ጠይቄው ግን አላውቅም፡፡
ልክ 7:30 ሲል በጊዎን ሆቴል ተገናኘን ኡስማን ላይ ቀጠሮ ማርፈድ የማይታሰብ ስለሆነ ደንበኛዬን ሶልን ደውዬለት በኮንትራት እንዲያደርሰኝ አደረኩ፡፡ ኡስማን ፈረንጅ ነው፡፡ አያረፍድም፡፡ እኛ ወፎቹ ካረፈድንበት ያቺ መሰሪ ፈገግታውን ብልጭ አድርጎልን ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኖ አጫውቶን ይሄዳል
ነገር ግን ለሁለት ወር ይቀጣናል፡፡ ምንም ዜጋ አያገናኘንም። ሳንቲም ሲጠርብን ቅጣት መሆኑ ይገባናል ይቅርታ እንጠይቀዋለን፡፡ ትንሽ አሽቶ ይታረቀናል ስለዚህ ኡስማን ላይ ማርፈድ የእንጀራ ገመድን በገዛ ቅብጠት እንደመበጠስ መሆኑን ሁሉም ወፎቹ አሳምረን እናውቃለን፡፡
እንደወትሮው ተሸቀርቅሯል፡፡ እሱ ምን ሀሳብ አለበት፣ ሁልጊዜም በምርጥና ዘመነኛ አልባሳት እንደዘነጠ ነው፡፡ አገር ውስጥ ልብስ ገዝቶ አያውቅም፡፡ ዱባይ ለስራ ጉዳይ ሲሄድ ሻንጣ ሙሉ ልብስ
ሸክፎ ይመጣል፡፡ መዘነጥ ያውቅበታል፡፡በተፈጥሮው ርካሽ ነገር ኣይወድም፡፡ ሰው አስተሳሰቡን ነው የሚመስለው አስተሳሰቡ ተልካሻ የሆነ ሰው ነው ተልካሻ ነገር የሚለብሰው” የሚል ፍልስፍና አለችው።
"መጽሐፍ በሽፋኑ አይለካም " የሚል ሰው ያናድደዋል፡፡ ጥሩ መጸሐፍ ከሆነ ጥሩ ሽፋን ሊበጅለት ይገባል ባይ ነው ለምሳሌ ራሷን የማትጠብቅ ሴት በጣም ይጸየፋል፡፡ የማርሸትን ከስራ ያባረራት
ከእለታት አንድ ቀን የአይናር አይቶባት ነው፡፡ «በምድር ላይ አንድ ጊዜ የሚኖር ሰው ቢችል ጥሩ ነገር ብቻ መልበስ ይኖርበታል» ይላል፡፡
ጉንጬን ሳመኝ፤ ሮዝ! ዛሬ በሁለት ደቂቃ ተቀድመሻል፤ለዚህ ማክያቶ ትቀጪያለሽ” ብሎኝ ደማቅ ፈገግታውን ለኮሰ፡፡ገና ከመቀመጡ ስልኩ አቃጨለች።
“እሺ የኔ እመቤት! እሺ…ችግር የለውም…ልክ ነሽ…ገብቶኛል…ስንት መኪና አገኛችሁ ታዲያ?”
የሴቷ መልስ የኡስማንን ብርሃናማ ፊት ደመና አለበሰው፤ኡስማን በንዴት ፊቱን አጨፈገገ፤ፊቱ ጨፍግጎም ፈገግ ማለትን ያውቅበታል፡፡
“ይገባኛል የኔ እመቤት! ሆኖም የኔ ሰዎች የሊቢያ ልኡካን ናቸው፡፡ ለኪራይ ከመደበኛው ዋጋ ቢያንስ አራት እጥፍ ይከፍላሉ፤… ይገባኛል.ይገባኛል…ጥር ወር የሰርግ ወር እንደሆነ አውቃለሁ፤…ኖ
ኖ….እንደሱማ አይሆንም…እንደሱማ ከሆነ ለሰርግ የታሰቡትን መኪኖች ለምን ለቀሩት የሊቢያ ልኡካን
አታከራዩዋቸውም ታዲያ ?”
ከደቂቃዎች በኋላ ኡስማን ተረጋጋ፤በአውራ ጣቱ እና በአመልካች ጣቱ ጉንጬን በስሱ ቆንጠጥ
አደረገኝ፡፡ ዳግመኛ ፈገግታውን ለኮሰ፡፡
ምንድነው ነገሩ ሰርግ ያለብህ ትመስላለህ.…ልትሞሸር ነው እንዴ ኡስማን?»
አፍሪካ የምትባል ነጭናጫ ሴት አለች…ሰሞኑን ልትዳር ነው…እኔ ደሞ ሚዜዋ ነኝ፡፡»
«ምንድን?»
