አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኩል_እና_ጥላሸት (2)

የወጋ ከረሳ ፥ የተወጋም ይርሳ
መልክ የሰጡት ቁስል
“ንቅሳት” ነው ስሙ ፥ ጌጥ ሲሆን ጠባሳ

ይህንኑ ጉዳይ
ስንመለከተው ፥ በሌላኛው በኩል
ኩልም ጥላሸት ነው ፥ ጥላሸትም ነው ኩል!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ኩል_እና_ጥላሸት (1)

ሁሉ አዋቂ ነኝ ሲል ፥ እውቀቱ አይታይም
ሁሉ ፃድቅ ነኝ ባይ ፥ ቅንጣት አይፀልይም
ሁሉ እኩል ነን ይላል ፥ የለም አንድም እኩል
የአንደኛው ጥላሸት ፥ ላንዱ ይሆናል ኩል
መደማመጥ የለም!
አፍ እየተገኘ ፥ በጆሯችን በኩል።
ነፃ አውጪው ብዙ ነው ፥ ማንም ነፃ አልወጣም
ሁሉም “ማር ነኝ” ይላል ፥ ሬትነት አያጣም
"ላንተ ስል ታግዬ
ላንተ ስል ቆስዬ” ፥ የሚለው ይበዛል
ሁሉ አዳኝ ነኝ ይላል ፣ ሁሉ ጣር ያበዛል
ማወቅ የተሳነው ፥ ባዋቂ ያፌዛል
ጆሮ እየሸጠ ; ሁሉ አፍ ይገዛል
ተናጋሪ ብቻ!
ለፍላፊነት ብቻ!
ቀልድና ፌዝ ብቻ ፥ ባ'ገሩ ገነነ
“መፅዋች ነኝ “ሚል በዛ ፥ ፅድቅ እየለመነ።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