#ከሳሽን_መስክርልኝ_ይሉታል
አለሌ ነበርኩ፤ ከሕንድ እስከ እብድ የቀረኝ የለም የምል አለሌ! የተኛኋቸው ሴቶች ጠቢቡ ሰለሞን ከተኛቸው የሚያንስ አይደለም፤ አልቆጠርኳቸውም እንጂ፡፡
ጀንጅኜ መዳረሻዬ ማራኪ ሆቴል ነው። ሆቴሏ ከመኖሪያዬ ራቅ ያለች ሸጎጥ ያለ ሰዋራ ስፍራ ላይ የምትገኝ ነች። አስተናጋጆቹም ምቹ ናቸው። በእርግጥ ጉርሻ ምቹ የማያደርገው የለም። ፈረንጁ እና መስኪ የሚባሉ አስተናጋጆችን የበለጠ አውቃቸዋለሁ፤ ጠብ እርግፍ ብለው ያስተናግዱኛል።
መስኪ የምትባለው አስተናጋጅ ትንሽ ተለቅ ትላለች። ፊት ከሰጠሁት ይጎነትለኛል ብላ ይሆን፣ ተፈጥሮዋ ሆኖ ይሆን፣ ብዙ : ሴት ስለማመላልስ ይሆን፣ ስለማጨስ ወይም ስለምጠጣ ይሆን እኔ'ንጃ ብቻ አትስቅልኝም አትኮሳተርብኝምም። ፊቷ ወጣትነትን ቢሸኝም ውበቷ ግን እንዳለ ነው፤ ምንም ያህል ቲፕ ብሰጣት አመሰጋገኗ ሆነ አስተያየቷ አይለይም፤ ተመሳሳይ ነው፡፡
ክላሴ ውስጥ አጭሼ፣ ጠጥቼ፣ ባልጌ ሹልክ ብዬ በጓሮ እሄዳለሁ። በሌላ ቀን ሌላ ሴት ይዤ እመጣለሁ። ካልጠረረብኝ ሴት አልደግምም። ሁሉንም እንደ ሙዳቸው እና እንደ ፍላጎታቸው እሰክሳቸዋለሁ። ላጤነቴ በነጻነት ታየሁ አልታየሁ ብዬ ሳልሳቀቅ ለመባለግ አግዞኛል።
ጓደኞቼ ሁሉ ሲያገቡ፣ የቤተሰቦቼ የአታገባም ውትወታ በበረታ ወቅት ሶልያና የምትባል ልጅ ተዋወቅሁ። ባገኘኋት በሁለተኛው ቀን ይዣት ለመተኛት በት በት አልኩ፣ ግን አልተሳካልኝም። በውስጤ ስንቷ እንደ አንቺ አካብዳ ጭኗን ሳትከፍት የቀረች የለችም ብዬ ፈገግ ስል
"ምነው?" አለቺኝ።
እርጋታሽ ደስ ይላል
“ውስጤ እንደ ላዬ የተረጋጋ እንዳይመስልህ"
ይሆናል ግን፣ ውስጥም ላይም አንድ ላይ ከመንቀዥቀዥ ይሻላል ስላት
ከንፈሯን ገለጥ አድርጋ ሳቅኩኝ ዓይነት ፈገግ አለችልኝና
"በነገራችን ላይ አንተም ረጋ ያልክ ነህ"
ትዝብት ፈገግ ስልባት
“ውስጥህ ወዲህ ወዲያ ስለሚል ነው እርጋታህ ያልታወቀህ" ይሆናል
ሶልያና የበዛ እርጋታ አላት። እርጋታዋ ይረብሸኛል። ከደስታ ይልቅ ለድብርት አጋልጦ ነው የሚሰጠኝ።
አብሪያት የምሆነው እስክወስባት ድረስ ብቻ ነበር። መስማት ትፈልጋለች ብዬ የማስበውን እነግራታለሁ፣ ሲኒማ እጋብዛታለሁ ትያትር ትጋብዘኛለች ከንፈሯ ጋር ሳልደርስ ቀናቶች ነጎዱ።
የወሲብ ወሬ ለማውራት በጭራሽ አትመችም፤ ወሲብ ነክ ከተወራ ለመቀጠል ፊቷ አይጋብዝም፤ ወሲብ ነክ ቀልድ ባወራ ራሱ ለይሉኝታ እንኳን ፈገግ አትልም። መንፈሳዊ ጉባኤዎች ትጋብዘኛለች፤ ለእሷ ደስ እንዲላት አንዳንድ አሰልቺ፣ አንዳንድ ማራኪ ስብከቶችን እሰማለሁ። ቀልቧን ለመግዛትም መንፈሳዊ መጽሐፍ እያነበብኩ፤ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ዕውቀት አለኝ ዓይነት ወሬ ሳወራት ቀልቧ ሲሳብ፣ ወሬው ሲጥማት አያለሁ።
