#የመኖር_ልኬ
ሰይጣን ከፈጣሪ እንዴት ይፏከራል?
እግዜርስ ከሰው ጋር እንዴት ይማከራል?
ድንቢጥ ሐሳብ ይዞ ከሰማይ ጋር መዋጋት
ደመና ላይ ምሎ ነፋስን መዘንጋት።
መርከብ ሳያበጁ መልሕቅ መወርወር
ከውቅያኖስ ጠልቆ ከውሃ መሰወር።
ጭላንጭሏ ኩራዝ ፀሓይን ረስታ
ጣራ አልባ ጎጆዋ ዝናብ ተመኝታ
ከማይችሉት መግጠም ከማይደርሱት ቦታ።
ውስጤ እንደዚህ ነው! የሚያግደረድረው
ሐሳቤ እንደዚህ ነው! የሚወዳደረው።
ስሜቴ ከልቤ እየተደበቀ
ነፍሴ ከምኞቴ እየተሳበቀ ፣
(ልቤ ትቢያ ቀረ . . .!)
ሚዛኑን ረስቶ እየተመዘነ
መመዘኛ ስቶ እየተተመነ ፣
ከማያሸንፈው እየተጋጠመ
የሽንፈቱን ጕዞ እየደጋገመ ፣
እየደጋገመ እየደጋገመ . . .
እያልጎመጎመ . . .!
ይኸው አለኹ አለ. .!
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
ሰይጣን ከፈጣሪ እንዴት ይፏከራል?
እግዜርስ ከሰው ጋር እንዴት ይማከራል?
ድንቢጥ ሐሳብ ይዞ ከሰማይ ጋር መዋጋት
ደመና ላይ ምሎ ነፋስን መዘንጋት።
መርከብ ሳያበጁ መልሕቅ መወርወር
ከውቅያኖስ ጠልቆ ከውሃ መሰወር።
ጭላንጭሏ ኩራዝ ፀሓይን ረስታ
ጣራ አልባ ጎጆዋ ዝናብ ተመኝታ
ከማይችሉት መግጠም ከማይደርሱት ቦታ።
ውስጤ እንደዚህ ነው! የሚያግደረድረው
ሐሳቤ እንደዚህ ነው! የሚወዳደረው።
ስሜቴ ከልቤ እየተደበቀ
ነፍሴ ከምኞቴ እየተሳበቀ ፣
(ልቤ ትቢያ ቀረ . . .!)
ሚዛኑን ረስቶ እየተመዘነ
መመዘኛ ስቶ እየተተመነ ፣
ከማያሸንፈው እየተጋጠመ
የሽንፈቱን ጕዞ እየደጋገመ ፣
እየደጋገመ እየደጋገመ . . .
እያልጎመጎመ . . .!
ይኸው አለኹ አለ. .!
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
👍1