አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሹክሹክታዋ

እምቢልታው ሰልችቶኝ
ክራሩ አስጠልቶኝ
በዋሽንት በርግጌ
ባታሞ ደንቁሬ
ከዜማ ከልሳን
ስኖር ተቃቅሬ
ባ'ርምሞ ስጸልይ
ባርምሞዬ ስቀኝ
ሹክሹክታዋን ላከ
ከድምፅ ሊያስታርቀኝ
አያልቅበት ታምር
አያልቅበት ድኂን
ጆሮ እንደ ጉሮሮ
ሹክሹክታ እንደ ክኒን
አድርጎ እያስማማ
ተውሳኬን ነቀለው
ድምፅዋን እያሰማ።

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