አትሮኖስ
268K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
434 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_7

ደብዳቤዎቹ በዘገዩና ይዘታቸው እየተለወጠ በመጣ ቁጥር ለእኔ ያላት ፍቅር አልቋል የሚል ግምት አደረብኝ። በተለይ ከዶክተር አድማሱ ጋር ያላት ግንኙነት እንደድሮው ቀጥሎ ከሆነ እኔን በእሱ ልትተካኝ ትችላለች የሚለው አስተሳሰብ ሁሌም ያስጨንቀኝ ነበር። ዶክተሩ ባለትዳር ስላልሆነ፣ አንድ ሴት ልጅና አንድ ወንድ ለብቻቸው ሲሆኑ "በመሐላቸው የማይጠፋው ሴይጣን' እንዳያሳስታቸው ሁል ጊዜ እፀልይ ነበር። አንዳንዴ ደግሞ አልማዝ ለኔ የነበራትን ፍቅር ሳስብ "ይህ ሊሆን አይችልም ብዬ እራሴን እየደለልኡ አዕናናለሁ፡፡ ትላንትና ለእኔና ለእሷ የወደፊት ሕይወት ከልቧ የምትጨነቀው ውድ ፍቅረኛዬ በአንድ ግዜ ትከዳኛለች ብሎ ማሰብ የሚከብድ ነበር፡፡ ግን እርግጥ አልማዝ ትወደኝ ነበር? አዎ ትወደኛለች እንጂ! ግን እኮ ፍቅሯ ቀንሶ ቢሆንስ? ይኸማ አይደረግም! ቢሆንም ሰው ነችና ልትሳሳት ትችላለች፣ እያልኩ መጨነቁ ግን አልቀረም፡፡ ለማንኛውም _ መልሱን ከዲያሪው ለማግኘት በማሰብ ስለዚሁ የሚያወራውን አውጥቼ ማንበብ ቀጠልኩ፡፡ መጋቢት 10 ቀን 1976 ዓ.ም "ለአማረ ያለኝ ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ፡፡ ስለሱ ሳስብ የምውልበት ቀን ከማጠናበት ቀን ይበልጣል፡፡ በየቀኑ ማታ ማታ ከቤተመጻሕፍት መልስ ተቃቅፈን ግቢውን መዞር የማይቀር የዕለት ተዕለት ፕሮግራማችን ሆነ፡፡ የግቢው ሰው ሁሉ የሮሜዮና የጁልዬት ተምሳሌቶች እንደሆንን አድርጎ ያየናል፡፡ እኔ ደግሞ የእነሱ መጨረሻ ስለማያምረኝ እንዲህ ሲሉኝ ብዙም ደስ አይለኝም፡፡ በልጅነቴ ያጣሁትን የእውነተኛ እናትና አባት ፍቅር የሚተካ ፍቅር ያገኘሁም ስለመሰለኝ ጁልዬት ሮሜዮን ባጣችበት መልኩ ላጣው አልሻም፡፡ ዛሬ ከአማረ ጋር ለሽርሽር ወደ ድሬደዋ ሄድን፡፡ በተለይ በከዚራ ዛፎች ስር በምሽት የተንሸራሽርነውና ናይት ክለብ ውስጥ ቯልስ የደነስነው የሚረሳ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ያላሰብኩት ነገር ሆነ፡፡ እንደዛ የምወደውና የማፈቅረው ጓደኝዬ ባልጠበኩትና ባልገመትኩት መንገድ የገባልኝን ቃል ጥሶ በሰርጌ ዕለት አቀርብለታለሁ ያልኩትን ክብረንፅህናዬን ገሰሰው፡፡ ይህ ብቻ አልነበረም፤ እኔም በእሱ ላይ የነበረኝን እምነት ናደው፡፡ ያላሰብኩት ነገርም ባላሰብኩበት ወቅት በመፈፀሙ በእጅጉ አዘንኩ፡፡ ግን ካለእሱ ማንም ስለሌለኝና እሱ ለእኔ፣ እኔ ለእሱ ያለን ፍቅር ቢናድ ደግሞ ወደብቸኝነቱ ዓለምና ዳግም ወደ ሐዘን ባህር የምሰምጥ መሆኔን በመረዳቴ ቢከፋኝም እንዳልከፋኝ ሆኜ እንደምወደው ነገርኩት፡፡ እሱም በድርጊቱ እጅግ በጣም ተፀዕቶ ስለነበር በዚሁ ተፅናና፡፡ በድርጊቱ ብናደድም አምላክ ግን ለእሱ ያለኝን ፍቅር እንዳይቀንስብኝ ፀለይኩ፡፡''

