አትሮኖስ
269K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
435 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_15


“ስማ አቶ አማረ ከእኛ የሚያመልጥ ነገር አለ ብለህ አስበህ ከሆነ ተሳስተሀል፡፡ እኔ ከደሙ ንፅህ ነኝ፤ በአልማዝ ግድያ ውስጥ እጄ የለበትም ብለህ እኛን ለማሳመን እየጣርክ ከሆነ እኛን ሳይሆን እራስህን እያታለልክ መሆኑን ብትረዳ ጥሩ ነው፡፡ ይልቅ እኛን ከማድከም ውጪ የምታገኘው አንድም ነገር የለምና እውነቱን ብትናገር የተሻለ ነው" ብሎ የአልማዝን ሞትን ባልጠበቅሁት ሰዓት ድንገት ሲያረዳኝ ራሴን ስቼ ወደቅሁ:: ከዚያ በኋላ የሆነውን ነገር ሁሉ አላስታውስም፡፡ በቀዝቃዛ ውሃ የራሰ ፎጣ ፊቴ ላይ ሲያስቀምጡብኝ ራሴን ከሳትኩበት ሁኔታ ነቃሁ፡፡ የነበርኩትም ምርመራ ክፍል ውስጥ ሳይሆን እስር ቤቱ ክሊኒክ አልጋ ላይ ነበር። እርጥብ ፎጣ ፊቴ ላይ ያደረገችልኝ ነርስ ከፊት ለፊቴ ቆማ መንቃት አለመንቃቴን ለማወቅ ስሜን እየደጋገመች "አቶ አማረ..." "አቶ አማረ…." እያለች ትጣራለች።

“ሲስተር የት ነው ያለሁት? ምን ሆኜ ነው የመጣሁት?" ብዬ ጠየቅኂት:: ስለአመጣጤ ሁኔታ ከነገረችኝ በኋላ ግን ሃሳቤን መሰብሰብ ጀመርኩ። ቀስ በቀስ የምርመራው ክፍልና የመጨረሻው መርዶ ትዝ እያለኝ መጣ። አዎን አልማዝ ሞታለች፡፡ ለእኔ የእሷን መሞት መስማት እጅግ መሪር ሐዘን ነበር። ሞቷ ፍጹም ያልጠበቅሁት ነገር ስለነበር ሐዘኑ ውስጤ ድረስ ዘልቆ ሲገባ ተሰማኝ፡፡ አዎ! አበባዬ ተቀጥፋለች፡፡ ከዛሬ ነገ ትመm ይሆናል እያልኩ በተስፋ የኖርኩበት ዘመን አክትሞ መጨረሻው ይኸው ሆነ፡፡ ለአልማዝ ያለኝ ጥላቻ ሁሉ በአፌ ዙሪያ የሚራገብ ተራ ቃል እንጂ ከውስጤ የሚመነጭ አልነበረም:: ዛሬም ውስጤ የእሷ ተገዢ ነው:: ለእኔ ሌላዋ ሴት ምኔም-ምኔም አይደለችም:: ፍቅርንና ሚስትን ከአልማዝ በኋላ የማስበውና የምመኘው አልነበረም:: ህልሞቼ ሁሉ ዳግም አግኝቻት ከእሷ ጋር በትዳርና በፍቅር ስንኖር፣ በበደሏ ተፀፅታ ወደ እኔ ስትመለስና ይቅርታ ስትጠይቀኝ የሚያሳዩ የፍቅር ህልሞች እንጂ የጥላቻ ህልሞች አልነበሩም። ዛሬ ግን ሁሉም ነገር ቅዠት ሆኖ ቀረ:: አልማዝ ዳግም ላትመለስ፣ ዳግም ላታየኝ፣ ይቅር ሳትለኝ ወይም ይቅር እንድላት ዕድል ሳትሰጠኝ ለዘላለሙ አሸለበች። ይህንን በማሰብ ላይ ሳለሁ እምባዬ እንደ ጎርፍ እየወረደ የተኛሁበትን አልጋ ትራስ ያረጥበው ጀመር፡፡ ይህም ውስጤ ያለውን ሐዘን ሊያስወጣልኝ ስላልቻለ ስቅስቅ ብዬ እየጮሁክ ማልቀሱን ተያያዝኩት፡፡ ሲስተሯ ሁኔታዬን አይታ በማዘን መልክ፤ "ምን እየሆንክ ነው? ለምንድነው የምታለቅሰው? አሁን እኮ ድነሀል" እያለች ለማፅናናት ብትሞክርም ለቅሶዬ እየጠነከረና መንሰቅሰቄ እየባሰብኝ መጣ:: የለቅሶ ድምፄንም ልቆጣጠረው ባለመቻሌ ፖሊሶቹ ምን ተፈጠረ በማለት ክፍሉን አጣበቡት:: በነገሩ ሁሉም ግራ የተጋቡ ይመስላል፡፡ ግማሾቹ ከመሞት ተርፌ በመመለሴ የማለቅስ፣ ሌላው እስር ቤት በመግባቴ ምክንያት አዝኜ የማለቅስ ሳይመስለው አይቀርም:: ሁሉም ለምን እንደማለቅስ እየደጋገሙ ቢጠይቁኝም፣ ለምንና ለማን እንደማለቅስ ግን መናገር አላስፈለገኝም፡፡ ማን ሊያምነኝ? ትርፉ ከንቱ ድካም ካልሆነ በስተቀር። ሻል እንዳለኝ ወደ እሥር ቤቴ በምመለስበት ግዜ ውጪውን ሳይ መሽቶ ነበር፡፡ወደ እዚህ የመጣሁት በጠዋት ስለነበር ለብዙ ሰዓታት ራሴን ስቼ እንደነበር ተገነዘብኩ፡፡ ግን ይህን ያህል ሰዓት ራሴን መሳቴ ካልቀረ ለምን ጌታ እንድስሰቃይ ሊመልሰኝ እንደፈለገ ሳስብ ግራ ተጋባሁ፡፡ የዚች ዓለም ኑሮ እያሳሳቸው ሞትን ቢቻል በገንዘብ፣ ይህ አልሆን ሲላቸው ደግሞ ለእሱ በመሳልና በመለመን ደጁን የሚያጣብቡት ስዎችን እየወሰደ፤ እኔን

መኖር ያስጠላኝን ሰው ግን ሳልፈልግ በግድ መመለሱ ምን ይባላል? ነው ወይስ እኔን ለመውሰድ እሱም መጠየፉ ይሆን? አልኩ፡፡ እስር ቤት ስገባ አስረኛው ከዓይኔ የሚወርደውን እምባ እንዳየ በሁኔታው ግራ ተጋባ፡፡ ግማሹ ተገርፌ የመጣሁ መስሎት፤ "ቻለው እንጂ ወንድ አይደለህ እንዴ! ቸብ ቸብ ነው ያደረጉህ፣ መች በደንብ መቱህና ነው የምታለቅሰው፡፡ እኛ እንኳን እንዲያ በደም እስከምንጨማለቅ ገርፈውን አላለቀስንም ይላል"፡፡ ሌላው አለመመታቱን የተረዳው ደግሞ፤ "ምነው? ዘመድ ሞተብህ እንዴ?" እያለ የመሰለውን የመላ ምት ጥያቄ ይጠይቀኝ ጀመር፡፡ ይሁን እንጂ ለእነሱም ቢሆን ልነግራቸው የምችለውና ሊያሳምናቸው የሚችል መልስ ስላልነበረኝ ማልቀሱን ብቻ ተያያዝኩት፡፡ ሁሉም ለሚጠይቀኝ ጥያቄ መልስ ሊያገኝ ባለመቻሉ በመጨረሻ ጥያቄውን ትቶ ማዕናናቱን ብቻ ተያያዘው:: እኔ ግን ሀዘኑ ውስጤ ዘልቆ ስለገባ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ተሰማኝ፡፡ የአልማዝ መሞት የመኖር ተስፋዬን አመነመነው፡፡ የህይወት ጣዕሙ ጠፍቶ መራራ ቃናው ብቻ ልቆ ተሰማኝ፡፡ አልማዝ ብዙ ጊዜ ፍቅር የህይወት ቅመም ናት ስትል ሰምቼአለሁ፤ ግን ምን ማለቷ እንደሆነ የገባኝ ገና አሁን ሳይሆን አይቀርም፡፡ ቅመም የወጥ ማጣፈጫ _ ነው፤ ፍቅርም እንዲሁ የህይወት ማጣፈጫ፡፡ ዛሬ አልማዝ የሌለችበትን ሕይወት ሳስበው ይህ ብሂል እውነት ብቻ ሳይሆን እጅግ የላቀ እውነት መሆኑንም ተገንዝቤያለሁ፡፡ እኔ ኖርኳአቸው ከምላቸው የሕይወቴ ዘመናት ውስጥ ጣዕም ያለው ምናልባትም በደስታ የተሞላ ሕይወት ኖርኩ ብዬ የምጠቅስ ከሆነ በእርግጠኝነት ከአልማዝ ጋር ያሳለፍኩትን ሕይወት ብቻ ነው፡፡ በእርግጥም የፍቅር ሕይወት በቅመም የተሞላ ነው፡፡ የማግኘት ጉጉቱ፣ የማጣት ፍርሀቱ፣ የማየት ናፍቆቱና አስጠዪ የሚባለው ቅናት ሁሉም በፍቅር ህይወት ውስጥ ሲሆን ይጣፍጣል፣ ያጓጓልም፡፡ ያ ሁሉ ነገር ዛሬ ሲቀር ሕይወት ትርጉም ያጣል፣ የባዶነት፣ የብቸኝነትና የመሰላቸት ስሜት ፍቅርን ተክተው በማናለብኝነት ይነግሳሉ፡፡ ሃይ ባይ አጥተው ይፈነጫሉ፣ ሕይወትን ቃናና ለዛ ያሳጧታል፡፡ ዛሬ ታዲያ የሆነው ይህ ነው፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ከአልማዝ በኋላ ያለው ሕይወቴ በባዶነት፣ በብቸኝነትና በመሰላቸት ስሜት የተሞላ ይሆናል፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ያ ማራኪ የፍቅር ገጽታዋ፣ ውብ ፈገግታዋ፣ ጣዕምና ለዛ ያለው ጨዋታዋ በቦታው የለም፡፡ በቦታው ባዶነትና ጨለማ፣ ጭካኔና ሀዘን ጥላቻና መሰላቸት

