#የቀን_ቅዠት
ደመ ግቡ ፣ ቀይ ሴት
የመልኬ ገጽ ፣ ፍኩ ሐሤት
በእይታ አፍታ ፣
በብልጭታ ፍጥነት . . .
ከዐጸዴ መጥታ ፣
ድንግዝግዝ ፍዝ ቀን ፣ በፈገግታ ጠርቶ
ወጀብን የሚያቆም . . .
የሰመመን ዓለም ከቤቴ ተገኝቶ።
ጀንበርን ሸሽጋ ፣ ጨረቃዋን ጋርዳ
በድንገት መሽጋ ከዕልፍኜ ጓዳ።
በሻማ ተስላ . . .
ሸማ ተሸልማ ፣ ተገልጣ በ'ኔ ዐይን
አበባ ታቅፋ ፣ ጽዋ ሙሉ ወይን ፣
(. . . ከዕቅፌ ገባች . . )
ማእዱን ተቋደስን ያብሮነትን መባ
በቅጽበት ደመኩኝ ፣ በቅጽበት ተውባ
ድንገት ተሰለበች !
እኛነት ለለበች።(ዋሸች,አታለለች)
( ምን ነበረ የኾነው . . . ?)
በቀን በጠራራ ሳልም የነበርኩት ?
በክፍልፋይ ሰከንድ እያየው የዋልኩት ?
እኮ ምን ነበረ? ...
ልፈታው ቸገረኝ !
ቅኔው ግራ ገባኝ ተመሳጥሮ ሕልሜ
ተሠፋኹ ፣ ተቋጠርኩ ፤ በቀን ሐሳብ ቀኔ።
ለማላውቃት ውብ ሴት . . .
ፀምን ሕልሟ ብኾንም ፣ ሕልም ብትኾን ለ'ኔ፤
ያልታኖረ ሕይወት . . .
የሐምሌ ፀሐይ ነው የክረምት ምናኔ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
ደመ ግቡ ፣ ቀይ ሴት
የመልኬ ገጽ ፣ ፍኩ ሐሤት
በእይታ አፍታ ፣
በብልጭታ ፍጥነት . . .
ከዐጸዴ መጥታ ፣
ድንግዝግዝ ፍዝ ቀን ፣ በፈገግታ ጠርቶ
ወጀብን የሚያቆም . . .
የሰመመን ዓለም ከቤቴ ተገኝቶ።
ጀንበርን ሸሽጋ ፣ ጨረቃዋን ጋርዳ
በድንገት መሽጋ ከዕልፍኜ ጓዳ።
በሻማ ተስላ . . .
ሸማ ተሸልማ ፣ ተገልጣ በ'ኔ ዐይን
አበባ ታቅፋ ፣ ጽዋ ሙሉ ወይን ፣
(. . . ከዕቅፌ ገባች . . )
ማእዱን ተቋደስን ያብሮነትን መባ
በቅጽበት ደመኩኝ ፣ በቅጽበት ተውባ
ድንገት ተሰለበች !
እኛነት ለለበች።(ዋሸች,አታለለች)
( ምን ነበረ የኾነው . . . ?)
በቀን በጠራራ ሳልም የነበርኩት ?
በክፍልፋይ ሰከንድ እያየው የዋልኩት ?
እኮ ምን ነበረ? ...
ልፈታው ቸገረኝ !
ቅኔው ግራ ገባኝ ተመሳጥሮ ሕልሜ
ተሠፋኹ ፣ ተቋጠርኩ ፤ በቀን ሐሳብ ቀኔ።
ለማላውቃት ውብ ሴት . . .
ፀምን ሕልሟ ብኾንም ፣ ሕልም ብትኾን ለ'ኔ፤
ያልታኖረ ሕይወት . . .
የሐምሌ ፀሐይ ነው የክረምት ምናኔ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