አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትቀርያለሽ_ብየ

ግድየለሽምና  ፥ ከልብ ላፈቀረሽ
ሶስቴ ተቀጣጥረን፥ አራት ጊዜ ቀረሽ::

ዛሬም እንደ ወትሮው፥ትቀርያለሽ ብየ
እድል የላከውን፥ እጣ የሚመስል፤ እጦት ተቀብየ፥
አበባ ሳልቀጥፍ
አልጋ ሳላነጥፍ
ሙታንታየን ሳልጥፍ
በትራስጌየ ላይ ፎቶሽን ሳለጥፍ ፥

ትቀርያለሽ ብየ

በመስታውቴ ፊት
ከልብ አስቀይሜ
አንድ እፍኝ ነጭ ሽንኩርት
እንደ ተልባ ቅሜ
አየሩን መርዤ፥ ህዋሴን አክሜ፤

ትቀርያለሽ ብየ
ጥፍሬን ሳልከረክም
በመቀስ ሳልንደው፥ የጉያየን ሸክም
ትቀርያለሽ ብየ
ጀንበርን ቀድሜ፤ ቤቴ ተከትቼ
ግቤን ያለ ረዳት፥ በጊዜ መትቼ
የከሸፈ ትውልድ አንሶላ ላይ ትቼ
ልተኛ ስዘጋጅ፥ እፎይ ብየ አርፌ
ከወደ በራፌ
“ ውዴ! ደርሻለሁ፥ የሚል ድምጽሽ መጣ”
ከመግባትሽ በፊት፥ እኔ በየት ልውጣ?

🔘ቤኩምሳ🔘
😁146👍87👏18😱16🥰154