አትሮኖስ
270K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
437 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
​​#ታላቁ_እልቂት

በዚያ ቀን፣ ልክ የዛሬ 89 ዓመት፣ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በተካሄደው ጭፍጨፋ አዲስ አበባና አካባቢዋ ውስጥ ብቻ ወደ 30 ሺህ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። የየካቲት 12 ሰማዕታት ቀን፣ ዘንድሮ 89ኛ ዓመቱ ላይ ነው። የካቲት 1929 ዓ.ም.የሚያክል ለኢትዮጵያ የመከራና የጽልመት ወራት ኖሮ አያውቁም።በጣም የሚገርመው፣ በዚሁ በወርኃ የካቲት 1888 ዓመተ ምህረትም ከሰባ ሺህ በላይ ወገኖቻችንን መሥዋዕት አድርገናል። ግፈኛው የንጉሥ ኡምቤርቶ ጦር፣ በጄኔራል ባራቴሪ እየተመራ ሃይማኖት ሊቀለብስ፣ መሬት ሊቆርስ፣ ነፃነታችንን ሊገስ መጥቶ ማጭድና ጎራዴ፣ ጦርና ጋሻ የያዙትን በመድፍና በዘመኑ መሳሪያዎች ፈጃቸው።
ከአርባ አንድ ዓመታት በኋላ ተመልሶ ለወረራ የመጣው በማርሻል ሩዶልፍ ግራዚያኒ የሚመራው የፋሺስትም ጦር፣ ከየካቲት 12 ቀን እስከ የካቲት 14 ድረስ ባሉት ሦስት ቀናት ከሠላሳ ሺህ በላይ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያንን ገደላቸው።

#የመታሰቢያ_ሐውልታቸው

ሀውልቱ የወራሪው የጣሊያን ወታደሮች በግፍ የጨፈጨፏቸውን 30ሺ ያህል ሰዎች ለመዘከር የቆመ ነው፡፡ ግራዚያኒ ሰራዊቱን እና መኳንንቱን ጠርቶ ፣ ህዝቡን ሰብስቦ የአሁኑ አዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ ቀደም ሲል ገነተ ልዑል በሚል ይታወቅ በነበረው በአፄ ኃይለስላሴ ቤተ መንግስት ውስጥ የተለመደ የእብሪት ንግግሩን በማሰማት ላይ ነበር፡፡ ግራዚያኒን ለመግደል አመቺ ቦታ እና ጊዜ ሲጠባበቁ የነበሩት አብርሐም ደቦጭ እና ሞገስ አሰግዶም የያዙትን ቦምብ አከታትለው ወረወሩበት፤ ግራዚያኒም ቆሰለ፡፡ ከዚያች ቅፅበት በኋላ በማንኛውም ሁኔታ የተገኘ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በግፍ ተጨፈጨፈ፡፡ አዲሰ አበባም በንፁሀን የደም ጎርፍ ተጥለቀለቀች፡፡ በህፃናት ለቅሶ በእናቶች ዋይታ ተዋጠች፡፡ በወቅቱ የተፈጠረው ሁኔታም ኢትዮጵያውያን በድፍረት እና በወኔ ጠላትን እንዲፋለሙ ብርታት ሆናቸው፡፡ እነዚህን ያለርህራሄ የተጨፈጨፉ ንፁሀን ዜጎች ለማሰታወስም ዛሬ በየካቲት 12 ሆስፒታል ፣ በአዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ እና በቀድሞዉ በአንበሳ ግቢ መካከል 6ኪሎ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የሰማዕታቱ ሃውልት ቆሟል፡፡
በዚህ ሀውልት ቀረፃ ላይ ኢትዮጳያውያን ባለሙያዎችም ተሳትፈዋል፡፡ ሀውልቱ 28 ሜትር ቁመት ያለው ሲሆን ባለ ሶስት ማዕዘንም ነው፡፡ ሀውልቱ የተሰራው በሁለት የዩጎዝላቪያ ዜግነት ያላቸው ባለሙያተኞች ሲሆን በሀውልቱ ላይ ኢትዮጵያውያን በጣሊያን ወታደሮች በግፍ ሲገደሉ የሚያሳዩ ቅርፃ ቅርፆችም ይስተዋላሉ፡፡ ሀውልቱ ከቅርፃ ቅርፆቹ ባሻገር የተለያዩ ፅሁፎችም አሉት፡፡

ክብር #ለተሰውት #ሰማዕታት……..!!!