ባነበብኩት ነገር ተገረምኩ፡፡ እንዲህ አዝናብኛለች ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ በወቅቱም ይቅርታዋ እና እወድሀለሁ ያለችኝ ከልቧ እንጂ በፍፁም ከአንገት በላይ የተደረገ ይቅርታ አልመሰለኝም ነበር፡፡ አልማዝ በእኔ ላይ ያደረገችው ሁሉ ሆን ብላ በቂም በቀል የፈጸመችው ሊሆን ይችላል ብዬም ገመትኩ፡፡ እውነቱንም ለማወቅ ዲያሪውን አለፍ አለፍ እያልኩ ማንበቤን ቀጠልኩ፡፡ ሚያዚያ 25 ቀን 1977 ዓ.ም "አማረ አብዛኛውን ጊዜ ከማጥናት ይልቅ ከእኔ ጋር እየተዝናና ቀኑን በሙሉ ቢያሳልፍ ደስ ይለዋል፡፡ እኔ ደግሞ ከእሱ ጋር መሆኑን ባልጠላውም ለትምህርቴ የተወሰነ ጊዜ መስጠት እንዳለብኝ ግን ይሰማኝ ነበር፡፡ ሁሌም ከእሱ ከተለየሁ በኋላ ሀሳብ ባህር ውስጥ ሰጥሜ እንዳልቀር መደበቂያዬ የጥናት ደብተሬ ነበር፡፡ ይህም በትምህርቴ ጥሩ ውጤት እንዳመጣ ረድቶኛል፡፡ ቀስ በቀስ የሱ ውጤት እያሽቆለቀለ መምጣት ጀመረ፡፡ አማረ ከእኔ ጋር ከመተዋወቁ በፊት ጎበዝ ተማሪ የነበረ ሲሆን ለአሁኑ ውጤቱ ማሸቆልቆል ሆን ብዬ ያደረግሁት ባይሆንም እንኳ በተዘዋዋሪ ተጠያቂ መሆኔን እኔ ብቻ ሳልሆን ተማሪዎች ሁሉ ያውቃሉ።ይህም በእኔ ላይ ትልቅ ሃላፊነት እንደሚያርፍ እያመላከተኝ በመምጣቱ ይበልጥ ማጥናቴን ተያያዝኩት፡፡ ውጤቴም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጣ፡፡ ለዚህም የዶክተር አድማሱ አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው፡፡ ለዶክተር አድማሱ ታሪኬን ነግሬው ስለነበር እጅግ ያዝንልኝና ይንከባከበኝ ነበር፡፡ እቤቱ በትርፍ ጊዜው ብመጣ እንደሚረዳኝ ቃል ገብቶልኝ ስለነበር ከእኔም በዕድሜ የበሰለና ብዙ ነገር ያየ በመሆኑ በእሱ ላይ ካለኝ እምነት የተነሳ ብቻውን የሚኖር ቢሆንም ምንም ሳልፈራና ሳልጠራጠር በትርፍ ጊዜዬ ሁሉ እቤቱ እየሄድኩ ያስጠናኝ ነበር፡፡ አማረ ይህ ሁሉ ደስ ባይለውም የእኔን ታማኝነት መጠራጠር ስላልፈለገ ደፍሮ ሊያስቀረኝ አልከጀለም፡፡ እርግጥ ከዶ/ር አድማሱ ጋር ከተዋወቅሁ ጀምሮ ከአሳዳጊዎቼና ከአማረ ውጪ ዘመድ ለሌለኝ ምስኪን አንድ ተጨማሪ ዘመድ ማግኘት ስለመሰለኝ ቅርበቴ ይበልጥ እየጨመረ መጣ፡፡ ከዚህም በላይ ዶክተር አድማሱ እንደአስተማሪዬ ብቻ ሳይሆን እንደጓደኛ ያቀርበኝ ነበር፡፤ በዚህም አስጠኚ ብቻ ሳይሆን ሲከፋኝ የሚያበረታታኝ፣ ሣዝን የሚያፅናናኝ፣ ጨዋታውም አፍ የሚያስከፍት ጓደኛ ሆነልኝ። ይሁን እንጂ ከአማረ ጋር ያለኝን ግንኙነት አይወደውም ነበር፡፡ በእሱም የተነሳ ውጤቴ ሊያሽቆለቁል ስለሚችል እንድጠነቀቅ እየደጋገመ

ይመክረኛል። ቀስ በቀስ ግን ለአማረ ያለኝን ፍቅር ጥልቀት እያወቀ ሲመm ጣልቃ መግባቱን ተወ። ስለዚህ ጉዳይ ባነሳ ቁጥር ከፊቴ ላይ የሚያየው የመከፋት ስሜትም ያንን የማይጥም ምክሩን እንዲተው አደረገው::" ሰኔ 20 ቀን 1977 ዓ.ም "የዛሬው ቀን በሕይወቴ ውስጥ የማልረሳውና እናትና አባቴ እውነተኛ ወላጆቼ አለመሆናቸውን ከሰማሁበትና ተጥዬ አግኝተው እንደሚያሳድጉኝ እንጂ እውነተኛ ወላጆቼ እነማን እንደሆኑ እንደማያውቁ በነገሩኝ ዕለት ከነበረኝ ስሜት ጋር አመሳሰልኩት። የዛን ቀን ወላጆቼ እነማን እንደሆኑ፣ ከእነማንና የት እንደተወለድኩ፣ የምን ብሄር ተወላጅ እንደሆንኩ፣ እህት፣ ወንድም፤ አክስት፤ አጎት ባጠቃላይ ዘመዶች ይኑሩኝ አይኑሩኝ ለማወቅ የነበረኝ ጉጉት በኖ የጠፋበት ቀን በመሆኑ፤ በሕይወቴ የማልረሳው የሀዘን ቀን ሆኖ አለፈ፡። አዎ! እውነተኛ የአብራካቸው ክፋይ አለመሆኔን የነገሩኝን ዕለት እጅግ አድርጌ እጠላታለሁ፡ አጋጣሚው እንዲህ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ከአንድ የሰፈር ልጅ ጋር ተጣላንና እኔ በዕድሜ ትንሽ በለጥ ስለምል እያሳደድኩ እደበድበው ጀመር። በመሃል እናትየው መስኮት አጠገብ ቆመው ያዩ ኖሮ እየሮጡ መጥተው ሕፃን ነች እንኳን ሳይሉ ባልወለደ አንጀታቸው ራሴን በተደጋጋሚ ኮረኮሙኝ፡፡ እኔም እያለቀስኩ ለእናቴ ተናገርኩ፡፡ እናቴም በአድራጎታቸው ተናዳ ወደ ሴትየዋ አስከትላኝ ሄደችና፤ "እንዴት ይቺን አንድ ፍሬ ልጅ ጭንቅላቷን በኩርኩም ይመቷታል? ልጅና ልጅ ዛሬ ቢጣላ ነገ ተመልሶ ይገናኛል፣ ነውር አይደለም እንዴ!" ትላቸዋለች፡፡ ሴትየዋ ሰው ዘርጣጭ ስለነበሩ፤ "ዝምበይ ይህችን የማደጎ ልጅሽን ቀጥተሸ ማሳደግ ነበረብሻ ይሏታል፡፡ በወቅቱ ማደጎ የሚለው ቃል ትርጉም አልገባኝም ነበር፡፡ እናቴ ግን በጣም ተናዳ፤ "ምነው ከአፎት የሚወጣውን ቃል ቢመርጡ.፣ ባለጌ!" ትላቸዋለች:: ሴትየዋም በንዴት፤ "ምነው አርፈሽ ብትቀመጪ፣ ንገሩኝ ባይ! ላልወለድሻት ልጅ ጠበቃ መኮኑ ነው? በቅሎ! " ይሏታል፡፡ እናቴ ሲሰርቅ እንደተያዘ ሰው ክው ብላ ደንግጣ ኩምሽሽ አለች፤ "እግዚአብሔር ይይልሽ!" ብላ ምልስ አለች፡፡