ሳይታወቀኝ የኔን መንገድ እየተውኩ በእሷ መንገድ መመላለስ ቀጠልኩ። ከሌሎች ስለተለየች ይሆን፣ እንደምፈልገው አለመሆኗ ይሆን፣ የምፈልገውን ስላልሰጠችኝ ይሆን ብቻ ቀልቤን ገዝታዋለች። አዋዋሏን ሥራዬ ብዬ እከታተላለሁ፤ ካልተደዋወልን ይታወቀኛል፤ እንቅስቃሴዋ እየገቡኝ መጡ፤ ሳላገኛት የት እና ምን እያረገች እንደሆነ መገመት ቻልኩ፤ ከደወለችልኝ ስግብግብ ብዬ አነሳለሁ፤ በሂደት መንገዷ ምቾት ሰጠኝ፤ ከተመላለስኩበት መንገድ በተሻለ ይሄኛው መንገድ ጣፈጠኝ። ሶልያና ወሲብ የአካል ልፊያ ሳይሆን የነፍስ ውሕድት እንደሆነ አሳይታኛለች፤ ወሲብ ከፍቅር ውጪ ያልተቆራኘ አድራጎት እንዳልነበር ገባኝ፤ ሳላቀው መርኋን ኮረጅኩ፤ ኑሮ ከበፊት በተለየ ጣፈጠኝ።
የድሮ አመሌ ውል ሲለኝ፣ ይዣቸው የምተኛቸው ሴቶች ውልብ ብዬባቸው ሲደውሉ ሳላቅማማ የድሮ ስልክ ቁጥሬን ቀየርኩ። የትላንት የውድቀት መንገዳችንን ካልቀየርነው ለለውጣችን ሳንካ ይሆናል።
አሁን ፈልጌ መጽሐፍ ቅዱስ አነባለሁ፣ እጾማለሁ፣ ጉባኤ. እከታተላለሁ፣ ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ፣ ከሶልያና ጋ እንፋቀራለን። የትናንት መንገዴን አልተረኩላትም። ለዛሬው ማንነቴ ግን መሀንዲሷ እሷ ናት። ለአምላኬ ስንቴ በእሷ ምክንያት ምስጋና እንዳቀረብኩለት፤ የትናንት ሕይወቴን እንዴት አሁን እንደማልወደው፤ ስለ ሴት አውልነት ሲነሳ ምንም ሐሳብ አልሰጥም።
ያ ዘመን ያሳፍረኛል።
ሶልያና አንድ ዕለት ስትፍነከነክ መጣች። የደስታዋን ምንጭ ስጠይቃት
“እቴቴ ሥራ አገኘች"
የት?
"ባንክ"
በቀላሉ ፍንክንክ የምትል አይደለችም፤ የእናቷ ጉዳይ ግን ስስ ጎኗ ነው፤ ብቻዋን ስላሳደገቻት ይሆን፣ እናት እና ጓደኛዋ ስለሆነች ይሆን፣ ብቻ ስፍስፍ ትልላታለች።
እናቷ ምን እንደምትሠራ አላውቅም ነበር። በትምህርት ያልገፋች ስለሆነች ማጽዳት፣ መላላክ ይሆናል ብዬ ገምቼ ምንድን ነው የምትሠራው፣ የት ነው የምትሠራው ብዬ ጠይቂየት አላውቅም። እሷም ሥራ ነች አልመጣችም፣ ሥራ ቀየረች ነው እንጂ የት እና ምን እንደምትሠራ ነግራኝ
አታውቅም። በረባው ባልረባው ወሬዎቿ መሀል እቴት ሳትል አትውልም። የድሮ ሥራዋስ ስላት፤ “ውይ የድሮ ሥራዋን እኮ አትወደውም ግድ ሆኖባት እንጂ" አለችኝ።
ስለ እኔ እንደ ነገረቻት እና እንደ ወደደችኝ የነገረችኝ ዕለት እንዴት ደስ እንዳለኝ። የምንወደው ሰው በሚወደው ሰው ከመወደድ በላይ ምን ደስታ አለ? ባሻዬ ብላ ቴክስት አደረገችልኝ። (ደስ ስላት እና ስትቀልድ ባሻዬ ነው የምትለኝ)
“ከእቴት ጋ እንደምንመሳሰል ነግሬህ አውቃለሁ ኣ?"
