አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የታረሙ_ነፍሶች


#በአሌክስ_አብርሃም

እጅጋየሁ ማታ ሦስት ሰዓት ላይ በቤታችን ስልክ ደወለች ማዘር ጋር አስራ አምስት ደቂቃ የሚሆን ሲያወሩ ቆዩና ጥግብ ሲሉ ማዘር እንዲህ አለች፣ “አብርሽ ስልኩ ያንተ ነው ና አናግራት…ቶሎ በል እንዳይቆጥርባት እጅግዬ ናት፡፡”

እጅጋየሁ ሰባትና ስምንተኛ ክፍል አብረን የተማርን ጓደኛዬ ናት፡፡ ይሄው እስካሁንም እንኳን ከኔ
ጋር፣ ከቤተሰብ ጋርም ጥብቅ ወዳጅ ሆና ቀጥላለች፡፡ በተለይ ማዘር ጋር በከፉ በደጉ ይጠያየቃሉ፤እንደውም እውነቱን ለመናገር እጅጋየሁ ከእኔ ይልቅ የእናቴ ጓደኛ ነው የምትመስለኝ፡፡ ከልቧ ጥሩ ልጅ ናት፡፡ የታመመ አሳዳ የምትጠይቅ፣ ሃዘን ካለ ከሃዘንተኛው ሳትለይ የምታፅናና (ጊዜው እንዴት ይለቃታል?) ሰርግም ካለ የጥሪ ካርድ ከማዘጋጀቱ ጀምሮ እስከቤተሰብ ቅልቅል ጎንበስ ቀና ብላ የምታዳድር ሌሎችን የማገልገል ፀጋ ያትረፈረፈላት ልጅ ናት፡፡ እች ናት እጅጋየሁ !

እኔ ታዲያ ወሬዋ ይሰለቸኛል፡፡ ይንዛዛል፡፡ ማቋረጫ የለውም (ስለእጅጋየሁ ወሬ ለእናቴ ስነግራት ግን 'ይንዛዛል አልልም፣ የምለው “ትንሽ ወሬዋ ዘለግ ይላል” ነው፡፡ እናቴ ታዲያ እንዲህ
አሳምሬም ነግሬያት ትበሳጭብኛለች፣ ሂድ እባክህ ወሬኛ ! ዝም ብለህ ወረቴ አለቃ አትልም…ዘለግ አጠር !! ሆዷ ክፋት የለውም፤ ውስጧ ያለውን ሁሉ ስለምታወራ ነው፣ እንደሌሎቹ ነገር በሆዷ የምታብላላ “ማሽንከ' አይደለችም፡፡”

እንግዲህ “ሌሎቹ” እና “ማሽንክ” የሚሉት ቃላት ዝምተኛዋንና የአሁኗን ፍቅረኛዬን 'ቤዛን ኢላማ ያደረጉ የእናቴ ጥይቶች ናቸው፤ እናቴ ቤዛን አትወዳትም፡፡ ከእጅጋየሁ ጋር እንድንገባ
ነበር ፍላጎቷ፡፡ ምን ያደርጋል፣ እጅጋየሁም አይታኝ አይታኝ አገባች፡፡ (ኧረ እንዲያውም የዛሬ
ስድስት ወር አካባቢ 'ወለድኩ ብላ ማዘር ሄዳ አይታታለች፡፡) እኔም ከቤዛ ጋር ፍቅር ጀመርኩ፡፡

ከስምንተኛ ክፍል ወደ ዘጠኝ አልፌ ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ስዘዋወር እጅጋየሁ ደገመችና
እዛው ስምንተኛ ከፍል የተማርንበት ትምህርት ቤት ቀረች፡፡ ታዲያ ልክ መስከረም ገብቶ ትምህርት ስንጀምር ደብዳቤ ፃፈችልኝ፡፡ ደብዳቤዋ ላይ መቼም የማልረሳው ግጥም ነበር፡፡

