#እንዳለ_ይቀመጥ
ተፋቅረን አየሁ ብልሽ
መጣላት አረግሽው
መሳሳቃችንንም
አላቅሰሽ አረፍሽው
በጥሩ መፍታት ሲቻል
ሁሉን ተቀራርቦ
እኔ አራምባ ስልሽ
አንቺ ካልሽኝ ቆቦ
ህልሜን ከፍቅሬ ጋር
ከምትፈቺው አብረሽ
ከሰለሞን ጥበብ
ካዋቂ ዘንድ ወስደሽ
ሳይቀንስ ሳይጨምር
አስቀምጪው አስቋጥረሽ፡፡
ተፋቅረን አየሁ ብልሽ
መጣላት አረግሽው
መሳሳቃችንንም
አላቅሰሽ አረፍሽው
በጥሩ መፍታት ሲቻል
ሁሉን ተቀራርቦ
እኔ አራምባ ስልሽ
አንቺ ካልሽኝ ቆቦ
ህልሜን ከፍቅሬ ጋር
ከምትፈቺው አብረሽ
ከሰለሞን ጥበብ
ካዋቂ ዘንድ ወስደሽ
ሳይቀንስ ሳይጨምር
አስቀምጪው አስቋጥረሽ፡፡