አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ነገረ_ጦቢያ

አስራ ሶስት ወር ብርሐን - አስራ ሶስት ወር ፀሐይ
አረንጓዴ ምድር - ሰማያዊ ሰማይ፤
አዕላፍ ክዋክብት - አማላይ ጨረቃ
በተፈጥሮ ውበት - የምትታይ ደምቃ....
አገሬ ናት እሷ-
ተፈጥሮ ያሳመራት
ታሪክ ያገነናት፡፡

ከ13 ወር ፀሐይ ፣
የ13 ወር ሌሊት ገዝፎ ሚታይባት
የቀኗ ብርሐን ፣
በሌሊት ጨለማ የተሸፈነባት፣
ሰማያዊው ሰማይ ፣
በአመዳም ደመና የተጋረደባት
አረንጓዴ ምድሯ ፣
በስንፍና አረም የደራረቀባት
አገሬ ናት እሷ-
ሰዎች የበደሏት
ትውልድ ያከሰራት።

🔘በሙሉቀን🔘