🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_5
ሃምሳ አለቃው መልስ በመስጠት ፋንታ ትኩር ብሎ አየኝና፣ "አቶ አማረ ከዚህ, ባራት በወንጀል ተከሰው ወይም ታስረው ያውቃሉ?" ብሎ ያልጠበኩትን ጥያቄ አቀረበልኝ:: ያን መሰል ጥያቄ ይቀርባል ብዬ ስላልጠበቅሁ ክው አልኩ። ይኸን ታሪክ ምን ከወንጀል ጋርር ኣያያዘው? ነው ወይስ ከተሾመ ጋር መደባደሽን ስለነገርኩት ወንጀለኛ አድርጎ አይቶኝ ይሆን? ግን ይኸ ሊሆን አይችልም ?? ምናልባት የአልማዝ ጉዳይ ከወንጀል ጋር የተያያዘ ቢሆንስ? ግን ምን ሆና ይሆን? ተደብድባ ወይስ ተገድላ ይሆን? ሞት! ሞት እንኳን በፍፁም አይሆንም፡፡ እንኳን ሞቷን ከባድ እንቅልፏን እንኳ ማየትም ሆነ መስማት አልሻም፡፡ የሆነው ሆኖ ጥያቄውን መመለስ ግዴታ ነውና ምን መመለስ እንዳለብኝ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ እርግጥ ተከስሼና ታስሬ አውቃለሁ፡፡ የታሰርኩት ግን በደረቅ የሌብነት ወይም በሌላ ተመሳሳይ ወንጀል ሳይሆን በፖለቲካ ነው:: ነገር ግን ይህንን ሰፊ ታሪካዊ ተጋድሎና ታሪክ እየተነተነ ለደርግ ሃምሳ አለቃ መናገር ማለት በዶሮ ፊት ስለፈንግል እንደማውራት የሚቆጠርና ሌላ የከፋ ጣጣ የሚያመጣ ስለነበር፤ “አዎ ታስሬአለሁ፣ ነገር ግን በወንጀል ሳይሆን በፖለቲካ ነው" አልኩት ቀለል ባለ ሁኔታ፡፡ ወዲያው ፖለቲካው ምን እንደነበር እንኳን ሳይጠይቀኝ የተማርኩ በመሆኔና ፀጉሬም ጎፈሬ ስለነበር ሌላ ላይሆን ይችላል በማለት ይመስላል፣ አንዴ አንቱ አንዴ አንተ እያለ እየቀያየረ የሚጠራብኝን ቃል ወዲያው ወደ አንቺ ለውጦ፣ "አሃ ኢሕአፓ ነሻ! " አለኝ፡፡ ሣይታወቀኝ በውስጤ ተናደድኩ፡፡ ላመል ታህል ኮስተር ብዬ፤ "አዎ! ግን ይኼ ከመጣሁበት ጉዳይ ጋር ምንም የሚያገኛኘው ነገር የለም፡፡ ደግሞም መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ምሕረት አድርጎልኝ ከእስር ተፈትቼያለሁ:: ይልቁንስ ስለመጣሁበት ስለ አልማዝ ሁኔታ ለምን አትነግረኝም?'' አልኩት፡፡
ሃምሳ አለቃ አደፍርስ እኔን ትቶ አጠገቡ ካለው አስር አለቃ ጋር ማንሾካሾክ ጀመረ። ወሬያቸርስ እኔን ትረሱ ኣደ እኔ ዞር ብሎ ፤ "አቶ አማረ አንተን ያለምክንያት የምናነጋግርህ ይልቅ ለከ ሰማህ ተሳስተሃል፡፡ ከአንተ ልንሰማ የምንፈልገው ታሪክ ከአንተ ይልቅ ለእኛ ያለው ጠቀሜታ የጎላ ነው የታሪኩ መድበስበስ ወይችን ኣስደብ ብ ማወቅ የምንፈልገውን መረጃ ሊያድበሰብስ ይችላልና እውነቱን ሳትደብቅ ብትነግረን ላንተም ሆነ ለእኛ የተሻለ ነው፡፡ ስለዚህ ስለእሷም ሆነ ስለሁለታችሁ ግንኙነት ማወቅ የሚገባንን በሙሉ ብትገልፅልን እኛ ደግሞ በተራችን ስለእሷ ታሪክ ማወቅ የምትፈልገውን ልንነግርህ እንችላለን" አለኝ ፡፡ የሕይወት ታሪኳን ማወቅ ፈልጎ ይሆናል በማለት እና ሌላም አማራጭ ስላልነበረኝ ቀጠልኩ፡፡ “አልማዝ የተወለደችውና ያደገችው በሀረር ክፍለ ሀገር ጭናክሰን በተባለ ቦታ ነው:: ገጠር ውስጥ ትደግ እንጂ ቤተሰቦችዋ ሀብታም ገበሬዎች ስለነበሩ አስተምረው ለዩንቨርስቲ አብቅተዋታል፡፡ ይሁን እንጂ ምስቅለቅል ከሆነው የቤተሰብ ታሪኳ ጋር ተያይዞ ሕይወቷ በአብዛኛው ደስታ የራቀው ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ዘወትር ትሳቅ እንጂ ደስተኛ አልነበረችም፡፡ በአጭሩ የአልማዝ ታሪክ ይኼ ነው፡፡'' አልኩት፡፡ በመሃል ሃምሳ አለቃው አንድ የረሳውን ነገር እንዳስታወሰ ሰው አስር አለቃውን በጥድፊያ ተጣርቶ፣ "ሂድና ከመረጃ ቢሮ ዲያሪውን ይዘህ ና! " ብሎ ላከው፡፡ ይኼ እንቆቅልሽ የሆነ ሀምሳ አለቃ በቀላሉ እንደማይለቀኝ እየገባኝና ትእግስቴም እያለቀ በመምጣቱ፤ "ሃምሳ አለቃ፣ እኔ ከእርሶ ዲያሪ ጋር ምንም ጉዳይ ስለሌለኝ ይልቅ የአልማዝን ሁኔታ ቢያሳውቁኝና ብሄድ፡፡ ደግሞም ሥራ አለኝ " አልኩት፡፡ "ስለ ሥራችንና አሠራራችን ልትነግረኝ የምትችል አይመስለኝም፣ ወይም አይገባህም" አለኝ ኮስተር ብሎ፡፡ ዲያሪው እስኪመጣ መጠበቅ ነበረብን፡፡ እኔ ግን ውስጥ ውስጡን መብከንከን ጀመርኩ፡፡ አይገርምም? ለእኔ የፖሊስ ዲያሪ ምን ያደርግልኛል? የፖሊስ ዲያሪ ያው እዚህ ቦታ ላይ አንድ ወንጀለኛን ለማደን ሄደን እጅ አልሰጥ ብሎ ለማምለጥ ሲሞክር ተኩሰን እግሩ ላይ መትተን ያዝነው፡፡ አሊያም የኢሕአፓ ወንበዴዎች በሌሊት ወረቀት እየበተኑና መፈክር ግድግዳ ላይ እየለቀለቁ ሲያበላሹ ደርሰን እጅ ከፍንጅ ያዝናቸው ወዘተ የሚል ነው፡፡ ይኸ ደግሞ እኔ ከመጣሁበት ጉዳይ ጋር
የማይገናኝ ለእኔም ፋይዳ የሌለው ነገር ነው:: ከዚህ በላይ ደግሞ እንደእኔ ሐሳብ ከሆነ የፖሊስን የሥራ ዝርዝር ታሪክና አልማዝን የሚያ እንዳእኔ ምንም ነገር እንዲህ በማሰብ ላይ ላሁ:: አስር አለቃው አንድ መለስተኛ መጽሐፍ የሚያክል ዲያሪ ይዞ ከች አለ፡፡ ሃምሳ አለቃ አደፍርስም ዲያሪውን ተቀብፍ አቀበለኝና፤ "አቶ አማረ፤ ይህ የአልማዝ ዲያሪ ነው፡፡ የእርሶን ጥያቄ በሙሉ ስለሚመልስ ያንብቡት :: ስለአልማዝ መረዳት የሚፈልጉትን በሙሉ እዚህ ውስጥ ማግኘት ይችላሉ" ብሎ ሻይ ወይስ ቡና እንደምፈልግ ጠይቀኝ:: ዲያሪውን ቶሎ የማንበብ ፍላጎት ስላደረብኝ ወጣ፡፡ ቡና እንደምፈልግ ነግሬው ዲያሪው የአልማዝ ዲያሪ መሆኑን