“ሮዚ ሰሞኑን እንቅልፍ በቅጡ እንኳ አልተኛሁም፡፡ ከኢትዮጵያ መንግስት በላይ ነው እየሰራሁ ያለሁት…እውነቴን ነው፡፡”
እኛን ትተህ ደሞ የሰርግ መኪና ማከራየት ጀመርክ…?ስማማ… እኔ ሳውቅክ እኛን ባሎች ላይ እየላከ
ትዳር ማፋታት ነበር እኮ ስራህ...አሁን ደሞ ማጋባት ሆነ?"
ኡስማን ተንከትከቶ ሳቀ፡፡ ሳቁ እኔም ላይ ተጋባብኝ፡፡
ይገርምሻል ሮዚ ልጆታ የደወለችው ከሀምኔት የመኪና ኪራይ ድርጅት ነው፤'ሁለት መቶውም መኪኖች በሙሉ ለዲፕሎማት አጃቢዎት ተከራይተዋል፤ለሰርግ ያከራየነው ምንም መኪና የለም ነው የምትለኝ ከቀናት በፊት ከግማሽ በላዩን በኔ በኩል የመጡት የሊቢያ ልኡካን ተከራይተዋቸዋል፤ግን
እስካሁን መኪና ያላገኙት የጋዳፊ ልኡካን በፕሮቶኮል ሃላፊው በኩል እየጨቀጨቁኝ ነው፤በጣም ተጨንቂያለሁ፤የቬኑስ የመኪና ኪራይ ድርጅት እና የቡቡ ካር ሬንታል ስልኮችን እየጠበቅኩ ነው፤ እነሱ
ካልደወሉልኝ we are all scrwed up! Seriously!”
ኡስማን ተከዘ፤
“ይህ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ መኪና ውስጥ ነው እንዴ የሚካሄደው? ምንድነው ይሄን ሁሉ ቆርቆሮ
ማርመስመስ”
«እኔንም ገርሞኛል…ደግሞ አንዳቸውም በውድ መኪና ካልተንቀሳቀሱ የተዋረዱ ነው የሚመስላቸው
:እንዳንዴ “ሁሉንም በአንበሳ አውቶቡስ ሞጅሮ ማሳፈር ነበር” እላለሁ.…እውነቴን ነው! ህዝባቸው ገና ከፈረስና በቅሎ ትራንስፖርት አልወጣም እነሱ 2007 መርሲዲስ ካልሆነ አልሳፈርም ይላሉ…ብሽቆች! »
«…በለው ኡስማን! ቀውጢ ፖለቲከኛ ሆንኩብኝ ባንዴ!» ሳቅኩባት
ያም ሆነ ይህ…ስብሰባው የመኪና አከራዮችንም በገንዘብ ያንበሸብሻል ማለት ነው! እኔ እኮ አንተና
የኢትዮጵያ መንግስት ብቻ ነበር ከዚህ ስብሰባ የምታተርፉ የሚመስለኝ» አልኩት ሳቄን አስከትዬ፡፡
ፈገግ አለ፤
ኡስማን የለኮሳት ፈገግታ ገና ሳትከስም ሞባይሉ አቃጨለ፡፡ የደዋዩን ማንነት ካወቀ በኃላ ደንገጥ ብሎ ቆሞ
ማናገር ጀመረ፡፡በአረብኛ ነው የሚያናግራቸው፡፡
መርሃባ ያ ሰይዲ…ማፊ ሙሽኪላ ያ ሰይዲመርህባ.አይዋ!.…አይዋ!…” የሚሉትን ቃላት ደጋግሞ ሲናገር
እሰማዋለሁ፡፡ “ችግር የለም ጌታዬ፣ ታዛዥ ነኝ ጌታዬ!” እንደማለት ነው፡፡ ከበድ ካለ ሰው ጋር እየተነጋገረ
እንደሆነ ገመትኩ፡፡ የስልክ ንግግሩን ሲጨርስ ተመልሶ ቁጭ አለ፡፡
ይቅርታ አድርግልኝና እንደዚህ ስትሽቆጠቆጥ አይቼህ አላውቅም…ምንድነው ጉዳዩ ንጉስ ፉዓድ
ነው የደወለልህ?” አልኩት በቀልድ መልክ፡፡
💫ይቀጥላል💫
Like 👍ማድረግ እንዳይረሳ ከ 130 👍 በኋላ ቀጣዩ ክፈል ይቀጥላል
ማንኛዉንም አስተያየት እንዲሁም በቀጣይ #እንዲቀርብ #የምትፈለሸጉትን #መፅሀፍ በ @atronosebot አድርሱን

👍9❤1