አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፍቅር ነው #የራበኝ

ደህና ነኝ እንዳልል
ደህንነቴ ጠፍቷል ፣
አሞኛል እንዳልል
ይሄው ፊቴ ፈክቷል ።
ሰው ሲያየኝ ጤነኛ ፣
ውስጤ በሽተኛ ፣
ቆይ ምን ብየ ላውራ
ሰሚ ሰው አግኝቼ ፣
በልቤ ጠራ ውስጥ
የትኛውን ትቼ ፣
*
አይቶ በሚፈርድ
ጆሮ ጠቢ ምላስ በሞላበት ሀገር ፣
ለየትኛው ሰሚ
ለየትኛው ሀኪም ህመሜን ልናገር ።
ከማንነት በላይ ፣
ከምንነት በላይ ፣
ምን ቃል ሊተነፈስ ?
በሽፋን መለኪያ
ምን እውነት ሊታፈስ ?
*
ፍቅር ነው የራበኝ..
እሱ ነው ያመመኝ ..
የሀገሬ መሬት ሰው እያካሰሰ ፣
ሰው እያናከሰ፣
የሀገሬ ቋንቋ
ዘር እያስቆጠረ ፣
ክልል እያጠረ ፣

ያዳም የ አብራክ ክፋይ
ሰውነት ቀረና ፣
በጎሳ በብሄር
ታጥሮ ህልውና ፣

በሽብር አይምሮ
ሀገር ይታመሳል ።
ለማይጠቅም አለም
ንጹህ ደም ይፈሳል ።
ክብር የ ሰው ስጋ
በግፍ ይቆረሳል ።
አፍ አየቀደመ
የህሊና ደወል
መሰማት ተስኖት ፣
የአምላክ ቃል ይፈርሳል ።
*
ይሔው ነው ህመሜ

የእድሜያችን ጣሪያ
ሰማኒያ ላይሞላ ፣
በሳር በቅጠሉ
ባፈር ስንባላ ፣
እኔ ነኝ የኔ ነው ፣
ማንነቴ እንትን ነው ፣
የሚል እድር ፈላ ።
በሉ እስኪ ንገሩኝ
ማንነት ምንድን ነው?
ምንነት የቱ ነው ?
*
ሰው ከመባል ወዲያ
ምን ትርጉም ተገኝቶ ?
ከአምላክ ፍጡር ውጭ
ምን ጠላት መጥቶ ?
*
ምንድን ነው ነገሩ ፣
ዝንትአለም መናከስ
ደምበር እያጠሩ ፣
በመግባቢያ ቋንቋ
በትውልድ ቀየ ዘር እየቆጠሩ ፣
ምንድን ነው ?ዘር መቁጠር
ዘር ማሳለይ እንጅ
ሰው ላይ ምን ያደርጋል ፣
ማን በሀሩር ደርቆ
ማን በዝናብ ያድጋል?
*
አመሉ ነው እንጅ ፣
ሞኝነት ነው እንጅ፣
ጥንትም ተፈጥሮውን
ሰው በአምላክ ካመነ፣
ማን ሀባሻን መርጦ
ማን ፈረንጅ ሆነ ?
ከግዜሩ ሆኖ አንጅ
ፍጥረት የተሰጠ ፣
ይሁንልኝ ብሎ
ማን ፆታ መረጠ ።
*
ከአፈር ተፈጥሮ
አፈር የሚሆን ሰው ፣
ከአፈር ጋር ታግሎ
አፈር የሚቆርሰው ፣
ምነው? ይሄ ትውልድ
ከራስ የዘለለ ማስተዋል አነሰው ።
*
ይገርማል ...
በማለዳ ፀሀይ
በምሽት ከዋክብት ቀን እየተዋጀ፣
ህዝቤ አንደጎበጠ
ቅን ሆኖ ቀን ሳያይ ሰማኒያውን ፈጀ ።
ፍቅር ነው የራበኝ ...........
*
03/02/2011
2:00pm
🔘ሳሙኤል አዳነ🔘

ከቻናሉ ተከታታይ የተላከ
ስለግጥሙ ያሎትን አስተያየት @Sam2127 አድርሱት