አትሮኖስ
281K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
482 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እንቆቅልሽ?”


ዘንድሮ ዐሥረኛ ክፍል ከሚጀምው የአጎቴ ልጅ ጋር ፣ "እንቆቅልህ? ምን አውቅልህ? ” እየተጨዋወትኩ ነበር ፡ : በእንቆቅልሽ ሕግ እንቆቅልሹን፣መፍታትና መልስ መስጠት ያልቻለው ሰው ፣ “ሀገር ስጠኝ” ይባልና መሱ
ይነገረዋል ።

ከተለመዱትና ከቀላሎቹ ጀመርን ። ጠያቂዋ እኔ ነኝ ።

“ጸጉሯን አበጥራ ገበያ የምትወጣ?”
.
“እ... አላወቀውም : : ሀገር ልስጥሽ? ።

“አትቸኩል ፤ አስብበትና ሲያቅትህ ፣ እኔ ነኝ ለመልሱ ዘገየህ ብዬ ሀገር ስጥ
የምልህ... እሺ...?

“ካላወቅኩት ሳትጠይቂኝ እኔ ራሴ ብሰጥሽስ?

ዝም ብዬ ቆየሁና ፣ እ... ...ም.. ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ ፤ ቢከብድህም አስብበት... ፍንጭም እሰጥሀለሁ ።

“እ..ሺ!”

“እንዲህ ቢሉ አትታይ፤ እንዲህ ቢሉ አትታይ ”

“እኔንጃ..... ሀገር ልስጥሽ ።

'ዞሮ ዞሮ መዝጊያው ጭራሮ?”

"ይሄንንም አላወቅኩትም ፤ በቃ ሀገር ልስጥሽ ።

ከዚ በኋላ ፣ እኔ ስጠቅ ፤ እሱ ፣ ፍንጭ ልስጥህና ሞክር”

እያልኩ+ ፣ አንዴ እንኳን የግምት መልስ ሳይሞክር ፣ “ሀገር ክስጥሽ” ሲለኝ ፤ ተበሳጭቼ ጨዋታውን አቆምን ።

ልክ ሲሄድ የሚከተለውን፣ አሰብኩ ፤ “እንቆቅልሽ ሲቀርብለት ጊዜ ሰጥቶና ተማክሮ ከመፍታት ይልቅ ሀገር ለመስጠት የሚቸኩለው የአጎቴ ልጅ ፣ ነገ ፓለቲከኛ ከሆነ ይህች ሀገር አለቀላት ።

🔘ሕይወት እምሻው🔘

#MUTE ያደረጋቹ ደሞ ምርጥ ምርጥ ድርሰት አምልጧቹሀል ቶሎ ብላቹ #UNMUTE አድርጉ

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
👍1