ሁሌ ብዬ የሳቅ ስቲከር ላኩላት።
“እንደ እሷ ቆንጆ ነኝ ግን?" ብላ ፎቶዋን ላከችልኝ። ያየሁትን ማመን አልቻልኩም። ክው! ድርቅ አልኩ፤ የላከችልኝን ፎቶ አገላብጬ አየሁት፤ አልቀየር አለ።
የማራኪ ሆቴል አስተናጋጇ መስኪ የሶልያና እናት ናት። ሁለቱ አብረው ሆነው እና አንድ የመስኪን ማራኪ እንግዳ መቀበያ ጋ የተነሳችውን ፎቶ ላከችልኝ። ውስጤ ታወከ፤ ያ ሴት አውል አብርሃም፤ ያ በየጊዜው ቁጥር ስፍር ከሌላቸው ሴቶች ጋ የሚጋድመው፣ ሱሰኛው አብርሃም፤ ያ በጥሩ አይን አይታው የማታውቀው አብርሃም የአንድ ልጇ ሶልያና እጮኛ ነኝ ብሎ ፊቷ እንዴት ይቆማል??
ትናንቴ ተከተለኝ፤ እግዜር " በተጸጸትንበት ትናንታችን ይቀጣናል እንዴ? ስንቴ ያመሰገንኩበት ጉዳይ መጨረሻው እንዴት እንደዚህ ሆነ??
አንዳንደ ትናንት ትናንት ላይ ብቻ አይቆምም። ዛሬያችንን የፈለገ ከትናንት አርቀን ሰቅለነዋል ብንል እንኳን፣ ጥለነው ብዙ መጥተናል ያልነው ትናንት ነጋችን ላይ በሁለት እግሩ ቆሞ እናገኘዋለን።
በነዚያ ሁሉ የአለሌነት ዘመኖቼ ከእኔ እኩል ዘልዛላነቴን ቆማ የታዘበች እናት ፊት ከልጇ ጎን ቆሞ መታየት አቃተኝ። የማደርገው ጠፋኝ! ጠፋሁ። የሆነውን ሁሉ የማስረዳበት ቋንቋ ስላላገኘሁ ምንም ሳልላት ጠፋሁ።
ብዙ መብከንከን እና ድብርት የተሸከመ ቀን እያለፈ እንዳለ አንድ ተሾመ የሚባል በደንብ የሚያውቀን የጋራ ወዳጃችን ከብዙ ጊዜ በኋላ አግኝቼው፣ ከብዙ ጨዋታ በኋላ ከሶልያና ጋ ስላንተ አንስተን ተጨዋውተን ነበር ሲለኝ ሰፍ ብዬ ምን አወራችሁ አልኩት። ከዲያሪዋ ላይ ፎቶ አንስታ የላከችለትን ምስል ከሞባይሉ እንዳነበው ሰጠኝ።
“አብርሃም እኮ ተለየኝ። በእርግጥ ሰዎችም ስለተለየኝ ራሴን የጣልኩ ይመስላቸዋል፤ ስልኩን ስለማያነሳልኝ ዱካክ እየበላ የሚያሰቃየኝ ነው የሚመስላቸው፤ ከእኔ መሸሹ ብቻ የመቆም ድፍረቴን የናጠው ነው የሚመስላቸው።
ግን አይደለም!
ሁሉን ነገር ተራ ማድረጉ አስደንግጦኝ ነው! አብረን ሳለን ያልወጣንበት የሐሳብ መሥመር፤ ያልተንሸራሸርንበት ስፍራ፤ ያልነገርኩት ገመና አልነበረም፤ ያልሆንነው አለመሆንን ብቻ ነበር!!

❤10👍5