የባህርዳር ቅጠል ዳርዳሩ ለስላሳ፣

ተለያየን ብለህ እንዳንረሳሳ፡፡

እኔም ያለሁ አዲስ አበባ እሷም ያለች አዲስ አበባ፣ “ባህርዳር ድረስ ሄዶ ቅጠል የሚያስበጥስ፣
ሙሾ የሚያስወርድ ምን ጉድ ተፈጠረ?” አልኩና ተገረምኩ፡፡ እጅጋየሁ ነገረ ስራዋ ሁሉ የትልቅ
ሰው ነበር ፤ ያኔ ትልቅ ሰው ማለት ዛሬ ላይ አካባጅ የሚለውን ቃል ይተካል፡፡

ይሄው ዛሬ ደግሞ ደወለች፡፡ መቼም የደወለችበት ምክንያት ወይ የታመመ አልያም የሞተ
ሰው ቢኖር ነው፡፡ ሁለቱም ግምቶቼ ልክ ካልሆኑ ግን የሚያገባ ጓደኛችን አለ ማለት ነው፡፡

“አንተ…ወይ የሰው ነገር፡፡ በቃ እንዲህ በዋል ፈሰስ ሆነህ ቀረህ ? ምን ይሻልሃል ? ወለድኩ
ብዬ አፍ አውጥቼ ተናግሬ 'ማሪያም ትማርሽ? ማንን ገደለ ?”

“አይ…ኧ…” አፍሬ ነበር፡፡

.
“ተወው ተወው… ደህና ነህ ግን ? ስራ ጥሩ ነው ? ቤዚዬስ እንዴት ናት ? ባለፈው መንገድ ላይ አግኝቻት ጉንፋን ያዘኝ ብላ፣ ተሸላት ? ውይ የሷ ነገር በሽታ አትችልም እኮ ሂሂሂሂ የትኛውን ልመልስ ? ትቀጥላለች፡፡ “አብርሽ ልጄ አለቀሰችብኝ፣ ቶሎ ጉዳዩን ልንገርህ.…ቲቸር በለጠ እኮ ሞቱ.."

“ምን?”

“ይሄውልህ ዛሬ ከረፉ፡፡ ነገ ሥላሴ ነው ቀብራቸው፣ ልንገርህ ብዬ ነው፣ ከተመቸህ ብቅ በል
አብርሽ ...እባክህ ከሰው አትለይ…"

“ትቀልጃለሽ በዚህማ አይቀለድም፡፡ ለቲቸር በለጠ ቀብር ….ሞት አልቀርም ለምን ሺ ስራ ጥንቅር አይልም" አልኩ፡፡

“ግን ምን አገኛቸው በናትሽ.…?”

“ሚስታቸው…አንገብግባ ገደለቻቸው፡፡”

“አትቀልጅ ባክሽ”

“እመቤቴን ! በስተርጅና እንዲት እሳት አግብተው፣ ቀን ምድረ ውሪ ጋር ሲዳረቁ ውለው ሲገቡ
እሷ ደግሞ ማታ ከቤት በምላሷ ትጠብሳቸዋለች፡፡ በቃ ሳይደላቸው ድፍት አሉትና አረፉ

ከንፈሯን መጠጠች፡፡
“የሚስት ምላስ ቢደፋ ኖሮ ቢኒ ገና ድሮ…" ቢኒ ባሏ ነው፡፡
“አትሞጣሞጥ አንተ! እኔይቱ ልጅት!” ሳቋ ይቀድማታል፡፡ ነገ መምህር በለጠ ቀብር ላይ ልንናኝ
ተቀጣጥረን ተለያየን፡፡

ምንጊዜም የአማርኛ ክፍለጊዜ ሊጠናቀቅ ሲል አሮጌ የሸራ ቦርሳቸውን ከፍተው በስርዓት ከተሰደሩ ወረቀቶች መሐል አንድ በካኪ ወረቀት የተሸፈነ ትልቅ መፅሐፍ የሚያወጡ፣ ከወገባቸው በመጠኑ ጎበጥ ያሉና ትንሽ ዘርፈፍ ያለ ቅጠልማ ሹራብ የሚለብሱ እድሜያቸው ወደ ሃምሳ ዓመት
የሚሆን ሰው - መምህር በለጠ !!
ተማሪዎቻቸው መልስ ስንመልስ ትናንሽ ዓይኖቻቸውን ጠበብ አድርገው በጥሞና ሲመለከቱን
በዓይናቸው የሚያዳምጡን ይመስለን ነበር፡፡ መምህር በለጠ !! በመምህር በለጠ ከፍላ ጊዚ ደስታችን ፊታችን ላይ ይንበለበላል፡፡ የማይወዳቸው ተማሪ አልነበረም፡፡ መስፍን እንኳን
አምስት 'ፔሬድ ዘግቶ' እሳቸው ክፍለ ጊዜ ቢሞት አይቀርም፡፡

እንደውም አንድ ቀን በቲቸር በለጠ ክፍለ ጊዜ ለመታደም በአጥር ዘሎ ሲገባ ተይዞ ወላጅ ጠራ፤ የመስፍን አባት፣ “ይሄ የልጄን የትምህርት ፍቅር ነው የሚያሳየው፣ ዘሎ ሲወጣ አልተያዘም ዘሎ ሲገባ እንጂ" አሉ፡፡ መስፍን ከግቢ ውጭ የበላው ፓስቲ የዘይት መሃተሙን ከንፈሩ ላይ እንዳተመበት በቲቸር በለጠ ክፍለ ጊዜ ከተፍ ይላል ያውም ፊት ወንበር ላይ ! በሒሳብ
ከፍለ ጊዜ መስፍን ፊት ወንበር ሂድ!” ከሚባል ሞያሌ ድረስ በባዶ እግሩ ቢሄድ ይሻለዋል፡፡

...በካኪ ወረቀት የተሸፈነው መጸሐፍ ይከፈታል፣ “ፍቅር እስከ መቃብር” ነው ! በመምህር በለጠ ሊተረክ ተከፈተ፡፡ ምድረ ማቲ ከይናችን፣ አፋችን አብሮ ተከፈተ፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር ተነስቶ መምህር በለጠን አለማንሳት፣ ከመጸሐፉ ላይ በዛብህን ከመርሳት አይተናነስም፣
እንደውም ፍቅር እስከ መቃብር ገለጥ ገለጥ ቢደረግ፣ በዛብህ ሰብለ ወንጌል..ጉዱ ካሳ.መምህር
በለጠና…ፊታውራሪ መሸሻ እኩል የመጸሐፉ ገፀ-ባህሪያት ሆነው የሚገኙ ይመስለኛል፡፡

በሚያምር ድምፃቸው ትረካውን ይጀምራሉ፡፡ ከዝምታችን ብዛት የልብሳችን ቱማታ ይሰማል
ጭጭ..መምህር በለጠ በትረካቸው መሐል የግል አስተያየታቸውን ይጨምራሉ፡፡ አንዳንዴ አስተያየቱን ጣል የሚያደርጉት በሚተርኩበት ድምፅና ፍጥነት ስለሆነ አስተያየቱን ከታሪክት መለየት ያዳግተናል ፤ ቢሆንም አስተያየቱን የታሪኩ ያህል እንወድደዋለን፡፡
አንደ ፊታውራሪ እየጎደሩ፣ እንደ በዛብህ እየተቅለሰለሱ፣ እንደ ሰብለ ረጋ ብለው፡ እንደ ጉዱ
ካሳ እያፌዙ እና እያሸሞሩ፣ እንደ ሃብትሽ ይመር እየተቆናጠሩ፣ እንደ ቄስ ሞገሴ እየተሽቆጠቆጡ
በግርምት አስጥመውን..እያለ ኪሊሊሊሊሊሊሊሊ ይላል ከፍለ ጊዜው ማብቃቱን የሚያረዳው
ደወል፡፡ ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ…ኤጭጭ! በየአፋችን እንጋጫለን፡፡
ቲቸር መጻሐፉን ደጋግመው ደጋግመው ስላነበቡት የሚበልጠውን በቃላቸው ነበር የሚወጡት፤
እያነበቡ ድንገት በመሐል አንዱን ወይም አንዷን ተማሪ ይጠራሉ፣

"ሃና"
እቤት ቲቸር!” ድንገት በመጠራቷ ደንግጣ ታፈጣለች፡፡ የከፍላችን ጎበዝ ተማሪ ናት ሃና…
“የሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎት ምንድን ነው ?” ይጠይቋታል፡፡
“ምግብ…ልብስ…መጠለያ..” መለሰችው እንላለን እኛ በሹክሹክታ፡፡ ገና ትላንት ነው አካባቢ ሳይንስ መምህርታችን ያስተማረችን፡፡
👍22