እንዳወቅሁ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ውስጥ ገባሁ፡፡ "ያለጥርጥር ሞታለች ማለት ነው" አልኩ፡፡ አለበለዚያ እንዴት ዲያሪዋ ሊገኝ ይችላል? አልማዝ ምንም ትበድለኝ እንጂ ክፉዋን የምመኝና የምፈልግ ሰው አይደለሁም፡፡ ለእሷ ያለኝ ፍቅር ከዕለት ዕለት እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ የሚሄድ አይደለም፡፡ የመሞቷንም ነገር ሳስብ ልቋቋመው የማልችል የሀዘንና የተስፋ መቁረጥ ስሜት አንዣበበብኝ: የተስፋ መቁረጥ ስሜቴም ገንፍሎ ድምፅ ሳላሰማ ተንስቀሰቅሁ፡፡ ግን እንዴት ሊሆን ቻለ? ሞታም ከሆነ ሰው ገድሏት መሆን አለበት፡፡ አለበለዚያ እኔም እዚህ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ተጠርቼ ባልመጣሁ ነበር። ግን ማን ገድሏት ይሆን? ገዳይዋ በእርግጠኝነት ባይታወቅ ነው እንጂ ቢታወቅ ኖሮ እኔን እንዲህ ባላስጨነቁኝ ነበር፣ እያልኩ ማውጣትና ማውረዱን ተያያዝኩት፡፡ ያም ሆነ ይህ ከፊት ለፊቴ የቀረበውን እውነታ ማወቅ ነበረብኝና እምባ የወረደበትን ፊቴን ጠራርጌ ዲያሪውን አነሳሁ፡፡ ዲያሪው ቢያንስ ከመቶ በላይ ገፆችን የያዘ ወፍራም መጽሐፍ ሊወጣው ይችላል፡፡ ግን ማወቅ የምፈልገውን ነገር እስከሰጠኝ ድረስ ማንበብ ስለነበረብኝ ማንበቡን ተያያዝኩት፡፡
አጭር መማጸኛ
"በአገራችን ኢትዮጵያ ምንም እንኳን እያንዳንዱ ሰው የራሱን ታሪክ እየፃፈ ማስቀመጥ እምብዛም ያልተለመደና አዲስ ባህል ቢሆንም ጠቃሚነቱን መረዳት በቻልኩበት ወቅት ላይ ስደርስ ቢያንስ ከዩንቨርስቲ ጀምሮ ያለውን ታሪኬን ዕፎ ማስቀመጥና ለትውልድ ማስተላለፍ ጉዳት የሌለውና ጥቅሙ ግን የበዛ መሆኑን በማመኔ እነሆ ከዛሬ መስከረም 20/1975 ዓም ጀምሮ፣ ማለትም ለመጀመሪያ ጊዜ የዩንቨርስቲውን ደጃፍ ከረገጥኩበት ጊዜ አንስቶ ያሳለፍኳቸ ን ውሎዎች፣ ያጋጠሙኝን ችግሮችና ያገኘኋቸውን ደስታዎች በዚህ ዲያሪ ውስጥ አስፍሬአለሁ፡፡ ይህንን ዲያሪ እኔ ካለፍኩ በኋላ ለባለቤቴ ወይም ለልጆቼ፤ እነዚህ ከሌሉ ደግሞ ዕድሜ ሰጥቶቸው መቆየት ከቻሉ ለብቸኛ ዘመዶቼ ማለትም ለእናቴ ወይም ለአባቴ በውርስ እንዲተላለፍልኝ ይሁን:: ነገር ግን ከሁሉም በላይ አደራ የምለው በማንኛውም መንገድ እኔ በሕይወት እያለሁ ዲያሪዬን ከጥንቃቄ ጉድለትም ሆነ ወይም በሌላ መንገድ ከእጁ ወጥቶ ማግኘት የቻለ ሁሉ ከዚህ ገፅ አልፎ ወደ ውስጥ በመዝለቅ የሕይወት ታሪኬን እንዳያነብ በፈጣሪ ስም እማፀናለሁ፡፡" አልማዝ አስፋው መስከረም 20 ቀን 1975 ፊርማ አለበት ወዲያውኑ ወደሚቀጥለው ገፅ ከመሄዴ በፊት ንባቤን አቁሜ ሃምሳ