🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_6
"እና ምንድነው? ምን ተፈጠረ?'' አለኝ፡፡ “አልማዝ መሞቷን እስካልነገርከኝ ድረስ ወደ ሚቀጥለው ገፅ ማለፍ አልችልም፤ ግዝት አለበት' አልኩት፡፡ እሱም እንደመሳቅ እያለ! "አቶ አማረ፤ እኔ ለጥያቄዎ በሙሉ መልስ የሚሆንዎትን ዲያሬ ሰጥቼዎታለሁ፡፡ ማንበብና አለማንበብ የእርስዎ የራስዎ ምርጫና ውሳኔ ነው" ብሎ ጥሎኝ ወጣ፡፡ ለጥቂት ደቂቃዎች አመነታሁ፡፡ ፊርማውን ትኩር ብዬ አየሁት፤ በእርግጠኝነት የእሷ ፊርማ ነው፡፡ ነፍሴ ተጨነቀች፡ ትንሽ ቆየት ብዬ ግን ራሴን ማታለል ካልሆነ በስተቀር አልማዝ እንደሆነ ሞታለች የሚለውን የራሴን ያልተረጋገጠ ድምዳሜ ይዤ ንባቤን ቀጠልኩ፡፡ "ዓለማያ የደረስኩት ወደ አሥር ሰዓት ገደማ ነበር፡፡ ከጭናክሰን ይዞን የተነሳው አውቶቡስ ቀርፋፋ ስለነበርና ሐረርና ጅጅጋ ላይ ብዙ ስለቆምን ከሚጠበቀው በላይ ዘግይተናል፡፡ ጭናክሰን ተወልጄ ያደግሁባት፣ ከጅጅጋ ከተማ በግምት ሃያ አምስት ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች፡፡ ወይናደጋ የአየር ጠባይ ያላት ሲሆን አብዛኛው ህዝቧ በግብርናና በንግድ ሥራ ይተዳደራል፡፡ የወታደር ካምፕ ያለባት በመሆኗ በተለይ የወታደሩ ቁጥር ብዙ ነው:: በከተማዋ ዙሪያ ከሁሉ በላይ ጫትና በቆሎ በብዛት ይመረታል፡፡ ከጭናክሰን ዓለማያ ድረስ ያለው ርቀት ወደ መቶ ሀምሳ ኪ.ሜ ይጠጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ሲታይ ዓለማያ ከጭናክሰን ቅርብ ስለሆነ ቢያንስ አለፍ አለፍ እያልኩ ወላጆቼን ለመጠየቅ እችላለሁ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አንድ ጊዜ ትምህርት ቤት በተዘጋበት ወቅት አዲስ አበባ አጎቴ ጋ ለእረፍት በሄድኩበት ጊዜ ዓለማያን አልፌ የሄድኩ ቢሆንም ዩንቨርስቲው እዚያው አካባቢ ይሆናል ብዬ ስላልገመትኩ እንደዚህ ቅርብ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበር፡፡ እንዲህ ቅርብ መሆኑን ባውቅ ኖሮ ጠዋት ጉዞ ስጀምር ያፈሰስኩትን ያህል እምባ በሸኚዎቼ ፊት ባላፈሰስኩ ነበር፡፡ የጎረቤት ሰዎች ያደረጉልኝን አሸኛኘት ሳስታውሰው ለምን ያንን ያህል አዝነው በብዛት ሊሸኙኝ እንደወጡ ገርሞኛል፡፡ እኛ ወጣቶቹ እንኳን ላይፈረድብን ይችላል፡፡ አብዛኞቹ ትልልቅ ሰዎች ግን አለማያንና ቅርበቱን ያውቁታልና ለምን እንደዚያ እንዳለቀሱ ሳስብ
