#አኮረፈች_መሰል...?
አኮረፈች መሰል . . . ?
ተፈጥሮ ንክ ኾነች
ቀኙን ግራ አረገች።
አኮረፈች መሰል . . .?
ሰማይ ደም መሰለ፤
ነጸብራቅ ተሞልቶ በጥቀረት ተሣለ።
ፍም መሳይ ደመና፣ እንባውን እረጨ
ዑደቱን ሳይጨርስ፣ ዘመንም ተቋጨ።
ጀንበር ተሸሸገች፤ ቀትር ተጠልላ
ከዋክብት አንድ ኾኑ፣ ፀሓይ ተጠቅልላ።
ፀሓይ እኩለሌት፣
ጨረቃም ታስያት፣
ኾኑ ተቀያይረ፤
ምድር ቀን ብታግድ፣ ጸዳልን ረስተው።
አኮረፈች መሰል . . . ?
የምድር ዘልማድ፣
ታሪክ ተረተረት ፣ በ'ውን ተሳከረ
እሳተ ጎመራ በረዶ ጋገረ።
( ሐሩር ቆፈን ኾነ! )
ዛፎች ፣ ዕለት ኾኑ . .
ዕለት ፣ ዛፍ አፈራ
ደርቆ ታየ ፤ ወይራ።
ቅጠልም ያለ ግንድ፣ ያለውም ከሰመ
ግንድም ሥር ሳይኖረው፣ ደርቆ ለመለመ።
አኮረፈች መሰል . . . ?
ባሕሮች ፣
ባ'ርምሞ ተዋጡ
ቅን ፋታን መረጡ።
ከጽሞና ዕብረዉ ፣ ጎርፎችም ዝም አሉ!
ጅረት ሽቅብ ወጣ . . .
ውቅያኖስ ጠብታ ፣ ወንዞች ጤዛ አከሉ።
አኮረፈች መሰል . . .?
አዎ . . . !
አኩርፋ ነው እንጂ፣
የሚኾነው ቀርቶ የማይኾን የኾነው
'ያቺ 'ምወዳት ሴት . . .
ምን ነገር ፈልጋ ፣ ምን ነገር አጥታ ነው ?!
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
አኮረፈች መሰል . . . ?
ተፈጥሮ ንክ ኾነች
ቀኙን ግራ አረገች።
አኮረፈች መሰል . . .?
ሰማይ ደም መሰለ፤
ነጸብራቅ ተሞልቶ በጥቀረት ተሣለ።
ፍም መሳይ ደመና፣ እንባውን እረጨ
ዑደቱን ሳይጨርስ፣ ዘመንም ተቋጨ።
ጀንበር ተሸሸገች፤ ቀትር ተጠልላ
ከዋክብት አንድ ኾኑ፣ ፀሓይ ተጠቅልላ።
ፀሓይ እኩለሌት፣
ጨረቃም ታስያት፣
ኾኑ ተቀያይረ፤
ምድር ቀን ብታግድ፣ ጸዳልን ረስተው።
አኮረፈች መሰል . . . ?
የምድር ዘልማድ፣
ታሪክ ተረተረት ፣ በ'ውን ተሳከረ
እሳተ ጎመራ በረዶ ጋገረ።
( ሐሩር ቆፈን ኾነ! )
ዛፎች ፣ ዕለት ኾኑ . .
ዕለት ፣ ዛፍ አፈራ
ደርቆ ታየ ፤ ወይራ።
ቅጠልም ያለ ግንድ፣ ያለውም ከሰመ
ግንድም ሥር ሳይኖረው፣ ደርቆ ለመለመ።
አኮረፈች መሰል . . . ?
ባሕሮች ፣
ባ'ርምሞ ተዋጡ
ቅን ፋታን መረጡ።
ከጽሞና ዕብረዉ ፣ ጎርፎችም ዝም አሉ!
ጅረት ሽቅብ ወጣ . . .
ውቅያኖስ ጠብታ ፣ ወንዞች ጤዛ አከሉ።
አኮረፈች መሰል . . .?
አዎ . . . !
አኩርፋ ነው እንጂ፣
የሚኾነው ቀርቶ የማይኾን የኾነው
'ያቺ 'ምወዳት ሴት . . .
ምን ነገር ፈልጋ ፣ ምን ነገር አጥታ ነው ?!
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