#ምስጠረ_ሰውነት
ወፍ መሳይዋ ፍጥረት ፣ ፍጠኚ ገስግሺ
ካ'ድማስ ተሻገሪ ፤ አድማስን ልበሺ።
ካስማ መቅደስሽን
ማረፊያ ጎጆሽን
ቅጽር አበጅተሽ ፣
ከባሕር የሚዘልቅ
ልብ ላይ የሚጠልቅ
ምስጢሬን አንግተሽ፤
ፍጠኝ ከዕድሜ ዥረት ፣ ከጊዜ ምናኔ
ደመናውን ፍቺ ፣ ባ'ካልሽ ውብ ቅኔ
ኺጂ ተሻገሪ . . .!
ከተራራው ግርጌ ሳትመሽጊ ደርሶ
የተፈጥሮ ዑደት ኺደቱን ጨርሶ
ፊትሽ ሳይደርስብሽ ፣
እንግዳን ይቀበል ፣ ያማሕፀን ደጅሽ።
ያያ'ርባ መሻገሪያ ሠላሳ ክረምቱ
የመከራን ዕድል አሐዱ ቍጥረቱ፣
ይህ ነው ሕግጋቱ . . .!
በ'ኩሌታ መሞት በ'ኩሌታ መትረፍ
ከሱባዔ መክተም ፣ በምናኔ ማለፍ።
( . . . ልክ እንደ ወፊቱ . . .!)
መንቆርሽ ሳይቆዝም ፣ ጥፍርሽ ሳይታጠፍ
ክንፍሽ ኃይሉ ሳይዝል ፤ ማሕፀንሽ ሳይሠንፍ ፣
ወፍ መሳይዋ ፍጥረት ፣ ፍጠኚ፤ ገስግሺ
ካ'ድማስ ተሻገሪ አድማስን ልበሺ ፤
እውነትሽን እውነቴን ...
ካ'ካሌ ላይ ወስደሽ ፣ አካልሽ ላይ ጻፊ!!
🔘ተሰፋሁን ከበደ🔘
ወፍ መሳይዋ ፍጥረት ፣ ፍጠኚ ገስግሺ
ካ'ድማስ ተሻገሪ ፤ አድማስን ልበሺ።
ካስማ መቅደስሽን
ማረፊያ ጎጆሽን
ቅጽር አበጅተሽ ፣
ከባሕር የሚዘልቅ
ልብ ላይ የሚጠልቅ
ምስጢሬን አንግተሽ፤
ፍጠኝ ከዕድሜ ዥረት ፣ ከጊዜ ምናኔ
ደመናውን ፍቺ ፣ ባ'ካልሽ ውብ ቅኔ
ኺጂ ተሻገሪ . . .!
ከተራራው ግርጌ ሳትመሽጊ ደርሶ
የተፈጥሮ ዑደት ኺደቱን ጨርሶ
ፊትሽ ሳይደርስብሽ ፣
እንግዳን ይቀበል ፣ ያማሕፀን ደጅሽ።
ያያ'ርባ መሻገሪያ ሠላሳ ክረምቱ
የመከራን ዕድል አሐዱ ቍጥረቱ፣
ይህ ነው ሕግጋቱ . . .!
በ'ኩሌታ መሞት በ'ኩሌታ መትረፍ
ከሱባዔ መክተም ፣ በምናኔ ማለፍ።
( . . . ልክ እንደ ወፊቱ . . .!)
መንቆርሽ ሳይቆዝም ፣ ጥፍርሽ ሳይታጠፍ
ክንፍሽ ኃይሉ ሳይዝል ፤ ማሕፀንሽ ሳይሠንፍ ፣
ወፍ መሳይዋ ፍጥረት ፣ ፍጠኚ፤ ገስግሺ
ካ'ድማስ ተሻገሪ አድማስን ልበሺ ፤
እውነትሽን እውነቴን ...
ካ'ካሌ ላይ ወስደሽ ፣ አካልሽ ላይ ጻፊ!!
🔘ተሰፋሁን ከበደ🔘