መገረሜ አልቀረም፡፡ ህፃን አዋቂው ሁሉ ያለቅስ የነበረው እዚህ ቅርብ አካባቢ እንደምሄድ ሳይሆን በጣም ሩቅ አገር ወይም ወደ ጦር ሜዳ እንደሚሄድ ዘማት አድርጎኝ ነበር። እንደሚመስለኝ ሰፈር ውስጥ ይበን ተወዳጅ ልጅ ስለነበርኩና በሁሉም የምላላክ በመሆኔ አብዛኛው ሰው ይወደኝ ስለነበር ሊሆን ይችላል:: በሌላ በኩል ደግሞ ከተማዋ ትንሽ ስለሆነችና ሁሉም ሰው ቀረቤታ ይችላል በለለግዚያ ጋር ግጭት በተነሳ ከበር ታራ ወደ ጦር ሜዳ ስላለውናንዲህ መያለቀሱ መሸኘት የተለመደ ስላካባናና ሰው መለየቱን እንጂ ሲሄድ እንዲተለውን የመጨረሻ ውጤት ልዩነት ሳያገናዝብ በለመደው መልኩ አልቅሶም ሊሆን ይችላል በማለት አሰብኩ። ብዙ ጊዜ ከወላጆቹ ጋር Eና ሰርቻለሁ:: አብዛኛውን ጊዜ ልብስ ሲገዛልኝ እመጣ ነበር፡፡ ከአዲስ አበባና ሐረር ቀጥሎ ያየሁት ትልቁ ከተማ ገሀል ነው። ከተማው ትላልቅ ፎቅ አይኑረው እንጂ ቆንጆ ከተማ ነው:: ሕዝቦቹም እንደጭናክሰን ሰዎች ኮ ና ግባቢዎች ናቸው፡፡ የአካባቢያችን ሕዝብ ዛሬ ያገኘውን ተካፍሎ መብላት እንጂ ለነገ ብዙም አይጨነቅም፡፡ የሰን ሰው ከዚህ የተለየ መሆኑን እናታው ንሬኛለች:: ሚስጢሩን በሆዱ ይይዛል? ያለውን ገንዘብ የሚያጠፋው ለብቻው ነው፣ በዚህ ላይ ለነገ እግዜር ያውቃል የሚለው አባባል እዚያ አይሰራም ብላኛለች፡፡ እንዲያውም ከዚሁ ጋር ተያይዘ አንድ የሚያስቅ ነገር ነግራኛለች፡፡ ሐረር ላይ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ አንድ ሱማሌ ወደ አዲሰ አበባ ይቀየርና ቀደም ሲል ሐረር ውስጥ የነበረና የሸዋ ተወላጅ ከሆነ ጓደኛው ቤት ሄዶ በእንግድነት ያርፋል፡፡ ያ ጓደኛው ሹፌር ስለነበር ከክፍለ ሀገር አራት ኩንታል ጤፍ በርካሽ ገዝቶ እንደመጣ ለዚሁ ሱማሌ ጓደኛው ይነግረዋል:: ይህንን የሰማው ሱማሌ በመደነቅ፧ "ታዲያ የፈለገ ቢረክስ ይህ ሁላ ጤፍ ምን ያደርግልሀል? ልትሸጠው ነው ?'' ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ባለቤቱም የእነሱን ባህል ያውቃልና በጓደኛው ጥያቄ ሳይገረም፤ "ለምን እሸጠዋለሁ? ክረምት እየገባ ስለሆነ በኋላ ጤፍ ሊወደድ ይችላል፡፡ አሁን ከገዛሁ ለዓመት ይበቃኛል" በማለት ይመልስለታል፡፡ ሱማሌውም አሁንም በመገረም ዓይን ዓይኑን እየተመለከተ፤ "ያባው! አሊያ አንተ አላህ ሆንክ ወይስ ከአላህ ጋር ተማክረሀል? እንዴት አንድ ዓመት ሙሉ በሕይወት እንደምትኖር እርግጠኛ ሆንክ? አለው ብላ ያጫወተችን አይረሳኝም፣
