#ራስን_ፍለጋ
በሕይወት አውሎንፋስ
በችግር ማዕበል ሲላተም ሲላጋ
ከተዘፈቀበት
ከገባበት አዘቅት
ሊወጣ ሲታገል ሌት ተቀን ሲተጋ
ዘመናት ሲነጉዱ
ፋይዳቢስ ሲሆን ሲቀር ያለዋጋ
ጭራሽ ሳያስበው አብሮ አደግ ጓዱ
“ራስህን ፈልግ!”
አለና መከረው ቆሞ ከመንገዱ፡፡
በአንክሮ አድምጦ ምክሩን በፀጋ
በአብሮ አደጉ ምክር እራሱን ፍለጋ
ሳይታክት ሳይሰለች
ቀኑ እስኪመሽ ድረስ ሌቱም እስኪነጋ
ከቆላ ወረደ ዘለቀ ከደጋ
ጨርቄን ማቄን ሳይል ሔደ ወይና ደጋ::
ኳትኖ ኳትኖ
ባዝኖ ባዝኖ
ባክኖ ባክኖ ዋትቶ ዋትቶ
ለፍቶ ለፍቶ
ፍለጋውን ትቶ ሳያገኝ እራሱን
ይዞ ተመለሰ ጥያቄና መልሱን፡፡
ለአብሮ አደጉ ሔዶ ልቡ እያመነታ
አለው በፈገግታ:-
“ይኸውልህ ጓዴ አገር አዳርሼ
እራሴን አጥቼ መጣሁ ተመልሼ፡፡
አንተ ጋ ነው የቀረኝ ዞር በልልኝ አንዴ
ራሴን ልፈልግ አትቁም ከመንገዴ::”
እሱ እንደጨረስ እየተነበበ ከጓዱ ቅሬታ
ዞር ቢልለት ለአፍታ
እቆመበት ቦታ
ቁጭ ብሎ አገኘው የሱን ዕጣ ፈንታ::
የገዛ አብሮ አደጉ እራሱን ፍለጋ
ሲኳትን ሲፈጋ
እያየ ዝም ያለው ምንም ሳይነካ
በጫማው ረግጦ
የጋዛ ዕድሉ ላይ ቆሞበት ነው ለካ!!
🔘በፋሲል🔘
17/12/1995
በሕይወት አውሎንፋስ
በችግር ማዕበል ሲላተም ሲላጋ
ከተዘፈቀበት
ከገባበት አዘቅት
ሊወጣ ሲታገል ሌት ተቀን ሲተጋ
ዘመናት ሲነጉዱ
ፋይዳቢስ ሲሆን ሲቀር ያለዋጋ
ጭራሽ ሳያስበው አብሮ አደግ ጓዱ
“ራስህን ፈልግ!”
አለና መከረው ቆሞ ከመንገዱ፡፡
በአንክሮ አድምጦ ምክሩን በፀጋ
በአብሮ አደጉ ምክር እራሱን ፍለጋ
ሳይታክት ሳይሰለች
ቀኑ እስኪመሽ ድረስ ሌቱም እስኪነጋ
ከቆላ ወረደ ዘለቀ ከደጋ
ጨርቄን ማቄን ሳይል ሔደ ወይና ደጋ::
ኳትኖ ኳትኖ
ባዝኖ ባዝኖ
ባክኖ ባክኖ ዋትቶ ዋትቶ
ለፍቶ ለፍቶ
ፍለጋውን ትቶ ሳያገኝ እራሱን
ይዞ ተመለሰ ጥያቄና መልሱን፡፡
ለአብሮ አደጉ ሔዶ ልቡ እያመነታ
አለው በፈገግታ:-
“ይኸውልህ ጓዴ አገር አዳርሼ
እራሴን አጥቼ መጣሁ ተመልሼ፡፡
አንተ ጋ ነው የቀረኝ ዞር በልልኝ አንዴ
ራሴን ልፈልግ አትቁም ከመንገዴ::”
እሱ እንደጨረስ እየተነበበ ከጓዱ ቅሬታ
ዞር ቢልለት ለአፍታ
እቆመበት ቦታ
ቁጭ ብሎ አገኘው የሱን ዕጣ ፈንታ::
የገዛ አብሮ አደጉ እራሱን ፍለጋ
ሲኳትን ሲፈጋ
እያየ ዝም ያለው ምንም ሳይነካ
በጫማው ረግጦ
የጋዛ ዕድሉ ላይ ቆሞበት ነው ለካ!!
🔘በፋሲል🔘
17/12/1995