አትሮኖስ
269K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
434 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_13

መጋቢት 14 ቀን 1980 "እንቅልፍ ሳይወስደኝ ቢነጋም ጠዋት ቀስቃሽ ሳያስፈልገኝ ዝግጅቴን ተያያዝኩት:: ዶ/ር አድማሱን ጠራሁት፡፡ እሱ ግን በሩን አልከፈተም፡፡ ልሰናበተው ፈልጌ ደጋግሜ አንኳኳሁ፡፡ ሊሸኘኝ ሆነ ሊሰናበተኝ ፍቃደኛ አልነበረም:: በአጨካከኑ ተገረምኩ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለፍቅር ሲል መጎዳቱን እያሰብኩ፣ ልይዘው ካሰብኩት ዕቃ ውስጥ በጣም አስፈላጊዬ ያልሆነውን ቀንሼና ሽክሜን አደላድዬ ሻንጣዬን ይዤ ከቤት ወጣሁ:: አሸክም ከመዳን አንፃር እንዲሸኘኝ ብፈልግም በሌላ በኩል ደግሞ ተኮራርፈን ከሚሸኘኝ ራሴ ብሸከም ይሻለኛል ብዬ በመወሰኔ፤ ዶ/ር አድማሱ : አልሸኘኝም ብዬ ምንም ቅር አላለኝም፡፡ ከቅጥር ግቢው ወጣ እንዳልኩ ወደ ኋላ ዞር ብዬ ከግቢው መግቢያ በር አናት ላይ የተፃፈውን “አለማያ ግብርና ዩንቨርስቲ" የሚለውን ፅሁፍ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አየሁት:: ከግቢው እንደወጣሁ ሰውነቴን የመቅለል ስሜት ተሰማኝ፡፡ ውስጤን ደስታ እንኳን ባይሆን ደስታ የሚመስል ነገር ወረረው፡፡ ከብዙ ዓመታት በኋላ ከእስር ቤት የተፈታሁ ያህል ሆኖ ተሰማኝ:: ይህ ግቢ ለእኔ ትምህርት ቤት ብቻ አልነበረም፡፡ ብዙ ውጣ ውረድ ያየሁበትና ደስታና ሀዘንም የተፈራረቁብኝ ቦታ ነው፡፡ ለጥቂት ጊዜያት ብቅ ብሎ የደበዘዘው የፍቅር ሕይወት፣ በእንቆቅልሽ የተሞላው የፍቅር ህይወት፣ ገላዬን ብቻ በመስጠት ዓይነት የተመሰረተ “የትዳር" ህይወት፣ ጥላቻ፣ ክህደትና ፍቅር የተፈራረቀበት ህይወት፣ ለእኔ የግቢው አይረሴ መገለጫ ነበር። ሻንጣዬን በጀርባዬ አዝዬ እየተንገዳገድኩ በቀጥታ ወደ መኪና መሳፈሪያ ገሰገስኩ፡፡ ወያላው “ድሬዳዋ! ድሬዳዋ!" እያለ ወደሚጮህበት "ኮስትር' መኪና አመራሁ:: ተሳፋሪ እስከሚሞላ ድረስ የጠበቅሁበት ሰዓት ግን የሚያልቅ አልነበረም:: በህይወቴ በጭንቀትና በፍርሀት የተሞላ ቶሎ አላልቅ ያለ ረዥም የጥበቃ ሰዓት ይህ ሳይሆን አይቀርም:: ከአሁን አሁን ዶ/ር አድማሱ መጥቶ "ነይ ውረጂ!" ይለኛል እያልኩ ከመፍራቴ የተነሳ ልቤ ምቱ ጨምረ። ምንም ያህል ልጨነቅ እንጂ ኮስትሩ የሚሞላ አልነበረም፡፡ በተለይም የመጨረሻዎቹ ሁለት ወንበሮች ሊሞሉ አልቻሉም :: ያለኝ አፋጣኝ

የመፍትኄ አማራጭ አንድ ነበር፤ ይኸውም ወያላውን ጠርቼ የቀሪውን ሁለት ወንበር ሂሳብ እንደምከፍለው ነግሬ ጉዞ ጀመርን። ጉዞ እንደጀመርኩ ግን አንድ ነገር ገረመኝ፡፡ ይኸውም ምንም እንኳ የእሱን መምጣት ባልፈልገውም፤ "ዶ/ር አድማሱ እንዴት እንዲህ በእኔ ሊጨክን ቻለ?* የሚለው ነበር። ከግቢው እየወጣሁ በነበረበትና መኪናው ውስጥ ሆኜ ዓይነ ማየት እስከሚችለው ድረስ ግቢ ግቢውን ባይም ብቅ አላለም ነበር:: በዚህም ምክንያት ፍቅር በሱ ውስጥ ስለመኖሩም መጠራጠር ጀመርኩ:: ዓይኖቼ የግቢውን አጥር ርቀት ተከትለው ከመኪናው ጋር አብረው ነጎዱ:: የግቢውን አጥር የመጨረሻ ማዕዘንን ስንጨርስ ግን በረዥሙ ተንፍሼ "እፎይ" አልኩ፡፡ ግልግል! ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ! አጠገቤ ያለው ሰውዬ በግርምታ ተመለከተኝ፡፡ በሆዱ "ምን ስታደርግ አድራ ነው እንዲህ በጠዋቲ የደከማት?" ሳይል አይቀርም:: ከዓለማያ እየራቅን በሄድን ቁጥር ልቤ በፍጥነት መምታቱን አቆመ ውስጤም በደስታ ተሞላ፡፡ አውቶቡሱ ወደ አለማያ ዩንቨርስቲ የሚያስገባውን መታጠፊያ መንገድ ጨርሶ ወደ አለማያ ከተማ አመራ፡፡ ቀስ በቀስ ከከተማው ግራና ቀኝ የተሰለፉትን የባህር ዛፎች እየተመለከትን ወደ ደንገጎ ቁልቁለት ገባን:: ይህም ለእኔ የትዝታ መንገድ ነው:: ያኔ ለመጀመሪያ ግዜ ደንገጎ ቁልቁለትን ስንወርድ ዓይኔን በፍርሀት ጨፍኔ አማረ ደረት ላይ ተለጥፌ ነበር። አሁን ግን በተደጋጋሚ ስለተመላለስኩበትና ፍርሃቴም ስለለቀቀኝ የምሽጎጥበት ደረት አላስፈለገኝም፤ አልፈራሁምም:: ዳሩ ቁርጥ ቀን ሲመጣ እንዲህ ነው፤ ዓይንን ጨፍነው ሊለጠፉበት ቢፈልጉስ ደረት ከየት ሊገኝ? ልመደው ሆዴ ነው ነገሩ፡፡ በሐሳብ ባህር ተውጬ ስለነበር ድሬደዋ _ ስገባም አልታወቀኝም። የምሄደው አዲስ አበባ ቢሆንም የመኪናም ሆነ የባቡር ቲኬት ለማግኘት አንድ ቀን ድሬደዋ ማደር የግድ ነበር፡፡ መኪናው እንደቆመ ዕቃዬን በአንድ ኩሊ አሸክሜ አልቤርጎ ፍለጋ ጀመርኩ:: የከዚራ ዛፎችንና የድሬ የጭፈራ ቤቶችን ሳያቸው እንደደንገጎው ሁሉ ከአማረ ጋር ተቃቅፈን በየመንገዱ ላይ ስንሳሳም የነበረውን ግዜ አስታወሱኝ:: ይህቺ አገር ለኔ የተለየች ሀገር ናት፡፡ ከሁሉም በላይ ክብረ ንፅህናዬን ያስረከብኩባት አገር ስለሆነች በህይወት ታሪኬ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት: ምንጊዜም እዚህ በመጣሁ ቁጥር ትዝ የሚለኝ ያቺ ከአማረ ጋር ያሳለፍኳት ደስታና ለቅሶ የተፈራረቁባት ሌሊት ነበረች፡፡ ከመቅጽበት አቅጣጫዬን ለውጬ ወደዚያች ታሪካዊዋ ሆቴል አመራሁ:: ቤቱ አርጀት ከማለቱ ውጪ ያው የድሮ መልኩን እንደያዘ ነው፡፡ ለየት ያለ ነገር ቢኖር፣ ያኔ ስመጣ ያስተናገደችን ሴት አስተናጋጅ ስትሆን፣ አሁን ግን አስተናጋጁ ወንድ መሆኑ ነው፡፡ ወደ ሆቴሉ እንደተገባ ፊት ለፊት

እንግዳ መቀበያ /Reception/ የሚል ጽሁፍ የተለጠፈባት ጠባብ ክፍል ያለች ሲሆን፣ እንደገባሁ ከአስተናጋጁ ጀርባ ያለውን የቁልፍ መስቀያ መመልከት ጀመርኩ:: የአብዛኞቹ ክፍሎች ቁልፎች መደርደሪያው ላይ የሌሉ ቢሆንም እኔ የምፈልገውና የሌሎች የተወሰኑ ክፍሎች ቁልፎች ግን ተንጠልጥለዋል፡፡ ይህም ማለት እነዚህ ክፍሎች አልተያዙም፣ አሊያም የተከራዩአቸው ሰዎች ወጣ ብለዋል ማለት ነው፡፡ እኔም ሁኔታውን ለማወቅ ከመቻኮሌ የተነሳ አስተናጋጁን የጠየቅሁት አልጋ አለ? ብዬ ሳይሆን፣ "205 ቁጥር ተይዞል እንዴ?" በማለት ነበር :: እሱም በመገረም መልክ ተመለከተኝና “አልተያዘም" ብሎ ቁልፉን ሰጠኝ ፡፡ ሂሳቡን ከፍዬ በጥድፊያ ወደ ክፍሉ አመራሁ:: ከፊት ለፊት ወደ መኝታ ቤቶቹ የሚወስድ ጠባብ ኮሪዶር ያለ ሲሆን፣ በኮሪደሩ ግራና ቀኝ የመኝታ ክፍሎች ይገኛሉ፡፡ ምንም ያህል ጊዜው ቢረዝምም ቁጥሩን ባላይ እንኳ የምፈልገውን ክፍል መለየት ግን የሚሳነኝ አልነበርኩም፡፡ ሁለተኛው ፎቅ ላይ፣ በስተቀኝ በኩል፣ አራት መኝታ ቤቶችን አልፌ የማገኘው መኝታ ቤት የእኔና የአማረ መኝታ ቤት እንደነበር እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ እንዳሰብኩትም ክፍሎቹን ቆጥሬ የያኔውን አምስተኛው ክፍል ላይ እንደደረስኩ ቀና ብዬ አየሁ፡፡ በእርግጥም ቁጥሩ 205 ነበር፡፡ ከመቸኮሌ የተነሳ ቁልፉን አንዴ እየገለበጥኩ፣ ወዲያው ደግሞ መዞር ወደማይገባው አቅጣጫ _ እያዞርኩ _ ለመክፈት ትግሌን ተያያዝኩት፡፡ የሚገርመው ግን ልክ ሰርቆ እንደመጣና _ ለመሸሸግ _ እንደተቻኮለ ሰው ስጣደፍ፣ እጄ ቁልፉን መያዝ እስከሚያቅተው ድረስ ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ እንደምንም ታግዬ በሩን ከከፈትኩና ውስጥ ገብቼ ከዘጋሁት በኋላ ግን እፎይታ ተሰማኝ፡፡ የድንጋጤዬ ምክንያት ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ትዝታ ካልሆነ በስተቀር ዶክተር አድማሱን ፈርቼ እንደማይሆን ግን እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ክፍሉ ውስጥ እንደገባሁ በትክክል ማደር እምፈልግበት ክፍል መሆኑን ሳረጋግጥ ደስታ ተሰማኝ፡፡ ቢያንስ ዛሬ ከአማረ ጋር እተኛሁበት አልጋ ላይ አድራለሁ፡፡ ቢያንስ ዛሬ እነዚያን የመከራ ቀናት ትዝታዎች ረስቼ ከአማረ ጋር ያሳለፍኩትን የፍቅር ሌሊት እያስብኩ አድራለሁ አልኩ፡፡ ምናልባትም ሁሌ በህልሜ አብሮኝ ለማደር መጥቶ ላቅፈው እጄን ስዘረጋ፤ የጣውንቱ ቤት ሆኖበት ሳይሆን አይቀርም፣ እልም ብሎ የሚጠፋው አማረ፣ ዛሬ ሌሊት ግን ወደዚያች ጊዜያዊ ክፍላችን ተመልሼ ስለመጣሁ ሳይደብረው አብሮኝ ሊያድር ይችላል ብዬም