ወደ ዓለማያ ስንሄድ ሌላዋ መንገድ ላይ ያየኋት ከተማ ሐረር ነች፡፡ ሐረር ነፍስ ካወቅሁ በኋላ ወደ አራት ጊዜ መጥቼባታለሁ። ወደዚህ ስመጣ ታዲያ ሁልጊዜ በመንገድ ላይ የማያቸው የባቢሌ የቆሙ ድንጋዮች ምንጊዜም ከሕሊናዬ አይጠፉም፡፡ የድንጋዮቹን ቅርፅና አቋቋም ያየ ሰው እውነት በተፈጥሮ የተገኘ ነው ብሎ ለመናገር ይከብደዋል። በጥሩ ጠራቢ ተጠርበው የተኮለኮሉ ሐውልቶችን ነው የሚመስሉት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አባቴ ሁል ጊዜ ባቢሌ ስንደርስ ኦቾሎኒ ሳይገዛልኝ አያልፍም:: እኔም ዛሬ አውቶብሱን ለቁርስ እንዳቆሙልን አንድ ኪሎ ኦቾሎኒ ገዝቼ እየበላሁ ሐረር ደረስኩ:: ሌላው ሐረርን ሳስብ የማልረሳው ቆንጆዎቹን የሀደሬ ሴቶችንና ሰፈራቸው ጀጎልን ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ እየተጓዝኩ ዓለማያ ደረስኩ፡፡ ግቢ እንደገባሁም በቀጥታ ወደ ሬጅስትራር ቢሮ ሄጄ ተመዝግቤ ከጨረስኩ በኋላ ቁልፍ ተቀብዬ ወደ መኖሪያ ክፍሌ አመራሁ፡፡ ከእኔ ጋር አምስት ሴቶች አንድ ላይ አንድ ክፍል ውስጥ የተመደብን ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ገና ሳያት ዓይኔ ያረፈባትና ለጓደኝነት የመረጥኳት ኤልሳቤጥ ነበረች፡፡ ኤልሳቤጥ የአዲስ አበባ ልጅ ስትሆን መልኳም ሆነ አለባበሷ እጅግ በጣም ማራኪ ነው፡፡ ከሌሎቹም ይልቅ ፈጥና የተግባባችው __ እኔን ስለነበር እርሷም እንደኔው ለጓደኝነት እንደመረጠችኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ከሰው ጋር ፈጥኖ መግባባት ላይ ችግር ያለብኝ ቢሆንም ኤልሳቤጥ ግን ተግባቢና ተጫዋች ስለነበረች ለመግባባት ጊዜ አልፈጀባትም፡፡ ልክ ብዙ ጊዜያትን አብረው እንዳሳለፉ ጓደኛሞች ማታም የቆጥ የባጡን ስናወራ አመሸተን ነው የተኛነው፡፡ እኔ በአንድ ቤት ውስጥ ከብዙ ሰዎች ጋር ስተኛ የመጀመሪያዬ በመሆኑ ልብሴን አውልቄ ለመተኛት ሁሉም እስኪተኙልኝ መጠበቅ ነበረብኝ:: ኤልሳቤጥ ግን እንዲህ ሁላችንም በተሰበሰብንበት አፏ ሥራውን ሳይፈታ ልብሷን አወላልቃና የሌሊት ልብሷን ለውጣ አልጋዋ ውስጥ ገባች:: እርግጥ ቀሚሷ፣ የጡት መያዢያዋና የሌሊት ልብሷ ሁሉ በውድ ገንዘብ እንደተገዛ የሚያስታውቅና የሚያምር ስለነበር እኛ እያለን ብታወልቀው እኛን ያስቀና እንደሆነ እንጂ እሷን የሚያሳፍር አልነበረም:: በዚህ ላይ የሰውነቷ ቅርፅና ጠቆር የገላዋ ቀለም እጅግ ውብ ነበር፡፡ እርግጥ እኛ አካባቢ የተለያዩ ልብሶች በኮንትሮባንድ ከሱማሊያ ስለሚገቡ እኔም ብሆን የለበስኩት ልብስ ለክፉ የሚሰጥ ባይሆንም እንደእሷ ግን በሰዎች መኻል ልብሴን ለማወላለቅ ድፍረቱን እንዲህ በቀላሉ ላገኘው የምችል አልነበርኩም፡፡''