አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዝናባማ_ምሽት

ደጁ ረጥቦ በ'ምባ~ሰማይ ባለቀሰው
በጎዳናው ማዕዘን~አይሄድም አንድ ሰው
ውዴ እኔና አንች~በከተማው መሀል ብዙ መንገድ አልፈን
ከመንገድ መብራቶች~አንዱን ተደግፈን
ተቃቅፈን በካፊያ~ፍቅርን የሞቅንበት ያ ጣፋጭ ውብ ማታ
ትዝ ይለኛል ሁሌም~ምሽቱን አስታኮ የዘነበ ለታ
ዝናባማው ሌሊት~አንች የሌለሽበት
አስተክዞኝ በሀሳብ~ይዞኝ ሄዶ ድንገት
ደጅ የጣለው ዝናብ~ቤቴ ሆኜ አራሰኝ
ያለፈው ትዝታ~አንችን ሲያስታውሰኝ
የምጠለልበት ናፈ'ኩት ገላሽን
ቀላቅሎ ጣለና ዝናብ ትዝታሽን
አስታውሳለው......................................
መሬቱ ርጥብ ነበር ጎርፍ ይንቦጫረቃል
አልፎ አልፎ ይሰማል የሚያስፈራ መብረቅ
በመስመር ብልጭታ ሰማይ ሲሰነጠቅ
በውሀ ነጠብጣብ መሬት ስትደለቅ
ዝናቡን ሊጠለል ሰው ገብቶ ከቤቱ
ከሰው ልንጠለል ከደጅ ወጥተን እኛ
ፍቅርን የሞቅንበት ያ ጣፋጭ ውብ ማታ
ትዝ ይለኛል ሁሌም ሌሊቱን አስታኮ የዘነበ ለታ
አስታውሳለው..........................................
ካፊያው እየጣለ ብርዱ ሲበረታ
ልሞቀው ስጠጋ ፍሙ ከንፈርሽን
በውሀ ነጠብጣብ ውስጥ
ድንገት ብቅ ብሎ ያየሁት መልክሽን
መቸም አልረሳውም......................
በየወቅት ይመጣል ሌላ ክረምት ሆኖ
ትኩስ ጉም ትንፋሽሽ በትዝታ ዳምኖ
ድቅን ይላል ፊቴ~~~ድንግጥ ይላል ልቤ ሁሌም በትዝታ
ምሽቱን አስታኮ የዘነበ ለታ

🔘ቴዲ አፍሮ🔘
👍2