#አሃ . . .!
በመጸው ሰማይ ሥር
በቀለም ሸብርቃ
ካ'ዋፋቱም ልቃ
የመስቀል ወፍ ታየች ፤
ወረኃ መስከረም
ለምልማና ደምቃ
ከምድር ማሕፀን
ዐደይ በቅላ ፈካች።
አካል ላባዎቿ .
ከጥዑም ድምጿ ጋር
ከደመናው በላይ
በሰማዩ በራ ፤
ሕብር ፣ ሕብረ ቀለም . .
ከአድማስ ጥግ ላይ
ውብ ቀስተ ደመና
በቃል ኪዳን ሠራ።
ማራኪ ገጽታ ፣
ጤዛ ጠብታዎች
አበባ አካሏ ላይ
እንዳሸበረቁ ፤
ቢራቢሮ ፣ ንቦች
ነፍሳቶች በሙሉ
ከዐደይ ላይ ቀስመው
ሕይወትን ሰረቁ።
ግና . . .
የመስቀል ወፍ ውበት ፣ ድምጿ ቢስረቀረቅ
ዐደይ አበባዋም ፣ ምድሩ ላይ ብትደምቅ
በምን ጥበብሽ ነው . . . ?
ያ'ነኚኽን ውበት፣ ጸጋሽ የሚደብቅ።
ምን ዐይነት ኃይል ነው?
መስህብ ጸጋሽ ኹሉ ፣
አንዳች ምስጢር አለው።
አሃ. . .!
ለካ . . !
ይህ ኹሉ የታየው
አንቺ ስላለሽ ነው።
እኔን የገረመኝ . . .!
ዐደይም ስትረግፍ ፣
የመስቀል ወፍ ስታልፍ
ከመጸው ጋር ዕብራ ፤
ፀሓይም ስትጠልቅ ፣
ጨረቃም ስትጎድል
ዝናቡም ሲያባራ ፤
ጊዜ በቀመሩ
ኹሉን አፈራርቆ
በኃይሉ ሲመራ ፤
ምን ምስጢር ኖሮት ነው . . .?
የቁንጅናሽ ጮራ
በዘላለም ስፍር
ኹሌም የሚበራ።
አሃ . . .!
ለካ . . .!
እንኳንና ኅዋው
ውበትም ራሱ
ካ'ንቺ ነው 'ሚሠራ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
በመጸው ሰማይ ሥር
በቀለም ሸብርቃ
ካ'ዋፋቱም ልቃ
የመስቀል ወፍ ታየች ፤
ወረኃ መስከረም
ለምልማና ደምቃ
ከምድር ማሕፀን
ዐደይ በቅላ ፈካች።
አካል ላባዎቿ .
ከጥዑም ድምጿ ጋር
ከደመናው በላይ
በሰማዩ በራ ፤
ሕብር ፣ ሕብረ ቀለም . .
ከአድማስ ጥግ ላይ
ውብ ቀስተ ደመና
በቃል ኪዳን ሠራ።
ማራኪ ገጽታ ፣
ጤዛ ጠብታዎች
አበባ አካሏ ላይ
እንዳሸበረቁ ፤
ቢራቢሮ ፣ ንቦች
ነፍሳቶች በሙሉ
ከዐደይ ላይ ቀስመው
ሕይወትን ሰረቁ።
ግና . . .
የመስቀል ወፍ ውበት ፣ ድምጿ ቢስረቀረቅ
ዐደይ አበባዋም ፣ ምድሩ ላይ ብትደምቅ
በምን ጥበብሽ ነው . . . ?
ያ'ነኚኽን ውበት፣ ጸጋሽ የሚደብቅ።
ምን ዐይነት ኃይል ነው?
መስህብ ጸጋሽ ኹሉ ፣
አንዳች ምስጢር አለው።
አሃ. . .!
ለካ . . !
ይህ ኹሉ የታየው
አንቺ ስላለሽ ነው።
እኔን የገረመኝ . . .!
ዐደይም ስትረግፍ ፣
የመስቀል ወፍ ስታልፍ
ከመጸው ጋር ዕብራ ፤
ፀሓይም ስትጠልቅ ፣
ጨረቃም ስትጎድል
ዝናቡም ሲያባራ ፤
ጊዜ በቀመሩ
ኹሉን አፈራርቆ
በኃይሉ ሲመራ ፤
ምን ምስጢር ኖሮት ነው . . .?
የቁንጅናሽ ጮራ
በዘላለም ስፍር
ኹሌም የሚበራ።
አሃ . . .!
ለካ . . .!
እንኳንና ኅዋው
ውበትም ራሱ
ካ'ንቺ ነው 'ሚሠራ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