሬያቸው ሞቅ ባለ ሰላምታ ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናበትኳቸው፡፡

የመጨረሻ ውሳኔዬ እንደሆነ ሲያውቁ ፊታቸው የካናዳ ደመና መስሎ ነበር፡፡

#የኡስማን_እርካታ

ቦሌ ላፓሪዝያን ካፌ ውስጥ ተቀምጬ ከኔ ጀርባ የተቀመጡ ሁለት ወጣቶት ተከታዩን ወግ ሲያወጉ ሰማኋቸው፤

“እዳስ አበባችን ውስጥ ግን ከነጭ፣ከአረብ፣ከቻይናና እና ከአፍሪካዊ ጋር አብረው የሚታዩ ሴቶች
አልበዙብህም?ሴቶቻችንን ዜጎቹ እየተቀራመቱን ነው፡፡ይህ ጉዳይ አያሳስብህም?”

እኔ እንደውም ጥቅሙ ነው የሚታየኝ”

“ቺኮቻችንን ወስደውብን ምን አይነት ጥቅም ነው የሚታይህ?”

“ጉዳዩን ከአገር ኢኮኖሚ አንጻር ነው መመልከት ያለብህ ፍሬንድ፡፡ሴቶቻችን ልክ እንደ ቡናው፣አበባው እና ሰሊጡ ወደ አገራችን የሚገባውን የውጭ ምንዛሪ ይጨምራሉ"…

መላሹ የምር በሆነ ስሜት ይናገር ስለነበር ፈጅግታን አጭሮብኛል፡፡

የልጆቹ ስጋት እውነትነት እንዳለሁ አሰብኩ፡፡ ለምሳሌ ዑስማን ወደ ኢምፓየሩ የሚያስገባቸው ወፎች
ቁጥር በየዕለቱ ይጨምራል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ደንበኞቹ ቁጥራቸው በየጊዜው እያሻቀበ በመሄዱ ነው፡፡
በተለይ አረቦቹ በሀበሻ ሴት እያበዱ ነው፡፡ ኡስማንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከነጮች ይልቅ ለአረቦች ልዩ
ትኩረት እየሰጠ መጥቷል፡፡ «አረቦችን መበቀል እፈልጋለሁ›› የሚላት አባባል አለችው፡፡ እንደዚህ ሲል እየቀለደ አይደለም፡፡ የምሩን ነው፡፡ «የኛ ሴቶች ግርድና 24 ሰዓት ሽንት ቤት ሲያጸዱ የሚከፍሏቸው
500 ዲርሃም እንኳን አትሞላም፡፡ ይህ በምንም መመዘኛ ብዝበዛ ነው፡፡ አረብ ለሽንት ቤት ቂጡን ለማጠብ፣ ጡሃራ ለማድረግ ለሶፍት ብቻ በወር 3000 ዲርሃም ያወጣል፡፡ ከሶፍት ባነሰ ዋጋ እህቶቻችንን ይበዘብዛል፡፡ ከ «አብድ>> ወይም ባሪያ ለይተው እንኳ አያይዋቸውም እኮ፡፡እኔ ይህንን ብዝበዛ እታገላለሁ፡፡ እበቀላቸዋለሁ፡፡ ለአንድ አረብ ሴት ለማገናኘት የማስከፍለው15 ሺ ዲርሃም ነው፡፡ አረቦች ዋጋ ሲከራከሩኝ ለሰራተኞቻችን ስንት እንደሚከፍሏቸው እነግራቸዋለሁ፡፡ ይደነግጣሉ፤ ያልኳቸውን ይከፍሉኛል፡፡ ለገስት ሀውስ አገልግሎት የእጥፍ እጥፍ እቀበላቸዋለሁ፡፡ አንድ አረብን በበዘበዝኩ ቁጥር ሴከስ ከማድረግ የበለጠ
ልዩ እርካታ ይሰማኛል» ይላል፡፡
ንጉስ ዑስማንዑስማን ዘ ፒምፕ፤ለምን እንደሆነ አላውቅም እንዲህ ሲል እወደዋለሁ፡፡ ዉድድድ አደርገዋለሁ፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like ማድረግ እንዳይረሳ ከ 120 👍 በኋላ ቀጣዩ ክፍል ይለቀቃል

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍51