🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_14
ደረጃውን ወርጄ የውጪውን በር ስከፍት፣ “ወዴት ነው? ዲያሪውን አንበብህ ጨረስክ እንዴ?" የሚል ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል ሃምሳ አለቃው ያንን አስፈሪ ፊቱን እንዳኮሳተረ እውጪው በር ጥግ ላይ ቆሞ አየሁት:: ክው ብዬ ደነገጥኩ፡፡ ከፖሊስ ጣቢያ የወጣሁ ይምስለኝ እንጂ ለካስ ሳላውቀው ግቢዬ ዙሪያውን ተከቦ በገዛ ቤቴ ውስጥ ታስሬ ኖሯል፡፡ ያም ሆነ ይህ ምንም እንዳልተፈጠረ ራሴን አረጋጋሁና፤ “አይ ሃምሳ አለቃ፤ ወደ አንተ እየመጣሁ እኮ ነበር። ዲያሪውን አንብቤ ጨርሼዋለሁ:: የታሪኩን ፍጻሜ ግን የምሰማው ካንተ ስለሆነ እየመጣሁ ነበር" አልኩት:: ሃምሳ አለቃው የፌዝ ሳቅ እየሳቀ፤ “ወደ እኔ የምትመጣ ከሆነ፣ ለምን ታዲያ ዲያሪውን አልያዝከውም? ለማንኛውም ዲያሪውን አምጣው" _ አለኝ:: በፍጥነት ወደቤት ተመለስኩና አምጥቼ ሰጠሁት፡፡ “ዲያሪውን ተቀብሎ ከፍርድ ቤት ያመጣውን የመያዢያ ትዕዛዝ አነበበልኝ፡፡ ግራ ተጋባሁ፡፡ ግን እንዴት ፍርድ ቤቱ እኔን ንፁሁን ሰው ተይዤ እንድመጣ ይወስናል? ሃምሳ አለቃውን ስላላመንኩት "ማየት ማመን ነውና" የመያዢያውን ትዕዛዝ እንዲሰጠኝ ጠየቅሁት፡፡ ለካስ እኔ ንፁህ ነኝ ልበል እንጂ ሳላውቀው ወንጀለኛ ሆኜ ኖሮ በእርግጥም ተይዤ እንድቀርብ ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡ አማራጭ አልነበረኝምና አንዳንድ የሚያስፈልጉኝን ዕቃዎች እንድወስድ እንዲፈቅድልኝ ጠየቅሁና ስለተፈቀደልኝ ወደ ቤት ገባሁ፡፡ የተወሰነ ገንዘብ ከሳጥን ለማውጣት ወደ መኝታ ቤት እየገባሁ ላለ አለሚቱን ጠርቼ ጋቢ፣ ፒጃማና አንድ ሁለት ቀለል ያሉ ልብሶች እንደታዘጋጅልኝ ነገርኳት፡፡ በጥያቄዬ ግራ እንደተጋባች በራፍ ላይ የቆመውን ፖሊስ ስታይ ይበልጥ ደንግጣ፤
"ምነው ጋሼ? ደህና አይደሉም እንዴ? ምን ችግር ተፈጠረ? ፖሊሱ ለምን መጡ?" በማለት ጥያቄዋን አዥጎደጎደችው፡፡ ጥያቂዋን እነ የምመልሰው ሳይሆን እኔ ራሴ የምጠይቀው ጥያቄ በመሆኑ መልስ ልሰጣት በልችልም፤ "ምንም ችግር የለም፣ ትንሽ የሚጠይቁኝ ነገር ስላለ ነው፤ ተመልሸ አሁን እመጣለሁ። ይልቅ ልብሱን አዘጋጅልኝ" ብዬ ብሩን ለመውሰድ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡ አለሚቱ የተናገርኩት ሁሉ እሷን ለማረጋጋት የተናገርኩት እንጂ አንዳች ችግር እንዳለ ተገንዝባ ሳይሆን አይቀርም! ልብሶቼን ትንሽ ተንጠልጣይ ሻንጣ ቢጤ ውስጥ ከትታ ሳሎኑ ውስጥ እያለቀሰች ጠበቀችኝ፡፡ እኔም ያሳመንኳት ይምሰለኝ እንጂ ለሚቀጥሉት ቀናት የሚያስፈልገኝን ጓዝ በመጠቅለል ላይ እያለሁ፤ “አሁን ተመልሼ እመጣለሁ' ማለቴ እንኳን እሷን የአምስት ዓመት ህፃንንም ቢሆን የሚያሳምን አልነበረም፡ ልብሶቼን ተቀብዬ፣ እንዳታለቅስ አባብያትና አረጋግቼያት ከጨረስኩ በኋላ ተሰናብቼያት ከቤት ስወጣ በራፍ ላይ ቆሞ ሲከታተለኝ የነበረው ፖሊስ ከፊት ለፊት አስፓልቱ ጠርዝ ላይ የቆመችውን የፖሊስ መኪና በእጁ እያሳየኝ ወደ'ዚያ እንድሄድ ነገረኝ:: መኪና ውስጥ ስገባ የፈራሁት እንደደረሰ ገባኝ፡፡ እኔ መሀል፣ ከግራና ከቀኝ ሁለት ፖሊሶች፣ ከፊት ለፊት ሃምላ አለቃው ሆነን እየከነፍን ስንጎዝ መጨረሻዬ እሥር ቤት እንደሆነ ገመትኩ፡፡ እኔን፣ ምናልባትም ሳያውቅ "ወንጀል የሠራ ንፁህ ወንጀለኛ" ይዛ መኪናይቱ ተፈተለከች:: ከመሀልም አጣብቂኝ ውስጥ አስገብተውኝ ሲከንፉ ወንጀለኛ ሳልሆን ሰላም በሌለበት ሀገር ውስጥ የአሸባሪዎች ጥቃት ለመከላከል ሲባል በፀጥታ አስከባሪዎች ከለላ የሚጓዙ የአንዳንድ ሐገሮች ፕሬዜዳቶችን ሁኔታ ታየኝ:: ልዩነቱ እኔ እንደእነሱ ተከብሬ ሳይሆን ወንጀለኛ ሳልሆን እንደወንጀለኛ ተቆጥሬ የምጓዝ መሆኔ ነው:: የአጃቢዎቹን ማንነትና የምጓዝበትን አቅጣጫ ተመልክቼ ወደ እዚያው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ፅ/ቤት እየሄድኩ መሆኑን አውቄአለሁ:: መኪና ውስጥ ከገባሁ ጀምሮ ከጎኔ የተቀመጡት ፖሊሶች በጎሪጥ፣ ሃምሳ አለቃው ከኋላ በሚያሳይ መስታወት ውስጥ ሰረቅ እያደረጉ ከሚያዩኝ ውጪ ለምን እንደምሄድ፣ ወዴት እንደምሄድ፣ ወይም በሌላ ጉዳይ ላይ አንዲት ቃል እንኳ ትንፍሽ ያለ ሰው አልነበረም:: ፖሊስ ጽ/ቤት ስንደርስ ከቀኝ በኩል የነበረው ፖሊስ ዘሎ ወረደና የጠመንጃውን አፈሙዝ ወደ መሬት ተክሎ "ውረድ!" የሚል የቁጣ ቃል መተንፈሱ ትዝ ይለኛል፡፡
አንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ካስገቡኝ በኋላ ሃምሳ አለቃው ከጎኑ የነበረውን ፖሊስ ሰዓት ጠይቆ አስራ እንድ እንደነገረው፣ ሰዓት ተኩል መሆኑን "ከአሁን በኋላ ምርመራውን ማካሄድ አንችልም፡፡ ሌላ የያዝኩት አስቸኳይ ቀጠሮ ስላለ ነገ ምርመራውን እናካሂዳለን፡፡ አሁን ወደ እስር ቤት ውሰደው::" የሚል ቁጣ አዘል ቀጭን ትዕዛዝ ሰጥቶ እየተጣደፈ ከቢሮ ወጣ። ተረኛው ፖሊስ በጣቶቹ ጫፍ እየገፈተረ ከቢሮ ካስወጣኝ በኋላ ወደ ሌላ ቢሮ ወስዶ ቦርሳዬን፣ የጫማ ማሰሪያ ክሬን፣ ቀበቶዬን፣ ሰዓቴንና የወርቅ ሀብሌን ተረክቦ ወደ እስር ቤት ወሰደኝ:: ደግነቱ ገንዘብ ቦርሳዬ ውስጥ ሳይሆን ሸሚዜ ውስጥ ስለማስቀምጥ ያን ስሰማው የምፈራውን የእስር ቤት የሻማ ክፍያ ገንዘብ በመያዜ ትንሽ ተረጋጋሁ፡፡ ፖሊሱ ገፍትሮ እስር ቤት ውስጥ ከወረወረኝ በኋላ በሩን ዘጋብኝ። ከብርሀን ወደ ጨለማ በመግባቴ ሰውን እየረጋገጠኩ ስራመድ፤ እንደፈራሁት እስረኞች ሆን ብለው የሚጠልፉኝ ስለመሰለኝ ዱላው ሳይበዛ የሻማ ለመስጠት እጄን ወደ ሸሚዜ ከተትኩ:: በመሀሉ አንዱ እሥረኛ እጄን ይዞ እየመራ ወደ ጥግ ወስዶ አስቀመጠኝ:: የሻማው ክፍያ ጥያቄ ከአሁን አሁን ይጀመራል በማለት የልቤ ምት ደረቴን መርገጥ ጀመረ፡፡ አንድ ጠብደል እሥረኛ ወደ እኔ ሲራመድ አየሁና ብሩን አውጥቼ እንዲቀበለኝ እጄን ዘረጋሁ፡፡ እስረኛው ግን ብሩን በመቀበል ፋንታ፤ “አይዞህ ተረጋጋ! ብሩም አንተ ጋ ይቀመጥ፤ ሲቸግረን ትሰጠናህ" ብሎ ትከሻዬን መታ መታ አድርጎ ከበስተኋላዬ ተቀመጠ። ዱላው የሚቀር ባይሆንም ወዲያውኑ አልተጀመረም:: ይሁን እንጂ ለዱላውም ቢሆን መጀመሪያ መረጋጋቴ የሚፈለግ ስለመሰለኝ ሙሉ በሙሉ ከፍርሀት ልወጣ አልቻልኩም፡፡ ቀስ በቀስ ዓይኔ ጨለማውን እየለመደ ሲመጣ ክፍሉ በእስረኞች ጥቅጥቅ ብሎ መሞላቱን ማየት ጀመርኩ:: እስረኛው ወለሉን ሞልቶ ቁጭ ብሎ፤ ግማሹ ያወራል፣ ግማሹ ከልብሱ ላይ ተባይ እያደነ ይገድላል፣ ሌላው ይሳሳቃል፡፡ እኔን ግን ከቁብ የቆጠረኝም አልነበረም። “ከተረጋጋ'' ውጪ የመጣ ዱላም አልነበረም። ምሽት ላይ የእስር ቤቱ የውስጥ ሀላፊ (ካቦ) ሁሉም ፀጥ እንዲል ትእዛዝ ከሰጠ በኋላ ሁላችም ለፀሎት እንድንነሳ አዘዘ:: በጣም ገረመኝ፡፡ በእኔ ግምት እዚህ ያለው ግማሹ ነፍስ ገዳይ፣ ሌላው ዘራፊ፣ ሁሉም _ አሥርቱ ቃላትን በአንድ ወይም በሌላ መልክ ጥሶ የታሰረ ስለሆነ እግዚአብሄርን ይፈራል ወይም ያውቃል፤ ቢያውቅም ለእግዚአብሄር ቁብ ይሰጣል የሚል
ቅንጣት ግምት አልነበረኝም:: ግን ባልጠበቅሁት ሁኔታ ሁሉም ፀሎቱን የሚያካሂደው ከልቡ ነበር። የፀሎቱ መዝጊያም እግዚአብሄር የሰሩትን ኃጢያት ይቅር ብሎ ከእሥር እንዲያስፈታቸው መማፀንን የሚጨምር ነበር:: ከፀሎቱ ሥነሥርዓት በኋላ የሚካሄደው ፕሮግራም አዲስ የገቡ እሥረኞች ትውውቅና የታሰሩበትን ምክንያት ለቤቱ እንዲያስረዱ መጋበዝ ነበር። በዚሁ መሰረት ከእኔ በፊት የገባ አንድ እሥረኛ ራሱን ሊያስተዋውቅና የታሰረበትን ምክንያት ሊያስረዳ ተነሳ፡፡ “ስሜ አንበርብር ይባላል፤ የታሰርኩት አንድ አፓርታማ ላይ ተንጠልጥዬ ወጥቼ የተስጣ ልብስ ሰርቂ ላመልጥ ስል አንድ የጎረቤት ሰው ያዘኝና ልቀቀኝ ብለው አለቅ ሲለኝ በጩቤ ሆዱ ላይ ወግቼ አመለጥኩ፡፡ ከዚያ በኋላ አንድ ልብሶቹን የሸጥኩለት ልጅ