አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የአንድ_አፈር_አፈሮች

ፍቅራችንን ድንበር ወሰን ላይገድበው፥
ሁለት ክልል ላይመጥነው፥
መገዳደል ፍትህ ላይሆነው፥
በሽንፈትህ እሰይ ላልል፥
በሽንፈቴ እፎይ ላትል፥
ከቂም በቀር ፍቅር ላይበቅል፥
ልጅህ በእጄ ለምን ይሙት?
ልጄስ በእጅህ ለምን ትሙት?
እኔና አንተኮ የአንድ እናት ልጆች፥
ወንድማማቾች፥
የአንድ አፈር አፈሮች
ርስት አፈሩማ ይቅርም ከወደዚ ይሂድም ወደዚያ፥
ያውነው የኢትዮጵያ አንድ አፈር መጠሪያ፥
ወዲያ ካለው የቀድሞዋ፥
ወዲህ ካለው የስካሁንዋ፥
ግዳይ ጥዬ በልጅህ ደም በጀግንነት ላልጠራ፥
ግዳይ ጥለህ በልጄ ደም ላትፎክር ላታቅራራ፥
ወንድም ገድለው ላይፎክሩ፥
ጀብዱ ሰርተው ላይኩራሩ፥
የሀዘን ሙሾ ልዘምሩ፥
እንደ ማህተብ የእምነት ክር ፍቅር ድሩ ላይበጠስ፥
በሀዘናችን ላትዘፍኑ በሞታቹ ላንደንስ፥
ስውር አይሁን ነጭ ሴራው ደስ አይበለው የጠላት ነብስ፥
ልጅህ አይሙት በልጄ ጣት፥
ልጄም አይሙት በልጅህ ቀስት፥
እኔና አንተኮ ከዘመናት በፊት፥
በታሪክ በሀይማኖት፥
በባህል በትውፊት፥
በደስታ በችግር፥
ስም የሌሽ ስመጥር፥
በጋሻና በጦር፥
ጀብደኛ ባላገር፥
የአንድ አያቶች ዘር፥
የሁለት አፈር ሰፈር፥
ስምየለሽ በጥጋብ፥
ስመጥር በረሀብ፥
እያሉ ሲተቹህ እያሉ ሲተቹን፥
በሙጫ ስድብ አጣብቀውን፥
ሲተቹህ መተቸት ሲተቹን መተቸት፥
እንዳለ ስናውቀው እንዳለ ስታውቁት፥
በአንድ እናት ተወልደን፥
በሁለት አባት አድገን፥
አንድ ውሀ ተራጭተን፥
አንድ አፈር አቡክተን፥
ቃታ ስንሳሳብ እሺ ላይለው ልብህ ደስ ላይለው ልቤን፥
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን?
እኔና አንተኮ የአንድ እናት ልጆች፥
ወንድምና እህቶች፥
የአንድ አፈር አፈሮች
እናም ወንድም ስማኝ ልስማህ
ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከእኔ ፀብ ሲያቃባ፥
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ፥
በሞትህ ደስ ላይለኝ ወስጥ ልቤ እዥ ሊያነባ፥
የእናቱን ልጅ ልጄ ገድሎ ላያሰማ ጉሮወሸባ፥
ፍቅር እንጂ ግድባችን ወሰን አይኑር የደም ካባ፥
ይልቅስ ልንገርህ፥
ኩራቴ ኩራትህ፥
ታሪኬ ታሪክህ፥
የሚያመፃድቀኝ የሚያመፃድቅህ፥
የኔም የአባቴ ነው ያንተም የአባትህ፥
ከቢዘን ባስቀድስ፥
ከግሸን ብትሰልስ፥
ባክሱም ብትኮራ፥
ብሸልል ባስመራ፥
ያንተአባት አባቴ፥
አባቴ አባትህ፥
የሚያመፃድቀኝ የሚያመፃድቅህ፥
ታሪኬ ታሪክህ፥
መሆኑን ስናውቀው መሆኑን ስታውቁት፥
በደምና ባጥንት፥
በስጋ በጅማት፥
በታሪክ በትውፊት፥
መንታ ናቸው ሲሉን፥
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን?
በብቀላ ፀፀት በቀር፥
ወንድም ጥሎ ላይፎክር፥
ጀግና ተብሎ ሜዳይ ላይኖር፥
በእናቴ ልጅ በመጨከን እሺ ላይለኝ የልቤ በር፥
ወንድ ልጄን ግዳይ ጥለህ ላይፈታ የደምህ ስር፥
ካንድ ደብር አድገን፥
በአንድ አስቀድሰን፥
አንድ ዳዊት ደግመን፥
ካንድ መስጊድ ኖረን፥
በአንድ ሰላት አድገን፥
አንድ ቁርአን ቀርተን፥
እኮ እንዴት እኔና አንተ ዛሬ እንዲህ እንጫከን?
ለጉዳትህ ተሰውቼ፥
ላንተክብር ብዙ ሞቼ፥
ስላንተ ነፃነት ካገርህ ደሜ አለ፥
በናቅፋ ተራሮች እቅፍ የታዘለ፥
መጎዳቴን እምቢ ብለህ፥
ስለክብሬ ተሰውተህ፥
የሰጠህኝ ክቡር ደምህ፥
ያንተም አጽም አድዋ አለ፥
ለኢትዮጵያ ነፃነት ስለኔ የዋለ፥
መንታ ናቸው ሲሉን፥
ፍቅር ናቸው ሲሉን:
እያወቁት ልቦናችን፥
ሁለት ክልል ላይመጥነን፥
ድንበር ወሰን ላይገድበን፥
መገዳደል ፍትህ ላይሆነን፥
በሽንፈትህ ስንዘምር በለው ያሉህ ሊታዘቡን፥
ነጭ ሴራ ወጣው ሊሉን፥
ስጋ ክንድህ ሲደማብህ፥
ልቦናችን ሊያዝንብን፥
በአለም ዜና ድላችንን ደምጥማት ነው ብለው ሊሉን፥
ልጅህ በጄ ለምን ይሙት?
ልጄም በእጅህ ለምን ትሙት?
ስማኝ ወገን ደስ አይበለው ነገር ሰሪ አንተን ከኔ ፀብ ሲያቃባ፥
ስውር አይሁን ነጭ ሴራው የሸረበው የሞት ደባ፥
እንዘምር ባንድ እንዝለል ወሰን አይኑር የደም ካባ፥
እናም በሞቱት ሞት፥
እኔና አንተ አንሙት፥
እኔና አንተማ የአንድ እናት ልጆች፥
የአንድ አፈር አፈሮች፡፡

🔘ኤፍሬም ስዩም🔘