አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#በመዋጮ_መሥዋትነት_አለቅን!

እኛ ለራሳችን፣ ኑሮ ከቀን ቀን የብረት ዘነዘና ሆኖ እንደጉድ እየቀጠቀጠን፣ እያደር እንዳረጀ የእንጨት ሙቀጫ እንሰነጣጠቃለን ፣በዚህ ለይ ትንሹም ትልቁም ገንዘብ አምጡ ። አዋጡ ይለናል

ለእንትና ክርስትና መዋጮ ፣ ለእገሌ አባት ቀብር መዋጮ፣ ለእገሊት አገባች መዋጮ ፣ የእድር መዋጮ ፣ የማርያም ማኅበር መዋጮ ፣ ጸድቶ
ለማይጸዳ አካባቢ ፣ የአካባቢ ጽዳት መዋጮ፣ ከአጥር ቀለም ባለፈ አረንጓዴነቷ ዕለት በዕለት ለሚያሽቆለቁለው ከተማችን የፅዱና አረንጓዴ አዲስ አበባ መዋጮ ፣ ዛሬ ያስቀመጥነው 4ዐዐዐ ብር ወር 500 ለሚሆነውና ለአመታት ለማናየው የጡረታ መዋጮ ፣ የአባይ ግድብ መዋጮ! መዋጮ! መዋጮ!

ሚጢጢው ገቢያችን ፣ እንኳን ዙረን አክርሮ ጥሎን ለሚበረው ኑሯችን ቀርቶ ፣ በወር ለምንፈልገው መዋጮ እንኳን አልበቃ እያለ ነው ።
ከዛሬ ገቢ ቀንሶ መስጠት ማዋጣት ሳይሆን፣ መሥዋዕትነት መክፈል ነው : : መሥዋዕትነት ብል የአሳማውና የዶሮዋ ታሪክ ትዝ አለኝ : :
ነገሩ እንዲህ ነው ። አቶ አሳማና እመት ዶሮ መንገድ ይገኛውሉ : ጥቂት ካወሩ በኋላ
ዶሮዋ ፣ “ስማ አንድ ግሩም ሐሳብ አለኝ : እኔና አንተ ለምን አንድ ምግብ ቤት በጋራ አንከፍትም?” ትለዋለች ።

አሳማም ፣ “ምን የሚባል ምግብ ቤት?” ይላል።
“የአሳማ ሥጋና እንቁላል ምግብ ቤቶ ብንለውስ? ” ዶሮ ትመልሳለች። አሳማ ዝም ብኰ ሲያስብ ፣ “ "ያው አንተም በሥጋህ እኔም በእንቁላሌ"
ማለት ነው” ብካ ቀጠለች ዶሮ"
አሳማም ትንሽ አሰብ አድርጎ ፣ “ግዴለም ይቅርብኝ ፡ : ይህች ምግብ ቤት ማቅናት ላንቺ መዋጮ ነው ፣ ለኔ ግን መስዋትነት ይጠይቃል ። ብሎ መለሰላት አሉ : :

የኛም ማለቂያ አልባ መዋጮ ፣ ምስኪኖቹ ከእመት ዶሮ ይልቅ አሳማውን፤
እያስመሰለን ነውና አንድ ቢባልስ?

🔘ጨረስኩ🔘

#MUTE ያደረጋቹ ደሞ ምርጥ ምርጥ ድርሰት አምልጧቹሀል ቶሎ ብላቹ #UNMUTE አድርጉ


ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
👍2