ተተክተውበታል፡፡ አልማዝ ላትመለስ ፍቅርንና ውብ ቅመማዊ ቃናውን ይዛው ሄዳለች፡፡ ይህንን እያሰብኩ ላለ በትዝታ ወደ ኋላ መለስ ብዬ ያኔ ለአልማዝ ገጥሜ የሰጠንት እና አልፎ አልፎ በቃሌ የምልላት ግጥም ትዝ አለችኝ።

ሕይወት ድሮ ለኔ ገንዘብና ሀብት፣
ያሻውን ሸምቶ፣ያሻውን አግኝቶ መሳቅ መደሰት፡፡
ሕይወት ድሮ ለኔ መደሰት መጨፈር፣
ጢምቢራ እስከሚዞረር ድብን ብሎ መስከር፡፡
ሕይወት ድሮ ለኔ ሴትን መለዋወጥ፣
ከዚች ጋር ጨርሶ ሌላዋን ማማረጥ። ሕይወት ድሮ ለኔ መኪና ማማረጥ፣
ቪላ ቤት ገንብቶ በሥልጣን መማገጥ፡፡
ነበር የሚመስለኝ እኔ የማስበው፣
ሀቁን ሳልረዳ እውነቱን ሳላውቀው፡፡
ከአንቺ በኋላ ግን መለስ ብየ ሳየው፣
ሕይወት ለኔ ዛሬ ትርጉሙ ሌላ ነው፣
ምስጢሩ የረቀቀ ሰምና ወርቅ ያለው፡፡
ሕይወት ማለት ፍቅር፣ ሕይወት ማለት ማፍቀር፣
ሕይወት ማለት መውደድ፣
በቅናት ተቃጥሎ እርር ብሎ መንደድ፡፡
ፍቅር ማለት ሕይወት፣

ፍቅር ማለት ስስት፣
የራስን አጥብቆ ሌላ አለመመኘት፣
ሌላን አለማየት፡።